ወያኔ-ሕወሃትን እንዲጥል የትግራይን ህዝብ እናግዘው! /ከሙሉቀን ገበየው/

ወያኔ-ሕወሃትን እንዲጥል የትግራይን ህዝብ እናግዘው! /ከሙሉቀን ገበየው/

በጥቂት የቤተሰብ አባላት የሚመራው አምባገነን  ወያኔ -ህወሃት በኢትዮጲያን ላይ ለሚፈጽመው በደልና ግፍ እጁ ንጹህ  የሆነውን አብዛኛውን ምስኪን የትግራይ ህዝብ ስም እየተጠቀመና እየነገደበት ነው። አብዛኛው የትግራይ ኢትዮጲያዊ  በተለይም በገጠር ትግራይ የሚኖረው በወያኔ አምባገነን የክፋት አሩጩሜ በገዥው ቤተሰብና ተላላኪ ካድሬዎች እየደርሰበት ነው።

አብዛኛው ምስኪን የትግራይ ኢትዮጲያዊ ለ 27  አመታት ከተጨቆነው ኢትዪጲያዊ በባሰ መብቱን የተነጠቀ ነው። ወያኔን ከመደገፍ ውጪ ሌላ አማራጭ ያለተሰጠው ይህ ህዝብ ከዚያ ቢያፈነግጥ ለእስርት፣ግድያ፣ዝርፊያ እና ስድት ይዳረጋል። ደፍረውም ጥያቄ ያነሱ ብዞዎቹ በመአክላዊ ፌደራል መንግስት በማይታወቅ ተራራ ስር ባሉ እስር ቤቶች ይማቅቃሉ።

በ 17 አመት ጦርነት ምስኪን የትግራይ ኢትዮጲያን እናቶችና አብቶች ልጆቻቸው በወያኔው ሃይል ተገደው ለጦረነት ሰለባ በመደርጋቸውና ከወንድሞቻቸው ኢትዮጲያን ጋር ደም ሲፋሰሱ በመኖራቸው   ሲያለቅሱ ኖርዋል። አብዝኞቹ የልጆቻቸው መሰአወት መሆን ውጤቱ ጥቂቱን  ገዢ የወያኔ ቤተሰብ ዙፋን ላይ ማውጣትና ኢትዮጲያንን ባምባገነንት ማሰቃየት ሆⶈል።

ወያኔ-ህወሃት ኢትዮጲያን በጥላቻ፣ በፍርሃት ድባብ፣ በከፋፍልህ ግዛው መሰሪ አገዛዝ ዘዴቸው ሲገዙ ኖረዋል።የአገራችንን ኤኮኖሚ፣ ወታደርዊ ከፍል፣ ጸጥታ ሃይል፣  ውጭ ጉዳዪን ና ዋና ዋና የመሃበር ሰቡንመገልገያዎች በበላይነት ተቆጣጥረዋል። ብዙ ኢትዮጲያንን በተለይ አማረኛ ና ኦሮሞኛ ተናጋሪውን አስርዋል፣ገለዋል፣አሰቃይተውል፣አፈናቅለዋል፣ዘርፈዋል እንዲሁም ከአገር እንዲሰደዱ አድርገዋል።

ወያኔ ለአግዛዙ ያመቸው ዘንድ የሃሰት ፌድራል ወሰን አዋቅሮ፣ የቤሄረሰብ ተውካዮችን ፊትፊት ወንበር ላይ ያልምንም ስልጣን አስቀምጦ፤ በጓዳ በር በመሰርያ ሃይል ሲገዛን ኑሯል። በከፋፍለህ ግዛው መርዘኛ ፖሊሲው ተጠቅሞ የልዩነት መርዝ እየነሰንሰ፣ በጎሳና በሃይማኖት እንዲሁም በፈጠራ ታሪክና ግነት እያሟሟቀ ሲያጋጨን፣ሲያጣላንና በጠላትነት ሲያሰላልፈን ኖሯል። በዘመኑም በዚህ መሰሪ ጸብ አጫሪነቱ ብዙዎችን ኢትዮጲያን እንዲፈናቀሉ፣ ንብርታቸውን እንዲያጡ፣ሜዳ ላይ እንዲወድቁ፣  አገር ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል።

