-
ለአሁኑ ለውጥ በር የከፈተው የወጣቶች አመፅ በተቀጣጠለበት ወቅት የግብፅ ሚዲያዎች ስራ ነገሬ ብለው ጉዳዩን ሠፊ ሽፋን ሰጥተው እግር ከግር ይዘግቡና ይተነትኑ ነበር። መዘገብ ብቻ ሣይሆን ከኛ ከባለቤቶቹ በላይ ውጤቱን በከፍተኛ ጉጉት ነበር የሚጠብቁት ።‘አመፁ ውጤት አምጥቶ የትግራይ የበላይነት ካከተመ አባወራ ጎሣ ማን ይሆናል? ‘ የሚለው እና ማን ቢሆን ይበጀናል የሚለው ጉዳይ አንኳር ነጥባቸው ነበር። በወቅቱም እንደ አል ቃድ አል ረቢ ያሉት ትላልቅ ግብፃዊ የቲቪ ጣቢያዎች ግጭቱ ለአገራቸው ትልቅ ብስራት እንደሆነ ሲያወጉ ከርመዋል።አመፁ በዋናነት የተቀጣጠለው በሀገሪቱ ሁለት ታላላቅ ጎሣዎች (አማራና ኦሮሞ) መሆኑ ደግሞ ከፍተኛ ተስፋ እንዲጥሉበት ና ያላቸውንም የሌላቸውንም ዐቅም አሠባስበው ቢሟሟቱበት አዋጭ እንደሆነ ታውቋቸዋል ። የታላቁን ግድብ ግንባታ ማስቆም የሚቻልበት ህጋዊ መሠረት እንደሌላቸው ስለተገነዘቡ ያላቸው አማራጭ ግንባታውን በማስተጓጎል እስከወዲያኛው ቁሞ ቀር ፕሮጄክት አድርጎ ማስቀረት ነው።ለዚህ ተፈፃሚነትም፤ የተለያዩ የግብፅ ፖለቲካዊ ተቋማትና ሚዲያዎች ከማንኛውም የኢትዮጵያ ጠላት ጋር እንደሚያብሩ ያለምንም ዲፕሎማሲያዊ ይሉኝታ ፤ ሲገልፁ ሠንብተዋል ።ለምሣሌ ፦ የአል ኻራም ፖለቲካዊ ስትራቴጂዎች ጥናት ተቋም መሪ የሆኑት ዶ/ር አሚነ ጦይል ፥ ማንኛውንም የኢትይጵያ መንግስት ተፃራሪ ኃይል ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል የተጠና ስልት ተግባራዊ ለማድረግ መነሣታቸውን በመግለፅ የአገራቸው መንግስትም ማንኛውንም የኢትይጵያ ጠላት እንዲጠቀም በወቅቱ በአደባባይ ጥሪ አቅርበዋል። አክለውም የትኛውንም ተገፋሁ ያለ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ እና በአገሪቱ ውስጥ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ አመፅ በገንዘብ መደገፍ የዚሁ የተጠና ስልትዋነኛ አካል መሆኑን አሳስበዋል።ብዙም ሣይቆይ የኦነግ አመራር ” ‘የተገፋ..ጠላት እና ገንዘብ‘ ” ስትሉ ሠማሁ ልበል ብሎ እቀያቸው ብቅ አለ። ከፍ ያለ የወዳጅ አቀባበል ተደርጎላቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሆድ የሆዳቸውን ሲዶልቱ ከረሙ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ገመዳ ሲቲ ደግሞ በሠአድ አል በልድ ቲቪ ጣቢያ በስልክ ድምፁን ልኮ ‘የአል ሲሲ መንግስት እቅፍ ድግፍ አርጎ የኢትዮጵያ አቻው ካደረጋቸው የተጀመረውን ግድብ መገተር ብቻ ሣይሆን ግብፅ የቀፈፋትን የትኛውንም የልማት ሥራ ንክች አናረግም አይነት ቃል ገባ። ይህና ተመሣሣይ የዕኩይ ፖለቲካ ቅባቶች በግብፅና አባሪዎቿ ሲቀመሙ አገራችን ለመስማትና ለማየት የአመፅጩኸት አደንቁሯት፥ የቃጠሎ ጭስ ጋርዷት ነበር ።