/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በኦሮሚያ ና ቤኒሻንጉል ክልሎች ድንበር ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች ካቅማቸው በላይ መሆኑን ክልሎቹ በጠየቁትና ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሠረት ፌዴራል መንግስት ጣልቃ ገብቶ የማረጋጋት ስራ መጀመሩን የብሔራዊ ፀጥታ ም/ቤትን መግለጫ ጠቅሶ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታወቀ ።
መንግስት ለህግ ማስከበር ሥራ እንቅፋት የሆኑበትን “ጥቅማቸው የተነካ” ፥ የሠብዐዊ መብት ሲጥሱና ሀገር ሲዘርፉ የነበሩ አካላትን ለነዚህና በየቦታው ለሚነሡ ግጭቶች ተጠያቂ ናቸው ብሏል ።
የፀጥታው ምክር ቤት በመግለጫው ግርጌ ህግና ሥርዓትን ለማስከበር የሚደረገው ሁሉ በልሎች ክልሎችም እንደሚቀጥል አስታውቋል ።
የብሔራዊ ፀጥታ ም/ቤት ሙሉ መግለጫ ያንብቡ