/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ (የስልጠና ፍኖተ-ካርታ) ለመቀየር ውይይት እየተደረገበት ነው። ውይይቱ ትናንት በይፋ የተጀመረ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድም በቦታው ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። በኢትዮጵያ በተግባር ላይ ያለው የትምህርት ፖሊሲ የታሰበውን ያህል ውጤታማ ባለመሆኑ ሀገራችን በርካታ ችግሮች ሲገጥሟት መቆየቱን ጠ/ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ እንደገለጹት፤ ላለፉት 20 ዓመታት በተግባር ላይ ያለው የትምህርት ፖሊሲ ያስገኘው ጥቅም እንዳለ ሆኖ በአብዛኛው ፍሬያማ አልነበረም ብለዋል።በህክምና፣ፍትህ፣ግብርና፣ፋይናንስና ሌሎች በርካታ መስኮች እየተስተዋለ ላለው የብቃት ማነስና የስነ_ምግባር ጉድለት የትምህርት ፖሊሲው ውጤት ነው ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላየ ጌቴ በበኩላቸው አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊስ ዥንጉር መሆኑንና ወጥነት የሌለው እንዲሁም የፍታሃዊነት ችግር ያለበት ነው ብለዋል።
ለትምህርት ፖሊሲ ማሻሻያ ለውይይቱ የቀረቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦
- የመምህራን ጥቅማጥቅም(ደመወዝ ፣ ቤት፣ ትራንስፖርት ፣ በጡረታ ሙሉ ደመወዝ ይዞ መውጣት ወዘተ)
- 2. ለመምህርነት ሙያ የሚመለመሉ ተማሪዎች መካከለኛ እስከ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ እንዲሆኑ
- 3. በመምህርነት ሙያ የክረምት ትምህርት እንዲቆምና የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ብቻ እንዲሰጥ
- 4. የትምህርት ምዘና ፦
– በ6ኛ ክፍል(ክልላዊ ፈተና)
– በ8ኛ ና 12ኛ ክፍል (ሀገራዊ/ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥ ሆኖ የ10ኛ ክፍል ፈተና እንዲቀር
- 5. የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ እንዲሰጥ(ደረጃ 1 እና 2 = በመደበኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ ደረጃ 3 እና 4 =በኮሌጆች፣ ደረጃ 5=በፖሊ ኮሌጆች እንዲሰጥ)
- 6. የትምህርት ቋንቋም ወደ 4 ከፍ እንደሚል (እንግሊዝኛ፣ አማርኛ፣ የአፍ መፍቻ፣ ከክልሎች ጋር ሊያገናኝ የሚችል ሌላ አንድ ቋንቋ
ወዘተ ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ዝርዝር ፖሊሲን በዳሰሰ መልኩ ረቂቅ የጥናት ሐሳብ ቀርቦ ውይይት ተጀምሯል ።
ውይይቱም ከመላው ሀገሪቱ በተመረጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ሲሆን ከትናንት ጀምሮ ለአምስት ቀናት እንደሚካሄድ ታውቋል።