የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ኮፊ አናን ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ኮፊ አናን ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ኮፊ አናን ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ጋናዊው ከፍተኛ ድፕሎማት ኮፊ አናን የመንግስታቱን ድርጅት ከ40 ዓመታት በላይ እንዳገለገሉ የታወቀ ሲሆን እ.ኤ.አ ከ1997—2006 7ኛው የተባበሩት መንግስታትን በዋና ፀሀፊነት ማገልገላቸውን የታሪክ ማህደራቸው ያስረዳል።

የኮፊ አናን በሰብዓዊ ዕርዳታ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅዖ እ.ኤ.አ በ2001 የኖቤል ተሸላሚ(Nobel Peace Prize) ነበሩ።አናን በተወለዱ በ80ኛ ዓመታቸው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን በርካታ ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት ዘግበዋል።

 ኮፊ አናን በድርጅቱ ውስጥ በነበሩበት ወቅት በተደጋገሚ ስለ ሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ችላ በማለታቸው የደረሰውን የዘር ማጥፋት መከላከል ይችሉ ነበር እየተባሉ በተደጋጋሚ ይወቀሱ ነበር።

LEAVE A REPLY