የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አብዲ መሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አብዲ መሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሃመድ ኡመር(አብዲ ኢሌ) አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢቲቪ ዘገበ። አቶ አብዲ መሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር የዋሉት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ አትላስ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ መሆኑ ተገልጿል። አቶ አብዲ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በመኖሪያ ቤታቸው መገኘቱንም ፖሊስ አስታውቋል።

አቶ አብዲ መሃመድ የታሰሩት በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣በጎሳና ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ግጭት በክልሉ በማስነሳትና በሌሎች ከባድ ወንጀሎች ተጠርጥረው መሆኑን ጠቅላይ አቃቤ ህግን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል። እርሳቸውን ጨምሮ ሌሎች በድርጊቱ የተሳተፉ ባለስልጣናትን በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑን ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።

  ሶማሌ ክልል ም/ቤት ትናንት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የአቶ አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ የሚታወስ ሲሆን

  1. የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግና ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲጀማል ቀሎንቢ
  2. የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ራህማ መሀሙድ
  3. የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብራሂም መሀድ
  4. የውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴቅ አብዱላሂ
  5. የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም መሀሙድ ሙባሪክ እና

6.የኢሶህዴፓ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ኡመር አብዲ መሆናቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY