የውጭ ሀገራት ህጋዊ የስራ ስምሪት በሚቀጥለው ወር እንደሚጀምር ተገለጸ

የውጭ ሀገራት ህጋዊ የስራ ስምሪት በሚቀጥለው ወር እንደሚጀምር ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው የውጭ ሀገራት  ህጋዊ የስራ ስምሪት በመስከረም ወር እንደሚጀመር ገልጿል። ለዓመታት ታግዶ የነበረው ህጋዊ የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት በመስከረም 2011 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ እንደሚጀመር ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

 የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር  የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ብርሀኑ አበራ ለኢቲቪ እንደተናገሩት፤ ስምሪቱ እስካሁን የዘገየው ስምሪት ከሚደረግባቸው ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ማድረግ አስፈላጊ ስለነበረ ነው ብለዋል። አዋጁ በ2008 ዓ.ም ቢፀድቅም እስከ አሁን ተግባራዊ ሳይሆን እንደቆየ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የዜጎችን የስራ ስምሪት አስመልክቶ ከሳኡዲ አረቢያ፣ ኳታርና ጆርዳን ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት በመደረጉ የስራ ስምሪቱ ከመስከረም ወር መጨረሻ ጀምሮ እንደሚጀመር ተገልጿል።

LEAVE A REPLY