በሶማሌ ክልል የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ሲከናወኑ መቆየቱን ኢሶህዴፓ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ

በሶማሌ ክልል የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ሲከናወኑ መቆየቱን ኢሶህዴፓ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢሶህዴፓ) የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ለኢቲቪ በላከው መግለጫ የኪራይ ሰብሳቢነትና የሙስና መንሰራፋት የክልሉን ህዝብ በመልካም አስተዳደር እጦት እንዲሰቃይ አድርጎታል ብሏል፡፡

የብልሹ አሰራር ስር መስደድ፤ የአመራር መምከን እና ወደ ገዥ መደብነት መቀየር ስር የሰደዱ የፓርቲው ችግር መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

በመሆኑም የችግሩ ባለቤት የአሶዴህፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ በመሆኑ በወሰደው እርምጃ 3 የኢሶህዴፓ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና 5 የማእከላዊ ኮሚቴ አመራሮች ከኮሚቴዎቹ እንዲታገዱ ተወስኗል፡፡

ከኢሶህዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ የተሰጠውን ድርጅታዊ ሙሉ መግለጫ ያንበቡ

የኢሶህዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አሁን በሀገራችን እና በኢትዮጵያ ሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ካለው የለውጥ ሂደት እና ጊዜው ከሚጠይቀው ድርጅታዊ ቁመና ጋር የሚሰምር ሁሉን አቀፍ ማስተካከያ ማድረግ ይቻል ዘንድ ከነሀሴ 4 እስከ ነሀሴ 11 ቀን 2010 ዓ.ም ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት ግምገማ ሲያካሂድ ቆይቶ ውጤታማ የሆኑ ውሳኔዎችን እና በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎችም ምቹ መደላድል የሚፈጥሩ ውይይቶችን በማድረግ በስኬት ተጠናቋል፡፡

ኢሶህዴፓ ባካሄደው በዚህ ታሪካዊ ግምገማ ወቅት ትኩረት ሰጥቶ ከገመገማቸው አንኳር ጉዳዮች ውስጥ ፓርቲው አሁን የሚገኝበትን እና በተራዛሚውም ሂደት ኢሶህዴፓ እያስተዳደረ ያለው የኢትዮጵያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ የተዳሰሰበት በሳል ግምገማ በዋነኝነት ይጠቀሳል፡

በዚህ ግምገማ ሂደትም የሶማሌ ክልል ህዝብን በተጨባጭ እየተገዳደሩ የሚገኙ እና ከልማት እና ከመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ረገድ እንቅፋት እየሆኑ ያሉ ተግዳሮቶችን ከነዝርዝር መገለጫቸው፣ ምንነታቸው እና ምንጫቸው ጭምር በመገምገም ተጠያቂነትን በሚያሰፍን መልኩ አቅጣጫ ለማስቀመጥ በሚያስችል ደረጃ በስፋት ታይቷል፡፡

በዚህም መሰረት በግምገማው ከታዩ ቁልፍ ችግሮች ውስጥ ቀጣዮቹ ጉዳዮች በዋናነት ይገኙበታል፡

 በክልሉ የሚታዩ እና በከፍተኛ ደረጃ የሚስተዋሉ የሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት

እንደነበሩ ማእከላዊ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡ እነዚህ የሰብአዊ እና የዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ከህይወት ማጥፋት እስከ አስገድዶ መድፈር እና ከአካል ማጉደል እስከ ማፈን- ማሰር ድረስ የዘለቁ እንደሆኑ በግምገማው ታይቷል፡፡

ከዚህም ባሸገር በጎሳዎች መካከል ጥላቻ እና ጥርጣሬን በመፍጠር ሁከት እና ብጥብጥ እንዲከሰት ከማድረግ አንጻር የአመራሩ እጅ እንዳለበት እና ለዚህም ተጠያቂ እንደሚሆን በማያሸማ መልኩ ግምገማው አሳይቷል፡፡

በሁከት እና ብጥብጡ ሰበብ ለጠፋው ህይወት፣ ለተዘረፈው ንብረት፣ ለወደመው የሀገር ሀብት እና ከቀዬው እና ንብረቱ ለተፈናቀለው ሰላማዊ ህዝብም የሚጠየቀው አመራሩ እንደሆነ በተካሄደው ግምገማ መተማመን ላይ ተደርሷል፡፡

