በአገራችን ኢትዮጲያ በተደርገው ሰላማዊ መራራ ትግል ብዞዎች መሰአውት ሁነው የለውጥ ጅማሬ በግልጽ ባለፉት 5 ወራት ታይቷል። የህዝቡ ትግል በገዢው ፓርቲ (ወያኔ-ኢሕአዴግ) ውስጥ ሰርጎ ገብቶ ለውጡን የሚደግፉ አመራሮች ባሸናፊነት ወደ ፊት የመጡበት ግዜ ላይ እንገኝለን። አዲሱ የለውጥ አመራር የጀመራⶨው መልካም የለውጥ ጅምሮች ብዙሃኑን ኢትዮጲያን ተስፋ እንዲያድርበት አድርጓል።
በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ የሚመራው ቡድን በተወሰነ መልኩም ቢሆን በአገሪቱ በሚገኙ ክልሎች ተንቀሳቅሰው የህዝቡን ቀልብ የሚስቡ ተስፋ ሰጭ ንግግሮች በማድረግ ፣ በተግባር ደግሞ የፖለቲካ እስርኞችን መፍታት፣ የታገዱና በሽብርተኛ ስም ተፈርጀው ከአገር ውጪ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶችን መጋበዝና መሪዎቻቸውን በሌሉበት በሃስት የተፈርደባቸውን የሞትና የእስር ፍርድ ማንሳቱ፣ በሓይማኖት አባቶች መካከል የነበርውን ጸብ በተለይም የተከፋፍለችውን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን እንዲሁም የሙስሊም ሃይማኖት መሪዎችን ማቀራርቡ፣ ከጎርቤት ሀገሮች ጋ በተለይም ከኤርትራ ጋር የተደረገው የሰላማ ጅማሮ፣ የዶ/ር አብይ ቡድን ሰሜን አሜሪካ ጉዞና በዛ ያሉትን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ቀርቦ ማነጋግሩ፣በአገር ቤት እንዲሁም በውጭ የነበሩትን የህዝብ መገናኛ አንጻራዊ ነጻንት መስጠቱና እንዲሁም ከሙሁራኑና ባለሞያዎች ጋር የሚደርገው ውይይት መልካም ስራ የሚመስግኑበት ሲሆን ተስፋም ሰጪ ነው።
አዲሱ የለውጥ አመራር የተደቀነበትን ውስብስብ ፈተና ለመወጣት የሚያደርገው እርጋታና ብልህነት ያለው አመራር የሚደነቅ ሲሆን በተለየም ሙሉ ለሙሉ ስልጣኑን ያለቀቀው ነገር ግን ከፊት ለፊት ወንበር የተነሳው የቀድሞ አመራርና ተከታዮቹ የሚተክሉትን እሾሆችንና ወጥመዶችን በሰከነ መንግድ የማለፍ ተግዳሮት ይጠብቀዋል።
የተጀምሩት ለውጦች ለጊዜው የታመቀውን የህዝብ ቁጣ የማበርድ ችሎታ ቢኖርወም ህዝቡንና ኢትዮጵያን ወደአስተማማኝ ሰላማዊ ጉዞ የሚወሰደው መሰርታዊ ጉዳዮች ግን ገና የሚሰራባቸው ቁም ነገሮች ናቸው። ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም እንድሚሉት ያቄምው/ያደፈጠው ህዝብ የሚጠላውን መንግስት ለመጣል አግዞ እንደልማዱ ወደ ቤቱ የሚመልስ ሳይሆን የወደፊቱን ፍታሃዊ መንግስት መሰርት መጣል ይኖርበታል።