የአብዛኝውን ምስኪን የትግራይ ህዝብን በወያኔየሚደርስበትን  ጭቆና ግን እኛም ወንድሞቻቸው እንዲሁም ባዳዎችም የውጭ ሃገር ሰዎች  ይህን ያህል አላወቅንላቸውም። ይህም የሆነው አብዛኞቻችን ባለን የተሳሳተ ግንዛቤና ወያኔ ሆነ ብሎ በስማቸው ስልሚነግድ አንድ አድርገን በመውስዳችን ነው። አብዝኞቹ በወያኔው ጥብቅ የስለላ ትብታብ መረብ ውስጥ ስለወደቁ  መርጃ ከነሱ አመልጦ አይወጣም። ትግራይ ከመሓል አገር ርቃ ያልች ክልል በመሆኗና ብዙ የመሀል አገር ሰው ስልማይኖርባት ወያኔው የሚያደርገውን አፈናና ጭቆና እንዳይጋለጥ እንደልቡ የሚደብቅበት ሁኔታ ተመቻችቶለታል። ምስኪኑ የትግራይ ኢትዮጲያዊ በድርብ ጭቆና ላይ ሲሆን ፣ እንደሳንዱች በወንድሞቹ መከራውን አለማወቅና በወያኔው የክፋት ዱላ  መካከል ወድቋል።

በእርግጥ ከወያኔ 27  አገዛዝ ያተርፉ፣ያል አግባብ የበለጸጉ፣ የሚጠቀሙ ጥቂት የማይባሉ የትግርይ ተወላጆች አሉ። እነዚህ አብዛኞቹ ግን ከትግራክልል ውጪ፣ በአዲስ አበባ፣ በሌላው የአገራችን  ከተሞችና በውጭ አገር የሚገኙት ናቸው። እነዚ አገዛዙ  ሆነ ብሎ ባመቻቸላቸው መንገድ የሚዘርፉ፣ ሃብት ያካበቱና ዋና ተጠቃሚ የሆኑ ናቸው። የምናያቸው ሚሊየነሮች፣ ታላላቅ የንግድና ቢዝንስ ባልቤቶች፣ባለሃብቶች፣ ጄኔራሎች፣ የጸጥታ ሃላፊዎች፣ እና የስእራቱ ቁንጮ ቦታዎችን የያዙ  ናቸው። እነዚህ ጥቅመኞች የመንግስትን፣ የማሃበርትን ገንዝብና ንብርት የዘርፉ፣ የባንኩ  ፋይናስን እንደልባቸው የሚጫወቱበትና እንዲሁም የህዝቡን መሬት የሚነጥቁና የሚቸበችቡ ናቸው። ከወያኔ ደግፊ ውጪ ያለ ማንኛውም የተሳካ የንግድ/ቢዝነስ ስራ ሁሉ  በታክስ አለመከፈል በሚል የሃስት ምክንያት  ህዝቡን እያስለቀሱ፡ ወደ እንርሱ ና ደጋፊዎቻቸው ንግዱን/ቢዝንሱን አዙረውታል። አገዛዙ በፈጠርው የፍርሃት ድባብ የሚጠቀሙ ትግሬዎች  ዘምዶቻቸውን ስም እየጠሩና ትግርኛ ቋንቋን  በመሃል እየቀላቀሉ የበላይነት መግለጫና ማስፈራሪያ አድርገውታል።

እንዚ የስርአቱ ተጠቃሚ ትግሪዎች ያካበቱትን ሃብት ተመክተው የወያኔውን አስከፊ አገዛዝ በመደገፈና ማንኝውንም ኢትዮጲያዊ  እንድይቃወመው ሽንጣቸውን ይዘው ይሟገቱለታል። አገዛዙ የሚያደርገውን ወደር የልሽ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት በሰላይነት፣ በስላይ አለቃነት፣ በፖሊስነት፣ በወታደርነት፣ በሚንስተርነት፣ በአምባሳደርነት፣ እንዲሁም ቁልፍ በሆኑ የህብረትሰቡ ክፍሎች ተመድበው የስርአቱን አገዛዝና  የሚጠቡቁና እድሜ  የሚያዝሙ ናቸው። እንዚህ ጥገኛ ተጠቃሚዎች ስርአቱን ለመጠበቅ የማይፈንቅሉትና የማይምሱት ነገር የለም። ካብዛኛው የትግራይ ኢትዮጲያዊ ጋር ሲወዳደሩ ቁጥራቸው አናሳ ቢሆኑም  በሃብታቸው፣ በያዙት ስልጥናቸው፣ ተጽኖ አድርጊንታቸውና ተሰሚነታቸው  ትልቅ ድርሻ ያላቸው ናቸው።