ይህ የክልሉንም ሆነ የሀገራችንን ሀዝቦች እጅግ ያሳዘነ እኩይ ድርጊት በሀሰት የማሸበርያ ወሬዎች አማካይነት እንዲቀጣጠል እና የደረሰው ቀውስ ሁሉ እንዲፈጸም ለማድረግ ማህበራዊ ሚድያውን በመሳሪያነት ከመጠቀም ረገድ የአመራሩ የጥፋት ሚና እጅጉን ከፍ ያለ እነደነበር በግምገማው ተመልክቷል፡፡

በማእከላዊ ኮሚቴው ገምገማ ወቅት ተነስቶ የነበረው ሌላው ነጥብ ሄጎ በመባል የሚጠሩት እና በአመራሩ እንደዲሰለጥኑ ተደርጎ በጥፋት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩት ወጣቶች ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ በዚህ ረገድም ወጣቶቹን ከመመልመል አስከ ማሰልጠን- ከማሰልጠን- አፍረሽ ተልእኮ እስከመስጠት ባለው ሂደት እና በውጤቱም በተከተለው ጥፋት አመራሩ ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው ሲል ማእከላዊ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡

ከሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጋር በተያያዘ የታየው ሌላው ነጥብ የፍርድ ቤቶች ፍትሀዊነት ጥያቄ እንዱ ሲሆን ከዚህ ረገድም ፍጹም ኢ-ህገመንግስታዊ በሆነ መልኩ የፍርድ ቤቶች ስልጣን እና የመወሰን አቅም ወደ ግለሰቦች ተላልፎ በአመራር ፍቃድ ብቻ ፍርድ የመስጠት፣ ፍርድ የማራዘም እና የፍትህ ስርአቱን በማን አለብኝነት እንደፈለጉ የመዘወር ኢ-ዴሞክራስያዊ ወንጀል ይፈጸም እንደነበር በግምገማው ተረጋግጧል፡፡

በመላው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የመናገር፣ የመጻፍ፣ በነጻነት የማሰብ እና አመለካከትን በግልጽ የማንሸራሸረር መብት ፍጹም የተገደበ በመሆኑ ይህንን በሚያደርጉ እና ለማድረግም ጭምር በሚያስቡ ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ የሆኑ ጸረ- ዴሞክራሲ እርምጃዎች ይወሰዱ እንደነበር ማእከላዊ ኮሚቴው በግምገማው አረጋግጧል፡፡

እነዚህ የማሰር፣ የማፈን፣የማባረር እና የማሸማቀቅ እርምጃዎች ደግሞ በነዋሪው ላይ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ አመራሩ ላይም ጭምር ይፈጸሙ እንደነበር በግምገማው ተነስቷል፡፡

በዚህ እጅግ ውስብስብ የሆነ ስፋት እና ጥልቀት ባለው ስርአት አልባ አስተዳደር ውስጥ የመንግስት መዋቅሩ የሚያቅፋቸው ተቋማት እና አሰራሮች ሽባ እንዲሆኑ እና እንዳይሰሩ ተደርጎ ሁሉም የክልሉ መንግስታዊ እንቅስቃሴዎች በግለሰብ ይሁንታ እና አምባገነናዊ አገዛዝ ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

የኢትዮ ሶማሌ ክልል ህዘብ እንደብዙዎቹ እህት ወንድሞቹ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ሁሉ ዘመን የተሻገረ ባህላዊ የጎሳ አመረር ስርአት ያለው ህዝብ ቢሆንም ባለፉት ጥቂት አመታት ግን እነዚህን የህዝባችን አይነተኛ መገለጫ የሆኑ የጎሳ መሪዎችን ሳይቀር በመንግስት መዋቅር ውስጥ ባለ የአዛዥ ናዛዥነት ሚና በግለሰብ እስከመሾም የዘለቀ የተሳከረ ተግባር ይከወን እንደነበር ማእከላዊ ኮሚቴው በተጨባጭ ገምግሟል፡፡

በግምገማው የታየው ሌላው ጉዳይ የሀሰተኛ መረጃዎች እንደ አሸን የመፍላት እና የመንግስት መዋቅሩን የመቆጣጠር ነገር ሲሆን በዚህም መሰረት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች፣ የስራ ልምዶች፣ የቅጥር ሰነዶች… ወዘተ እጅጉን እንደተበራከቱ ተመልክቷል፡፡

