/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ትንሽ ቆዬና አማራ ኦሮሞ የሚለው ይቀራል፤ ሃረር ወለጋ ጅማ ተብሎ ይከፋፈላል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቡራዩ የተጠቁ ወገኖችን ከጎበኙ በሗላ ባሰሙት ንግግር ይፋ አደረጉ።
በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወደ ሀገር ቤት መመለሰ ጋር በተያያዘ በቡራዩ በተፈፀመው አሰቃቂ እልቂት እንግልትና አስገድዶ መድፈር ምክንያት የጥቃት ሰለባ የሆኑትን ኢትዮጵያዊያን ለመጎብኘት ዛሬ ወደተጠሉበት አካባቢ ለጉብኝት ያቀኑት ዶ/ር አብይ አህመድ የተሠማቸውን ጥልቅ ሃዘን ከገለጹ በኋላ በሶማሌ ክልል የተደረገው የእርስ በርስ ግጭት መከራ ያልተሳካላቸው ሰወቸ የፈጸሙት ድርጊት መሆኑን ጠቁመው ደም በማፍሰስ የሚረኩ ካሉ ይሄው ፈሷል ይጠጡት ሲሉ በቁጭት ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ለተቃዋሚ ድርጅቶች ባስተላለፉት መልእክትም የአውራ ጎዳና ፖለቲካ እንዲያቆሙና የማይቆጣጠሩትን ሰልፍ እንዲያይጠሩ ማሳሰቢያ ከመስጠታቸውም በተጨማሪ በአዳራሽ መነጋገርን እንደአማራጭ እንዲወስዱ አሳስበዋል።
በቡራዩ ጥቃት ሃዘናቸው ከተጠቂዎች በላይ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የለውጡ ሂደት የሚቆም እንዳልሆነ እና ወጣቶች የተራ ፖለቲካ መጠቀሚያ እንዳይሆኑ በወጣቶች ትግል የመጣውን ለውጥ እንዲጠብቁና በማያውቁት አጀንዳ እንዳይነዱ ጠቁመዋል።
“…ትንሽ ቆዬና አማራ ኦሮሞ የሚለው ይቀራል። ሃረር ወለጋ ጅማ ተብሎ ይከፋፈላል…” ያሉት ዶ/ር አብይ በማከልመ “… ወሎ፣ ጎጃም፣ ጎንደር እያለ ይከፋፈላል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቡራዩ የተጠቁ ወገኖችን ከጎበኙ በሗላ ባሰሙት ንግግር ይፋ አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከዚህ በፊት በወልቃይት እና በራያ ጉዳይ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ ባሰሙት ንግግር የወሰን አከላልን በሚመለከት የሚያጠና ኮሚሽን ተቋቁሞ በመስራት ላይ መሆኑን ጠቁመው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።