27 አመታት የኢትዮጵ ህዝብ ያደርገው ትግል ባልፉት 2  አምታት ያሳየው እምርታ የወያኔውን ተጽኖ  አንገዳግዶት በተለይም ባለፉት 4 ወራት ውስጥ የፊት፤ ለፊቱን የስልጣን ወንበር ቢለቀም መቀሌ ግን ተሰባስቦ አድፍጧል። እዛም ሆኖ በብዙ ቢሊዮን ዶላር የሚገምት ንብርት ዘርፎ ያካብተውን ገንዘብና ሃይል ይዞ ኢትዪጲያን የለውጥ ሃይሎች የጀምሩትን ሰላማዊ ለውጥ ለማሰናከል  በተለይም በዶ/ር አብይ የሚመራውን አዲስ የለውጥ አመራር ፈተና ውስጥ ለመክተት በዘርፈው ገንዝብ በመጠቀም፣ ቅጥርኞችን በማሰማራት  በተለይም በወንጅለኞቹ እንጋፋ ወያኔዎች አብረታችነት በመሃል አገርና በዳር ወሰን አገር ሁከትና ረብሻ በማንሳሳትና በመጫር ተግቷል። በተለይም ኤፈርት በሚባለው በደም ገንዝብ የተመሰረተ በብዙ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት ያለው የግል ንግድ ድርጅታቸው በመጠቀም በሚጎፍላቸውን ገንዘብ የለውጡን ሂደት ለማስትጓጓልና ለማደናቀፍ እይተፍጨርጨሩ ነው።

መቀሌ መሽገው እንደቆሰለ ነብር እያጓሩና እይተናከሱ ምስኪኑን የትግራይ ኢትዮጵያዊ ህዝብ እንደገና በስሙ ሊነግዱበትና ለደም መፋሰስ፣ ለጦርነት እንዲሁም ከእናት ሃገሩ ኢትዮጲያ ለመገነጠል በማስፈራሪያ እይተጠቀሙበትና እያሰቃዩት ይገኛሉ። ወያኔ  ገዢ ቤተሰ  ህልውናውን ለማስጠበቅ በትግራይ ህዝብ የማይነግደውና የማሰረው ደባ የለም።

በዶ/ር አብይና ጓዶቹ የሚመራው አዲስ የለውጥ ሃይል፣እንዲሁም የኢትዪጲያ ህዝብ በተለይም ወጣቱ፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ና ሙሁራኖች የአብዛኝውን ምስኪን የትግራኢቲዮጲያዊ  ፈተናና ትግል በመደገፍ በስማቸው ከ 40 አመታት በላይ  ከሚነገደው የወያኔ-ህወሃት አስከፊ አገዛዝ እንዲወጡ የማገዝ  የአምሮዊ ሞራል ግዴታ አለበት። የትግራይ ህዝብ ወንድሞቻችን እንድማንኛውም ኢትዮጲያዊ የነጻነት አየር መተንፈስና የወደፊቱን እድላችንን አብርን መወሰን አለብን።

ትግራይ ኢቲዮጵያዊ  ወጣትና ህዝብ፣እንዲሁም በስርአቱ ውስጥ ያሉ ተራማጅ የለውጥ ደጋፊዎችን ጨምሮ በጥቂት የገዢ ቤተሰቦች የሚመራውን ጨኳኝና አምባገነን ለ40 አምታት ሲነግድባቹሁ  የኖረውን የወያኔ-ሕወሃትን በሰላሚዊ ትግል ለመጣል መበርታት አባችሁ። ከእንግዲህ ወዲያ ወያኔ-ህወሃት በትግራይ ህዝብ ቀሚስ ውስጥ መደበቂያ መኖር የለበትም።

ይህን የጸረ-ህብረትና የመከፋፍል አባዜ የተጠናወተውን ወያኔ-ህወሃት  በአሁኑ ግዜ የሚጠነስሰውን ሴራና ጥላቻ ለማስቀርና ለማጥፋት  የተቀረው ኢትዮጲያውያን ከወንድሞቻችን የትግራይ ኢትዮጲያዊ ጋር  በጋራ ቆሟል። የትግራይ ህዝብም ወያኔ-ህውሃት በስምህ እንዳይጠቀሙ በተለይም  የአገዛዙ ተጠቃሚ ትግሬዎች  ሊያስናክሉህ ቢሞክሩም ይህን አልፈህታላቅ እርምጃ አድርገህ ከወገኖችህ ኢትዮጲያን ትግል ተቀላቀል።

LEAVE A REPLY