መሰረታዊ የሆኑ የፖለቲካ ውሳኔዎችና ስራዎች በተለይም የፍትህ አካሉን፤ፖሊስን፣ አቃቤ ህጉን፣ ፍርድ ቤቶች፣ ሰራዊቱን ከ ፖለቲክኞችና ሀብታሞች ተጽእኖ ስር የወጡ ህዝቡ ለተሰማማበት ህግ (ህገ-መንግስት) ብቻ የሚገዙ መሆን አለበት። ይህን ተከትሎ የምርጫው ኮሚሽን ገለልተኛ መሆን ፣ የምርጫው ሜዳ ለሁሉም አጫዋች የሚሆን፣ ሚዲያው በነጻነት የሚንቀሳቀስ እንዲሁም መስርታዊ የግለስቦች መብት መክበርና ይህን የመሳስሉትን መሰርታዊ ጉዳዮችን በህግ የሚግድበው ሁሉ ከህገመንገስቱ ተወግደው ባዲስ መለክ ተስተካክሎ መቀጠል አለበት። አገራችን ሰላምና መረጋጋት የሰፍነባት፣ አድሎ ያልበዛባት፣ ድሃ በሃብታም የምይንገላታበት፣ ዜጎች ለሁሉም ነገር እክሉ እድል ያለቸው መሆን አለበት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ እንደገለጹት ሌሎች የፖለቲክ ድርጅቶችን ያካተተ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም እቅድ የላቸውም። ራሳቸውና ቡድናቸውን የለውጥ ሽግግር መንግስት ነን ብለው ተናግርዋል።ከለሎች ተፎካክሪ ፖለቲካ ድርጅቶችን በማመከርና የህዝቡን ጥያቄ በሚመልስ መልክ የሽግግሩን መንግስት እንዲሚቀጥሉ ያሳወቁ ሲሆን መጪው ምርጫን እንጥብቃለን እንጂ ሌላ የመንግስት ለውጥ አይደርግም ብለዋል። የሚቀጥለውም ምርጫ ከሁለት አምት ባንሰ ግዜ ይካሄዳል ተብሏል ።
አሳሳቢውና መሰራታዊ ነገር ግን ለሰላማዊ ምርጫና ዘላቂ በህዝብ ፈቃድ የሚመስርት መንግስትና የዜጎችን መብት የሚያክበር አስተዳደር ለማቆም የሚጠቅሙ ወሳኝ ዲሞክራሳያዊ መሰርትና ምሰሶ ሳይቋቋሙ ምርጫው ቢድርስና ቢደርግ ተመልሶ ውሃ ቅጂ ውሃ መልሺ መሆኑ ነው። ይህም አሳዛኝና ተስፋ አስቆራጭ ይሆናል።
በሚቀጥሉት ሳምንታትና ወራቶች በአገራችን ከ 40 አምታት በላይ ለደረሱ ጥፋቶች ባደባባይ ተገልጾ በዳይ ይቀርታ ጠይቆ ተበዳይ ይቀር ብሎ፣ አገር አቀፍ የህዝቦች መግባባት ሳይፈጠርና የቂም ዘመን ሳይቋጭ ለምርጫ መሮጡ ሊያመጣ የሚችለው መዘዝ አስክፊ ነው። አዲስ ስልጣን የሚወጣው ሰውና ድርጅት ቂሙን ለመወጣት ሌላ ጥፋት ከማደርግ የሚያቆመው አይኖርም። ይህንንም በማወቅ አዲሱ አመራር መድርክ አዝጋጅቶ በዳይም የሰራውን ሃጢያት በግልጽ የሚናዘዝበትና ይቅርታ የሚጥይቅበት ወይም ወደ ፍትህ አካል የሚሄደበትን መስመር ማዝጋጅት ያስፈለጋል።
የእርቅና መግባባት ሳይፈጸም፤ መሰርታዊ የዲሞክራቲክ ምሰሶዎች ሳይተክሉ ወደ ምርጫ ከተኬደ፡ ተፎካክሪ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያራግቡት የምርጫ ፕሮፕጋንዳዎች አንዱን ባንዱ ላይ የሚያስነሳ፣ ያለፈን ቁስል የሚያመርቅዝ ሊሆን የሚችለና የዜሮ ስሌት ድምር ጨዋታ ይሆንብናል።
