የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ ሚስማር የተተከለበትን ዱላ ማንም ሰው እንዳይዝ ከለከለ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ ሚስማር የተተከለበትን ዱላ ማንም ሰው እንዳይዝ ከለከለ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ እንደተናገሩት በከተማዋ ሚስማር የተተከለበትን ዱላ የያዙ ግለሰቦችን እንደተመለከተና እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል። ከዚህ በሗላም ማንኛውም ሰው እንዲህ አይነት ዱላላ ሌሎች ስለት ነገሮችን እንዳይዝ አስጠቅቀዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለው እንደተናገሩት በህዝብ መገልገያ ንብረት፣ በመናፈሻዎች፣ በግንቦች፣ በአውቶብስ መጠበቂያዎችና በአጠቃላይ ባንዲራ ወይም አርማ መቀባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው ብለዋል።

 አዲስ አበባ የዲፕሎማት መቀመጫና ትልልቅ ጉባኤዎች የምታስተናግድ የአፍሪካ መዲና ለሆነችው ከተማ ደረጃዋን የጠበቀ ሰላምና ፀጥታ እንዲፈጠር ፖሊስ ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በአዲስ አበባ የተከሰተው ውጥረት ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ከኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ከተማው የገቡ ወጣቶች በፒያሳና አከባቢው ግጭት ፈጥረው ፖሊስ በትኗቸዋል።

 የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ከቄሮና አዲስ አበባ ወጣቶች ተወካዮች ጋር ውይይት እንዳደረጉና  አሁን የተፈጠረውን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ፈተው ወንድማማችነታቸውን እንዲያጠናክሩ መጠየቃቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት አስታውቋል።

LEAVE A REPLY