/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ የተካሄደው የራያ ተወላጆች ሰልፍ የትግራይ ህዝብ አንድነትን ለማዳከም የታለመ መሆኑን የትግራይ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። የክልሉ መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ ኢቲቪ በር ላይ የተካሄደው የራያ ተወላጆች ሰልፍ የትግራይ ህዝብ አንድነትን ለማዳከም በሚፈልጉ ሀይሎች የተጠነሰሰ በማለት ገልፆታል። በመሆኑም የክልሉ መንግስት እንደማይቀበለው በመግለጫው አስታውቋል።
መግለጫው እንደሚያመለክተው “እንደዚህ አይነቱን እኩይ ተግባር” እንደሚታገለው ገልፆ፤ በድርጊቱ ተሳትፈዋል ያላቸውን አካላትም አስጠንቅቋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የራያ ተወላጆች የትግራይ ልዩ ሀይል ፖሊስ በራያ እና አላማጣ ህዝብ ላይ የሚፈፅመውን መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በማውገዝ ዛሬ ጠዋት በኢቲቪ በር ላይ በመሰባበሰብ ተቃውሞ አሰምተዋል።የመከላከያ ሰራዊትም ህገ መንግስታዊ እና ሀገራዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣም ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።
የራያ ህዝብ ከ27 አመት በፊት ወደትግራይ ሲካል የተቃወሙ የአካባቢው ተወላጆች ላይ የእስር የግድያና የማንገላታት ድርጊቶች ሲፈፀምበት ሊደርስለት የቻለ አካል ባለመኖሩ ስቃይና ሙከራውን ተሸክሞ ለመኖር እንደተገደደ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ሰልፉ ላይ በአደበበየ በርካታ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል።
~የራያ የማንነት ጥያቄ ይመለስ
~ ለ27 አመታት በራያ ህዝብ ላይ የተዘረጋው ቅኝ አገዛዝ ያብቃ
~ ራያ አማራ ነው
በራያ የሚደረገው ህገ-ወጥ የመሬት ወረራና ማፈናቀል ይቁም
~ በራያ የሚፈሰው ጥቁር ደም የኛም ነው
~ የትግራይን ህዝብ እንወዳለን ግን በፍፁም ትግሬ ልንሆን አንችልም!
የሚሉና መሰል መፎክሮች ተሰምተዋል።