አፋር ክልል አዲስ ርዕሰ መስተዳድር ሾመ

አፋር ክልል አዲስ ርዕሰ መስተዳድር ሾመ

ሊቀ መንበሯ የመንግስት ሹም በመሆናቸው የመስተዳደሩን ቦታ ም/ሊ/መንበሩ አቶ አወል አርባ ይረከባሉ

/ኢትዮጵያነገዜና/፡- የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጀነር ኤይሻ የክልሉ ገዢ ፓርቲ ሊ/መንበር ሆነው ተመረጡ ።

ውዝግብ የበዛበት እና ከተያዘለት ቀነ ገደብ ተጨማሪ ሁለት ቀናት የወሠደው የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጉባዔ ኢንጂነር አይሻ መሃመድን ሊቀ መንበር ፤ የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ደግሞ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።
ረዥሙ ጉባዔ 11 የፓርቲውን ስራ አስፈፃሚዎች ኮሚቴ አባላት ምርጫንም አካሂዷል።

በዚህም መሰረት፦
1.ኢ/ር አይሻ መሃመድ
2.አቶ አወል አርባ
3.አቶ ኢብራሂም ዑመድ
4.አቶ አህመድ ሱልጣን
5.ወ/ሮ ዘሃራ ዑመድ
6.አቶ መሃመድ ሃሠን
7. አቶ መሃመድ ጠይብ
8.አቶ ጣሃ አህመድ
9. አቶ ዓሊ ሁሴን ዌኢሳ
10. አቶ ኤላማ አቡበከር
11. አሊ ሁሴን ዑመር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጠዋል።

ከህዳር 23 ጀምሮ በሰመራ ሲካሄድ የቆየው የአብዴፓ 7ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባዔም ባለፉት አመታት በክልሉ በነበረው አፈፃፀም እና በወደፊት የልማት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

ሊቀ መንበሯ የፌዴራል መንግስት ሹም በመሆናቸው ።
የርዕሰ መስተዳደሩን ቦታ ም/ሊ/መንበሩ አቶ አወል አርባ እንደሚረከቡ ተረጋግጧል ።

LEAVE A REPLY