ከውጭ ሃገር ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ በህዝባቸው መካከል ገብተው ፣ ቢሮ ከፈተው፣ ራሳቸውን ለማስትዋውቅና ካድሬ ፈጥረው በመላ ኢትዮጲያ ለምንቀሳቀስና ፕሮግራማቸውን ለማስትዋወቅ፣ አባላት ለመፈጠር ግዜና የህግ መመቻቸት ያስፈልጋቸዋል። በሃገር ውስጥ ያሉትም የፖለቲካ ድርጅቶችም በነበርባቸው ተጽኖ ተመሳስይ እጣ ላይ ስለነበሩ እንሱም ግዜና የህግ ጥበቃ ያስፈልጋቸውል።
አሁን ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር ብዛት እጅግ ብዙ ስልሆነ ለህዝቡና ለአገራችን መልካም የወደፊት እድልን ለምፈጠር እንዚህ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደየፕሮግራማቸው ተመሳሳይነት ተዋህደው 3 ወይም 4 ትላልቅ ድርጅቶች በመሆንና በምርጫው አማራጭ ለመሆን ግዜ ያስፈልጋቸውል።
ከላይ የተጠቀሱት ነግሮች ሳይሟሉ የሚደርግ ምርጭ ምንም ማጭብርብር እንኳን ሳይደርገ ገዢው ድርጅት ኢሕአዴግ እንድሚያሽንፍ ጥርጥር የለውም። ይህ ታድያ እኩል የመወዳደሪያ ሜዳ አለተዘጋጀም ማለት ነው።
በእርግጥ ዶ/ር አብይና አዲሱ የለውጥ ሃይል ምንም እንኳ ለህዝቡና ለሃገራቸው መልካም ነገር ለማድርግ የሚወዱና የሚጥሩ ቢሆኑም ሊያደርሱን የሚችሉት ግማሽ መንግድ እንጂ ከዛ በላይ አይሆንም። የፈለገው ቢሆን አባል የሆኑብትና የሚመሩትን ድርጅት ስልጣኑን እንዲያጣ በፍጹም አይሰሩም። ሊኖር የሚችለውን ማንኛውን እድል ( ከ መግደል፣ ማሰር ፣ ማሳደደ ወይም መስረቅ ውጪ) ያለውን ተጠቅመው የሚታገሉለትን ፓርቲ ስልጣን ላይ እንዲቀጠል ማድርጋቸው አይቀርም። የሚቀጥለው ምርጫ በተወስነለት ግዜ እንዲፈጽም ከመግፋት ወደኋላ አይሉም። ይህም ለመስርቅ ያመቻቸዋል ማለት ሳይሆን የለውጡ መሪዎች ባላቸው ጊዜያዊ የህዝብ ፍቅርና ተፎካክሪዎቻቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ለምርጫው የመዘጋጃና የመተባበርያ ግዜ ስለሌላቸው ነው። ይህም ሁኔታ ለኢሕአዴግ ጠቃሚእድል ነው።
በሌላ በኩል ያለው አማራጭ ደግሞ ምርጫው ይራዝመ የሚለው ይሆናል። ይሄ ደግⶁ አሁን ያለውን ህግ መንግስት ህግ ይጻረራል። ነገር ግን መጪውን ምርጫ በትክክለኛ ሜዳ ለሁሉም ተፎካካሪ እኩል የመሆን እድል ይኖራል። ምርጫው ከተራዘመ አሁን ያለው መንግስት፡ መንግስት ሆኖ ከቀጠለ የህግ ድጋፍ ወይም ከለላ በህገመንግስቱ እይኖርወም። ያለው አማራጭ ከተፎካካሪዎች ጋር ጥምር መንግስት መመስርት ይሆናል ወይም ክሁሉም ተፎካክሪዎች የመንግስትን እውቅና ማግኝት ይኖርበታል። ሌላው አማራጭ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚወክሉበት ምክር ቤት የሚመሰርት ከፖለቲካ ወጭ ያሉ ሙሁራናን የአግር ሽማግሌዎች የሚመሩት መንግስት ይሆናል።
