ኦሕዴድ ስሙንና አርማውን በቀየረበት ዘጠነኛው ጠቅላላ ጉባኤ አንጻራዊ ለውጥ እና የስልጣን ሹም ሸርተት ማድረጉን ይፋ አደረጉ።
በጅማ ከተማ ባካሄደው ድርጅታዊ ጉባኤ የድርጅቱን ስያሜው መቀየሩንና አዲሱ ስያሜ “ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” (ኦዴፓ) እንዲሆን ውሳኔ ማስተላለፉ ታውቋል። የፓርቲው መዝሙርን ጨምሮ በተለይ ሲጠቀሙበት የነበረውን የድርጅቱን አርማ መቀየሩን በይፋ አሳውቋል።
ፓርቲው ነባር አመራሮች በመባል የሚታወቁትን አባላቶችን በክብር አሰናብቶ በምትካቸው ውጤት ሊያመጡ እና ከወቅቱ ጋር ሊራመዱ የሚችሉ ምሁራኖችን ያካተተ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቶችን መርጧል። ከፓርቲው የተሰናበቱት ነበርና በድርጅቱ ምስረታ ጀምሮ በከፍተኛ ስልጣን ላይ የነበሩት አመራሮች የሚከተሉት ናቸው፦
-አባዱላ ገመዳ
-ጌታቸው በዳኔ
-ኩማ ደመቅሳ
-ግርማ ብሩ
-ድሪባ ኩማ
-እሸቱ ደሴ
-ተፈሪ ጥያሩ
-ሽፈራው ጃርሶ
-ሱሌይማን ደደፎ
-አበራ ሀይሉ
-ኢተፋ ቶላ
-ዳኛቸው ሽፈራው
-ጊፍቲ አባሲያ
-ደግፌ ቡላ።