ኢቢሲ በወቅቱ በምሥልና ድምፅ አስደግፎ ቢዘግበውም፤ እንደቧልተኛው እረኛ ‘ቀበሮመጣብኝ‘ ጬኸት በቅጥፈቱ ተሠልችቶ ነበርና ዜና አንባቢውን ከቀረፃ ቡድን ውጭ የሠማው ያለ አይመስልም። አመፁ በጎሪጥ እንዲተያዩ የተደረጉ ጎሳዎችን አጎዳኝቶ፥ ሁለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆችን አልፎ፥ ብዙ መስዋዕትነት አስከፍሎ፥ ውጤታማነቱ አይቀሬ መሆኑ እየታወቀ ሲመጣ የነዶክተር አሚና የተጠና ስልት አካል እንደሁ እንጃ፤ የኦሮሞ መብት ተቆርቋሪዎችና ድርጅቶች በዚህ የድል ዋዜማና በማግስቱ ብዛታቸው ጨምሮ፥ ምሬታቸው አይሎ፥ ልብወለዶቻቸው ዳብረው፥ በሽብር መኣዛ ታውደው በየ ኤሌክትሮኒክ መስታወቱ ብቅ እያሉ መፎግላት ጀመሩ።በአማራው በኩልም የተናፈቀው ነፃነት ወጋገኑ መታየት ሲጀምር በሌላ ወገን የተነሣውን የፅንፈኝነት ግርሻ ሚዛን ለማስጠበቅ ይጠቅማል ተብሎ የተመሠረተውና በፍጥነት እየጎለበተ የመጣው የአማራ ብሔርተኝነት አራማጅ ቡድን አብንም በቅርብ ርቀት እየታየ ላለው ለውጥ እንከን የሆነውን ፤ሁሉን ‘ ኬኛ‘ ባይ ቡድን ያስታግሣል ተብሎ ሲጠበቅ ጭራሹኑ ግብፅ የምትፀየፈውን የአንድነት ስሜት መናከስ ጀመረ። ኦነግም ከረም ብሎ ይኽንን ለሡ በፕሮግራም ደረጃ እንቅፋት የሆነን ድርጅት ‘ስትራቴጂካዊ አጋሬ ለማድረግ እየመከርኩ ነው‘ መሣይ መግለጫ ለቀቀ።የአማራ አቻው አብንም ‘እኔ በወከልኩት ጎሣ ላይ የእልቂት ፕሮፓጋንዳ የሚረጬትን አክቲቪስቶችህን መጀመሪያ አስታግስ‘ ብሎ ኩምያደርገዋል ብለን ስንጠብቅ በእሺታ በሚተረጎም ዝምታ አለፈው። የድርጂቱ የሶሻልሚዲያ አፈቀላጤዎችም እነዚህን በይፋ አማራ ላይ ደምደም የሚከረፋ ዛቻ የሚያነበንቡ ኃይሎች ትቶ ዕድል ተሠጥቶት የማያውቀውን በመቻቻልና በመከባበር ላይ የተመሠረተ አንድነት መናደፍ ቀጠሉ። ይኽ እየሆነ ያለው እንግዲህ አመፁን አዳምጠው ራሳቸውንና ድርጅታቸውን ለማደስ የተነሡ ቡድኖች ለለውጥ በሚተጉበትና ይኽን ተከትሎም አመፁ በረገበበት ወቅት መሆኑ ሌላ ህቡዕ ተልዕኮ እንዳለ የሚያሣብቅ ነው።ወደ ምስር ስንዞር ስትራቴጂዋ ቢያንስ ሁለት አማራጮች ያሉት ይመስላል1, ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አመፅ ደምህ ደሜ ነው በተባባሉ ወጣቶች መስዋዕትነት ቀጥተኛ ዉጤት ቢያመጣና መንግስት በኃይል ቢገለበጥ የተጠናው ስልት ባለቤት ግብፅ በኢትዮጵያ ጎረቤቶች ላይ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ተጠቅማ በገንዘብና በቁስ በማገዝ የተማመነችበትን የተገፋ ቡድን ዙፋን ላይ አፈናጥጣ ግድቡ በቁፋሮየ ተገኘ ከተማ መስሎ እንዲቀር ማድረግ፤ወይንም ደግሞ:-2, የመንግስት ግብዐተ መሬት ከተፈፀመ በኋላ የሁለቱን አውራ ጎሣዎች እና ሌሎችንም ከፋፍሎ በማቧደን መሪዎቻቸውን በሪሞት በመዘወር የማያባራ ግጭት ውስጥ ከቶ ግድቡን መጨረስ ቀርቶ ማሠብ የማይቻልበት ደረጃ ማድረስ ነው። አመፁ ግን ከሁለቱም ተጠባቂ ውጤቶች ውጭ በሆነ መልኩ ረገበ።የኢህአዴግ መንግስት ራሱን አክሞ የሥልጣን ፖስቴ ሲመታ ፥ የዘሀሩን ወንበር የኢትይጵያዊ አንድነት ሽታ ያላቸው ሰዎችያዙ። ይኽ በራሱ ለምስር ግብዳ ዕንቅርት ሆኖ ሣለ የአዲሡ አመራር ብሔራዊ እርቅን ማወጅ ደግሞ ተደራቢ ጆሮደግፍሆነ። ነቄው የለውጥ ኃይልም ‘ያዋከቡት ነገር‘ እየተዘፈነበት ብሔራዊ እርቁን ከማካለብ በተጨማሪ ባልተጠበቀ ፍጥነት ከኤርትራ ጋር ዕርቅ ማውረዱና ይኽን ተከትሎም የምስራቅ አፍሪካን ቀጠና የሚያረጋጉ ርምጃዎች መወሠዳቸው፤ ግብፅ ነፃ መሬት ና ነፃ የኢትይጵያ ጠላት ለማግኘት የሚቸግራት መሠለ። ‘ለውጡን የግድ እኛ ካላመጣነው አንልም‘ የሚለውን ሃሣብ የተጋሩ የመሠሉ እና በሠላማዊ መንገድ እንወዳደራለን ያሉኃይሎችም አውፍ ተባብለናል ብለው ዕርቁንና ለውጡን ደገፉ ወይም የደገፉ አስመሠሉ።ነገር ግን ግድቡን ለማስተጓጎል ሌላ አጋር እስክታገኝ እንቅልፍ ባይኗ ላይዞር የወሠነችው አገር በስልጣን ሽግሽጉ የተከፉ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ከስልጣን ያልተወረወሩትን የህወሀት ባለሥልጣኖች መቃኘቷ የማይቀር ነው። እነዚህ አካላት ደግሞ ከስልጣን ማጣት በተጨማሪ በቀላሉ በይቅርታ ይነፃል ብለው የማያምኑት ዕድፍ ስላለባቸው ለማባበል ቀላል ያደርጋቸዋል። በተጨማሪም ሙሉ በሙሉ ስላልተነቀሉ፤ መግቢያ መውጫውን በሚያውቁት የተንኮል ፖለቲካ ሌሎች ኃይሎችንም በማስተባበር ትልቅ ሙያእንደሚፈፅሙ ስለሚታመን እነዚህን ሠዎች በፈለጉት አንቀፅ ለመደራደር ግብፅ አታመነታም።ለዚህም ይመስላል ጠ/ሚር ዐብይ በሲመታቸው ማግስት ወደ ካይሮ በረው ለአል ሲሲ ህዝብና መንግስት‘እንዳትሠጉ ግድባችን ወደናንተ ከሚደርሰው ውሃ አንድ ሲሲ እንኳን አያስቀርም ‘ ዓይነት መግለጫ በመሀላ አስደግፈው የሠጡት።ግብፆችም ዲፕሎማሲያዊ ጭብጨባቸውን ለመሪው ባይነፍጓቸውም፤ አንድም ይኼንኑ ነገር መለስና ኃ/ማርያምም በተደጋጋሚ አረጋግጠውላቸው ስለነበረ፤ አንድም ደግሞ የአባይ ፖለቲካ የውሃ ብቻ ስላልሆነ አርፈው ይቀመጣሉ ብሎ ማመን የዋኅነት ነው። እናም የቅድመ ዐብይ ነውጥ በቀጥታ መንግስት ባለመገልበጡ ዕቅዷን “በሠላማዊ” መንገድ ለመፎካከር ወደ ገቡት ተቃዋሚዎች ስታዞር ለውጥኗ የሚያመቿት ጎሠኛ ፖለቲከኞች መሆናቸውን ጠንቅቃ አጥንታለች።ሠሞኑን የሚታየው ብሔርተኛ ድርጅቶች በአንድነት ቡድኖች ላይ የሚሠነዝሩት ግልፅ የፕሮፓጋንዳና የኃይል ሸፍጥ (ሣቦቴጅ)፤ ሌሎች በአካባቢያችን ላይ ዓለም አቀፍ የኃይል የበላይነት አጀንዳካላቸው እንደ ሩሲያና ቻይና የመሣሠሉ አገሮች በተጨማሪና ምናልባትም በዋናነት የግብፅ እኩይ ለጋስነት አለበት ብሎ ማመን የሚናቅ መላምት አይደለም።በተለይ ደግሞ ሦስቱ ብሔር ተኮር ድርጅቶች (ህወሀት፣ አብን እና ኦነግ) የስትራቴጂካዊ ወዳጅነት ፍንጭ እያሣዩ ባሉበት በዚህ ሠሞን ተደጋጋሚ ዘግናኝሁከቶች መፈጠራቸውና ሁከቱ ብሔር ተኮር ከመሆኑ አንፃር ርስ በራስ መወቃቀስ ወይም መመካከር ሲገባቸው ጉዳዩን ለፖለቲካ ስልጣን በሚያሠጋቸው ህብረ ብሔራዊ ድርጅት ላይ ማላከክ መፈለጋቸው፤ እንዲሁም ለለውጥ እየባዘነ ካለው መንግስት እናከሚታገሉለት ህዝብ ጋር ሆነው መፍትሔ መሻት ሲገባቸው በለውጡ የገበያ ግርግር የመንግስት ሥልጣን የጨበጡ አጋሮቻቸውን በመጠቀም ወደዛቻና ወከባ ስልት ማዘንበላቸው ጥርጣሬውን ይበልጥ ያገዝፈዋል።ምናልባት እነዚህ ድርጅቶች በለውጥ ኃይሉና በህብረብሔራዊ ድርጅቶች ላይ ለአገር ና ለትግላቸው ያዩት ሣንካ ካለ እስከ ቀበሌ ወርደው ህዝባቸውን ማንቃት እና ማግባባት ላይ ማተኮር ሲገባቸው ከቀበሌ ይልቅ ኢሊሌና መቀሌ ተሠትረው የመግለጫ ፖለቲካ ላይ መጠመዳቸው ለህዝባቸው ሣይሆን ለአሰሪያቸው የሚተጉ አስመስሏቸዋል። ይኽን በዚህ ትተን ከለውጡ በኋላ የታዩ ወሣኝ ክስተቶችን በነጥብ እንይና ነጥቦቹን አንባቢ ያገናኛቸው ።=) በለውጡ ሠሞን እውነተኛ ተቆሮቋሪ አጥቶ የከረመውን የአማራ ህዝብ አደራጃለሁ የሚል አሣማኝ ነጥብ የያዘ ድርጅት ራሱን አብን ( የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ) በማለት ተቋቁሞ በአጭር ጊዜ በርካታ ደጋፊዎችን ማሠባሠብ ቻለ።– ከሩሲያ የውጭ ደህንነት ድርጅት አርማ ጋር ብዙም ልዩነት የሌለው አርማ አሳተመ ።– በፈጣን እድገቱ ሳይዘናጋ ህዝብ ለማደራጀት አስተማማኝ ስልት ነድፎ ይንቀሳቀሳል ተብሎ ሲጠበቅ ፤ ከመቶ አመት በፊት ልጅ እያሱ የተወገዱበት አይነት የፎቶሾፕና የአብዮቱ ዘመን አይነት ሥም የማጠልሸትና የእኔ አውቅልሀለሁ ፖለቲካ ማራመድ ተያያዘ። በዚህም የሁሉንም አማራ ቀልብ መግዛት ተሥኖት በመጣበት ፍጥነት እንዳይጓዝ ተገደደ።በይቅርታ ያለፈውን ትተናል ያሉ አክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኝነት አቀንቃኝ እንደ ነበሩ የሚታወቁ እና አንድነት ጠል የነበሩ ሠዎች በአዲስ አበባ ከንቲባነት፣ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነርነት፣ በመከላከያ ና ደህንነት መዋቅር ተሠገሠጉ።=) በጠ/ሚሩ የድጋፍ ሠልፍ ቦንብ ተወረወረ። ሠዎች ሞቱ፣ ቆሠሉ።– ፖሊስ ‘በውጭ አሸባሪዎች የገንዘብ ድጋፍ የተፈፀመ መሆኑን ደርሼበታለሁ‘ በማለት “ዉጭ“የምትለውን ቃል ሣያፍታታ መግለጫ ሠጠ።– በቅርቡ ደግሞ ‘ጠቅላዩን ገድለው ኦነግን ለመሾም ያለሙ ግለሠቦች ያቀናበሩት ነው‘ በማለት አቃቤህግ ክስ መሥርቻለሁ አለ።=) የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሞተው ተያንን የከረፋ የመነካከስ ፖለቲካ መራጨት የጀመሩት ግን ገና የናፈቃቸውን ወገን–ዘመድ የሣሙበትን ከንፈር ሳይጠርጉ ነበር ።=) ሻሸመኔ ላይ አባ ቄሮ ነኝ በሚለው የኦሮሞ መብት ተሟጋች አቀባበል ላይ ፤ ጃዋር የሠው ይሁን የድርጅትሥም የሚያውቁ በማይመሥሉ ተንቀሳቃሽ ሙታን የአንድ ወጣት ህይወት አገራችን ላይባልተለመደ ዘግናኝ ሁኔታ ተቀጠፈ።– ፖሊስ ጥርሱን እየፋቀ በመመልከት ከዘግናኙ ግድያ የበለጠ ዘግናኝ ትዕይንት አሳየን ። በሱ ምክንያት ነፍስየጠፋበት ጃዋርም የሟቹን ዘር እስኪያጣራ ድረስ እንደሆን እንጃ ዘግይቶ ከድርጊቱ ዘግናኝነት አንፃር የተለሣለሠ መግለጫ ሠጠ።=) ህወሃት ‘የለውጡ አካሄድ ስላላማረኝ ከዚህ በኋላ ከማንኛውም የሚመስለኝ ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት ተገድጃለሁ‘ በማለት ያስከፋውን ነገር ሣያፍታታ መረር ያለ መግለጫ ሠጠ።=) የኦነጉ መሪ ዳውድ ኢብሳም ከወያኔ ጋር ችግር የለብኝም አይነት መግለጫ ከወደ አስመራ ላከ ተባለ።– ከየትኛውም ድርጅት በበለጠ ግፍ የሠራበትን ኦነግን ህወሀት “የእናቴ ልጅ ” ብሎ አገላብጦ ስሞ በፌሽታ ተቀበለ ።=) ከጥቂት ወራት በፊት በአሸባሪነት ይኮንኑት የነበሩት እንደ ዳንኤል ብርሃኔ ያሉት የህወሃት ባለ አምሥት ኮከብ ካድሬዎች ‘…ኦነግ ዝም ብሎ ድርጅት አይደለም የኦሮሞ ህዝብ የነፃነት አርማ ነው ‘ ሲሉ መሠከሩለት ።=) ዘግናኝ ብሔር ተኮር ጭፍጨፋዎች በየቦታው መሠማት ጀመሩ ።– ፖሊስ የግጭት አፈታቱ ዘገምተኛነት ሳያንስ እንደ ገለልተኛ የፍትህ ተቋም ሳይሆን እንደ ወገንተኛ የፖለቲካ ተቋም በሌሎች (በተለይም በግ 7) ማሣበብና ጭፍጨፋዎቹን የተቃወሙትን ወደማስፈራራት ያዘነበሉ መግለጫዎች መሥጠት ያዘ።5=) የፍትህ አካላት ‘ ከየት?’ የሚለውን ባይገልፁም በተለያዩ ቦታዎች ከተፈፀሙት አሰቃቂ ግድያዎች ፥ ዘረፋዎችና መፈናቀሎችጋ በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች እጅ በርከት ያሉ ገንዘቦች አግኝቻለሁ፤ የድርጊቱዋና ማበረታቻም ገንዘብና የፖለቲካ ግብ መሆኑን ጠርጥሬአለሁ አለ።(የአሚና ጦይል የተጠና ስልት ዋና ማስፈፀሚያ ገንዘብ መሆኑን ያስታውሷል)=) ኦነግ አብንን ስትራቴጂካዊ አጋር ለማድረግ እያሠብኩበት ነው የሚል ሹክሹክታ አሠማ ።=) በህወሀት ደማቅ ቀናት ዋና የልማት አጋር የነበረችውና ከድርጅቱ ቱባ ባለሥልጣናት ጋር ኩባንዮቿ አግባብ ባለውም በሌለውም ጥቅም እንደተሣሠሩ የምትታማው ቻይና ለጠ/ሚር አብይ ከደረጃ በታች የሆነ አቀባበል አደረገች።=) በመስከረም 9 2011፤ በአለም አቀፍ የኃይል ሚዛን ከሩስያ ና ቻይና ጋር አይንና ናጫ የሆነችው አሜሪካበጠቅላዩ ላይ መፈንቅል ሳይታሠብ አይቀርም የሚል ጥቆማ ሠጥታ ትኩረት እንዲያገኝም ኤምባሴየን ሙሉቀን ዘግቻለሁ አለች።=) ጠ/ሚሩ በኦህዴድ (ኦዴፓ) ጠቅላላ ጉባዔ መክፈቻ ላይ የኦሮሞ አክቲቪስቶች በደፈናው ‘ጠላቶቻችን‘ ካሉት ኃይል ጋር ለውጡን ለመቀልበስ ሸፍጥ መጀመራቸውን እንደደረሱበት ገልፀው ጫን ያለ ማስጠንቀቅያ ሠጡ ።=) የትግራይ አክቲቪስቶች በለውጡ የተከፋውን የህወሀት ቡድን የፑቲን ቡድን በሚል ተቀፅላ ማንሞካሸት ጀመሩ።=) ከሌሎቹ የኢህአዲግ እህት ድርጅቶች በተለየ ህወሀት ጠቅላላ ጉባኤዉ መክፈቻ ላይ የቻይና ተወካዮችን ጋበዞ አስተናገደ ።=) ከሠሞኑ ደግሞ የኢትዮጵያን ስትራቴጂክ ፋይዳ በተመለከተ ለአሜሪካ ምክር ቤት በቀረበ ጥናት ፤ አጥኚዋቻይናና ሩሲያ በአካባቢዉ ተፅዕኗቸውን ማሣረፍ መጀመራቸውን አትተው፤ አሜሪካ የአብይን መንግስት የጀመረውንተሥፋ ሠጪ ለውጥ በቀጥታ ካልደገፈች በአከባቢው ያላትን ጥቅም ለማሥከበር እንደሚሣናት በዝርዝር አስረድተዋል።በመጨረሻምጠቅላይ አቃቤ ህግ ታዬ ደንደአ የሠኔ 16 ቱ የሽብር ጥቃት ና መሪውን የመግደል ሙከራ ” በጣም ውስብስብ ነው። የተለያዩ አካላት ለተለያዩ አላማዎች እንደተሣተፉበት የእስካሁኑ ምርመራ ያሣያል። ” ሲሉ በፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል