በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በርካታ ገነዘበ ተያዘ፤ ለሦስት ሰዓታት ወደ ቻይና የበረረ አውሮፕላን...

በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በርካታ ገነዘበ ተያዘ፤ ለሦስት ሰዓታት ወደ ቻይና የበረረ አውሮፕላን እንዲመለስ ተደርጓል

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ከአዲስአበባ ወደ ቻይና ጉዞ ለሶስት ሠዓታት የበረረ አይሮፕላን ተመልሶ እንዲያርፍ ተደርጎ፤ በርካታ ገንዘቦችን በማሸሽ የተጠረጠረች ግለሠብ በቁጥጥር ስር እንድትውል ተደርጓል ።

የአየር መንገድ ሠራተኛ የሆነ ሠው ያለመፈተሽ መብቱን ተጠቅሞ ወደ ቻይና ለምትጓዘዉ ሴት ሻንጣውን ሲያስተላልፍ በጥርጣሬ ሻንጣውን ተቀብለው ሲፈትሹት 6 ሺህ ፖውንድ፥ 33 ሺህ ዩሮ እና 1 ሚሊዮን 240 ሺህ 976 ብር እንደተገኘ ተገልጿል።

ይህንን ፍተሻ የአየር መንገዱ የፍተሻ ሠራተኞችና የጉምሩክ ሠራተኞች እያኪያሄዱ ሳለ ዋና ተጠርጣሪዋን ያሳፈረው አይሮፕላን ጉዞ ቢጀምርም በመንግስት አካላትና አየር መንገዱ ትብብር ከሶስት ሠዓታት በረራ በኋላ ተመልሶ አዲስ አበባ አርፎ ተጠርጣሪዋ በቁጥጥር ስር መዋሏን ለመረዳት ተችሏል።

LEAVE A REPLY