አርበኛው አያቴ
ወራሪን ሲፋለም በዱር በገደሉ
ጃንሆይ ፋሽስትን ላውሮጳ ሊከሱ ሂደው ነበር አሉ
ከዚያ ሲመለሱ
ለድል አጥቢያ ጄግኖች ሹመት ሲለግሱ
ለባንዳ ላጎብዳጅ ክብር ሲያላብሱ
አያቴን ረሱ ።
አባቴና ደርጉ
ምክንያት አይሆን ምክንያት ምክንያት እያረጉ
ሲጋደሉ ኑረው
በመሀል ከተማ በየጥጋ ጥጉ
አልበቃ ብሏቼው,
ወደጠረፍ ዘምተው ሲዋጉ— ሲያዋጉ
በ”ቼ” ና “ሼ” ሰበብ እየተቧቀሱ
በምናምኒት “ዝም” እየተጫረሱ,
እኔን በጄርባዋ ያዘለች እናቴን ደም እንባ አስለቀሱ ።”
አንዱ አንዱን ሊያጠፋ — ርስበርስ ሊጣፉ
እንደተሰለፉ እንደተጣደፉ ”
ሲባክኑ አለፉ ።
የኔው ዘመን ደሞ
ዘመነ ራዕዩ ዘመነ ህዳሴ
በእኔነቴ ምክንያት በማንነት ውርሴ
በውልደቴ ሰበብ ተከፍቶልኝ ዶሴ
ይካስሰኝ ይዟል
ያራክሰኝ ይዟል
ያናክሰኝ ይዟል — ራሴን ከራሴ ።
—
—
—
— ልጄስ? ??