ክልሉ በግለሰቦች ፍቃድ፣ ፍላጎት እና ይሁንታ ብቻ ለኪራይ ሰብሳቢነት ምቹ የሆኑ ግንኙነቶችን በመፍጠር በክልሉ ዙርያ መለስ ጣልቃ ገብነት እንዲንሰራፋ እና የክልሉ ህዝብ ህገ- መንግስቱ ከሰጠው ራስን በራስ የማስተዳደር ስልጣን ወጪ በእጅ አዙር በሌሎች እንዲተዳደር መደረጉን ማእከላዊ ኮሚቴው በስፋት ገምግሟል፡፡

 የከፋ ተብሎ ሊገለጽ የሚችል የኪራይ ሰብሳቢነት እና የሙስና መንሰራፋት እንዲሁም ለብዙ አስከፊ ችግሮች መሰረት የሆነ የብልሹ አሰራር ስር መስደድ የክልሉ ሀብት እና ንብረት እጅግ ከፍተኛ በሆነ መልኩ እንደባከነ እና የህዝቡን ችግሮች በመሰረታዊነት መቅረፍ የሚችል ሀብት እንደዋዛ እንደጠፋ ማእከላዊ ኮሚቴው በጥልቀት ገምግሟል፡፡

ይህ የመንግስትን ንብረት አለአግባብ የማባከን ጉደይ የመንግት ንብረትን ግለሰበች ተካፍለው እስከመውሰድ በጥሬ ሀቁም እስከመዝረፍ የዘለቀ እንደሆነ በስፋት ተገምግሟል፡፡ የመንግስት ገንዘብና ንብረት ለጎሳ መሪዎች እና ለአመራር ዘመድ አዝማዶች ይከፋፍል- ይታደል እንደነበረ እና በመንግስት የሚሰሩ ፕሮጄክቶች ያለምንም የጨረታ ሂደት ለአመራሮች፣ ለአመራር ዘመደች፣ ለጥቅም እና ሌብነት ሸሪኮች እንዲሁም ለጣልቃ ገብ ሹመኞች ይሰጥ እንደነበረ እና ይህም በኔትወርክ የመጠቃቀም ድር እና የአብሮ መዝረፍ ህገወጥ መስመር ሲከሄድ እንደቆየ ማእከላዊ ኮሚቴው በስፋት ገምግሟል፡፡

በክልሉ ተጠናቀዋል ተብለው የተመረቁ የተለያዩ ፕሮጄክቶች ፍጹም ያልተጠናቀቁ፣ አገልግሎት የማይሰጡ፣ ከጥራትም የተፋቱ…. ወዘተ እንደሆኑ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡ የሶማሌ ክልል ህዝብ ሀብት የሆነውን መሬት በህገወጥ መንገድ መውረር እና መከፋፈል እንዲሁም ለፈቀዱት ሁሉ በችሮታ መስጠት ባለፉት አመታት የታየ የሌብነት እና የሙስና አዙሪት ውጤት እንደሆነ በግምገማው ታይቷል፡፡ የክልሉ አመራር እና የአመራር ዘመድ አዝማድ የንግድ እንቅስቃሴውን በሞኖፖሊ በመቆጣጠር የክልሉን ህዝብ ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በዜሮ ከማባዛት ባሸገር የበይ ተመልካች በማድረግ ለችግሮች ሁሉ መሰረት የመጣል እኩይ ድርጊት በአመራሩ መፈጸሙን ማእከላዊ ኮሚቴው ማረጋገጥ ችሏል፡፡

ከዚሀም ባሻገር ክልሉን የጥቁር ገበያ ማእከል በማድረግ ለራሳቸው እና ለተባባሪዎቻቸው ጥቅም ሲሉ ኮንትሮባንድ ንግድን በማስፋፋት በክልሉ እና በህዝቡ ላይ አሳዛኝ ወንጀሎች እንደተፈጸሙ በኮሚቴው በጥልቀት ተገምግሟል፡፡ ከዚህም ሌላ የአመራሩ ዝቅጠት እና የሌብነት ችግር ስፋት የሴፍትኔት ብርን እስከመከፋፈል በሚዘልቅ ኪራይ ሰብሳቢነት እንደሚገለጽ ኮሚቴው ተመልክቷል፡፡

 የአመራር መምከን እና ወደ ገዥ መደብነት መቀየር አንዱ የፓርቲው ችግር እንደነበር ተግምግሟል፡፡ የመንግስትን ተቋማዊ አሰራር ሙሉ በሙሉ በማምከን ሁሉንም መንግስታዊ ስራዎቸ እና ሀላፊነቶች በግለሰብ በጎ ፍቃድ እና ትእዛዝ ስር የማዋል ህገወጥ ተግባር በክልሉ ተፈጽሟል፡፡ በዚህም መሰረት በመንግስታዊ ተቋማት ውስጥ የሚሾሙ ሀለፊዎች የራሳቸውን የዘመድ አዝማድ ኔትዎርክ በመዘርጋት መንግስታዊ የአመራር መምከን እንዲፈጠር ሆኗል፡፡

የተለያዩ ሹመቶች እና ምደባዎች በልምድ፣ በችሎታ፣ በክህሎት እና በብቃት ሳይሆን በቅርበት፣ በዝምድና እና በግለሰብ አመራር በጎ ፍቃድ ይከናወን እንደነበር እና ይህም የክልሉን የአመራር መስመር የመከነ በማድረግ መንግስታዊ መዋቅርን እንዳሽመደመደ ኮሚቴው በጥልቀት ገምግሟል፡፡

የመንግስት እና የድርጅት የሆኑ ተቋማት ወደ ግለሰብ እንዲዘዋወሩ ተደርጎ በክልሉ ህዝብ ላይ ትልቅ በደል ብቻ ሳይሆን ከባድ ወንጀልም እንደተፈጸመ ማእከላዊ ኮሚቴው በስፋት ተመልክቷል፡፡ ከዚህም ሌላ የመንግስትን ገንዘብ፣ ጊዜ እና ሀብት በመጠቀም አፍራሽ ሃይሎችን አደራጅቶ ክልሉን እና ሀገርን የማፈራረስ እና የማጥፋት ስራ ተሰርቷል፡፡

ከስነ ምግባር ጋር በተያያዘ በማእከላዊ ኮሚቴው ከተገመገሙ ጉዳዮች ውስጥ የሀሰት ሪፖርቶች ተቋማትን የማጥለቅለቅ አሳዛኝ ድርጊት አንዱ እና ዋነኛው ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር እንደ መንግስት እና እንደ ድርጅት መጠበቅ ያለባቸው ሚስጥሮች በተገቢው መንገድ ባለመጠበቃቸው እና የግል ጥቅምን ለማስከበር መዋላቸው ክልሉን፣ ድርጅቱን እና ህዝቡን ዋጋ እንዳስከፈሉ ተመልክቷል፡፡

ሌላው ከስነምግባር ጋር ተያይዞ የተነሳው ጉዳይ የመንግስትን የስራ ሰአት የሚመለከት ነው፡፡ ከከፍተኛ አመራሩ አንስቶ በመንግስት መዋቅር ውስጥ እስካለው የበታች ሰራተኛ ድረስ የመንግስትን የስራ ሰአት ያለማክበር ስር የሰደደ ችግር እንደነበረ ማእከላዊ ኮሚቴው በአጽንኦት ገምግሟል፡፡ ይህ የስነ ምግባር ችግር የብዙ ጥፋቶች እና ችግሮች መሰረታዊ ሰበብ መሆኑንም ኮሚቴው ተመልክቷል፡፡

ማእከላዊ ኮሚቴው እነዚህን አበይት የክልሉን አመራር ችግሮች ከገመገመ በኋላ የችግሮቹ ሁሉ ምንጭ የአመራሩ ራስ ወዳድነት፣ የፕሬዝዳንቱ አምባገነንነት፣ ጥቅመኝነት እና እንደ ድርጅት እና እንደ መንግስት ያሉ አሰራሮችን ለራስ እና ለተባባሪዎች በሚመች ኢ- ህገመንግስታዊ አቅጣጫ የመዘወር የአመራር ችግሮች የመጡ እንደሆኑ ገምግሟል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ ፍጹም ጓዳዊ ትግል ከተደረገበት ግልጽ፣ ነጻ እና ዲሞክራስያዊ ግምገማ<

LEAVE A REPLY