ምርጫውን ለማራዝም ከተወሰነ፡ ከላይ የተገለጹት አማራጭ ግዜያዊ 3 አይነት መንግስቶች የራሳቸው ጠቃሚና ጎጂ ባህሪያት አሉቸው። ያለው መንግስት እንዳለ እንዲቀጥል ከተፈለገ በሁሉም ዘንድ ፈቃድ ማግኝት ይኖርበታል። ሁሉም እሺ ይላል ብሎ መጠበቁ አስቸጋሪ ነው። ቢቀመጥም ያለው መንግስት ለራሱ የሚበጅ በምርጫ ሊያሸንፍ የሚያስችሉትን እድሎችን የመዘርጋት እድሉ ይኖረዋል። ጠቃሚ ጎኑ ደግሞ ልምድ ያለው የለውጥ መንግስት በጊዚያዊነት ይቀጥላል ማለት ነው።
ጊዚያዊ የጥምር መንግስት ቢቛቋም ፤ አብዛኛወተፎካክሪ የፖለቲካ ድርጅት የሚወከል ቢሆንም ፡ ካሉት የፖለቲካ ተፎካክሪ ፓርቲዎች ቁጥር ብዛት አዃያ ለስንቱ የመንግስት ሚኒስቴር መስርያ ቤት ለማዳረስ አስቸጋሪ ይሆናል። አብርው ሰርትው የምያውቁ፣ በጠላትነት ለዘመናት ሲተያዩ የነበሩ ድርጅቶችን አብራችሁ ስሩ ማለቱ ራሱ ችገር ሊሆንባቸው ይችላል። በሌላ በኩል ግን መንግስት ሁነው በ ጊዜዊነት ቢቆዩ፡ የተመቻቸ ፍትሃዊ የምርጫ ስራአትና ምርጫ ማስፈጽም ይችላሉ።
ጊዜያዊ የሽማግሌዎችና የሙሁራን መንግስት ማኖሩ (ከፖልቲካ ደርጅት ነጻ የሆኑ) የተሻለ ፍታሃዊ መንግስት ሊሆን የሚችል ሲሆን በተፎካክሪ ድርጅቶች ያለውን አለምግባባትና የስልጣን ፉክቻ የሚቀርፍ እድል ሲኖረው ነገር ግን በነርሱ ይሁኔታ ካላገኙ ጠንካራ እርምጃ ለመወስድ የሚቸግሩ ይሆናሉ።
ከላይ የተቀመጡትን ተግዳርቶች አዲሱ የለውጥ አመራር መንግስትና ተፎካክሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በቶሎ መከርው ዘዴ ቀይሰው ይህን መከራና ሰው ሰርሽ ችግር ሲግርፈው የከርመውን ወገናቸውን ከሌላ መከራሊያድኑት የሚገባ ነው። ይህን ችላ ካልነው ግን ችግሩ አፍጥጦ 2 አመት ሳይሞላ ይመጣብንና ሌላ ቀውስ ይሆናል።
አገራቸሁን እና ወገንቸሁን የምትወዱ የመንግስት የለውጡ አመራሮች ፡ እንዲሁም የተፎካክሪ ድርጅት መሪዎች በታሪክ አጋጣሚ በጃቹህ የገባውን እድል ለመልካም ነገር ለማውል የግል ውስጣዊ የስልጣን ፈተናዎችን በመተው ለወገናችሁና ለወደፊቱ ትውልድ የሰላምና ፍታሃዊ አገር ለማስርከብ ህዝቡን እንድትመሩት አደራ።
ህዝቡም በተለይም የዚህ ለውጥ ዋና ሞተር የሆነው ወጣቱ ትውልድ በመንግስትም በ ተፎካክሪ ድርጅት መሪዎች ላይ ለዚህ መልካም ጉዳይ ጠንክረው እንዲስሩና እንዲተባብሩ ተጽኖ ማድርግ ይኖርበታል።
መልካሙን ለማድርግ እግዚሓቤር ይርዳን።