አዲስ አበባ ቤተመንግሥት አካባቢ ውጥረት ነግሷል

አዲስ አበባ ቤተመንግሥት አካባቢ ውጥረት ነግሷል

ADDIS ABABA - NOVEMBER 1: Emperor of Ethiopia, Haile Selassie, in front of the Jubilee Palace in Addis Ababa, Ethiopia on THE TWENTIETH CENTURY. Episode called, "Ethiopia: The Lion and the Cross." Image dated November 1962. (Photo by CBS via Getty Images)

/Ethiopia Nege News/:- ዛሬ ጠዋት በቤተመንግሥት አካባቢ ውጥረት እንደነበርና በአካባቢው የሚገኙ መስሪያ ቤቶች እንዲዘጉና ሰራተኞች ከቢሯቸው እንዲወጡ መገደዳቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል።

ዛሬ አራት ኪሎ በሚገኘው የምኒልክ ቤተመንግስት አካባቢ የሚያልፉ መኪናዎች እና መንገደኞች በጥብቅ ሲፈተሹ መዋላቸውን የሚያስረዱ መረጃዎች የደረሱን ሲሆን በአካባቢው የታጠቁ ሃይሎች በከፍተኛ ሁኔታ ሲዋከቡ መታየታቸውን ለመረዳት ችለናል።

የቤተመንግስት ጠባቂዎች የደመወዝ ጭማሪ በመጠየቅ የተፈጠረ አለመግባባት እንደነበር እና ችግሩን ለመፍታት ውይይት መደረጉን ለመረዳት ችለናል።

ሁኔታውን የመፈንቅለ መንግስት ሂደት ይመስላል የሚሉ ሌሎች  እማኞች ቢኖሩም አካባቢው አሁን የተረጋጋ እንደሚመስልና ፍተሻው ረገብ ማለት መጀመሩን ገልጸውልናል። ሙሉ መረጃ ይዘን እንመልሳለን።

LEAVE A REPLY