/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በሰጠው መግለጫ በየቦታው ለውጡን በመፈታተን ላይ ያሉ ኃይሎችን በቁርጠኝነት ለመታገል መወሠኑንና ለማንኛውም የፀጥታ ስጋት ጥቆማ ማድረስ የሚቻልበትን መንገድ ማዘጋጀቱን አመልክቷል። መግለጫው አንዳንዶች መንግስት የሌለ እየመሰላቸው ሌሎች ደግሞ ተመልሰው ስልጣን ለመያዝ በሚያደርጉት ህገወጥ እንቅስቃሴ የዜጎች ሰላም እያደፈረሰ መሆኑን ጠቁሟል።
ሙሉ መግለጫው እነሆ ፡ –
ከኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት የተሰጠ መግለጫ
ሃገራችን ኢትዮጰያ እየተከተለች በሚገኘው ሁሉን አቀፍ ሃገራዊ ለውጥ የተለያዩ በውስጥም በውጭም ሃገረ የትጥቅ ትግል አማራጫቸው አድረገው ሲታገሉ የነበሩ ሃይሎች ለውጡን ተከትሎ በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ለተደረገላቸውን ጥሪ ተከትሎ ከነ ትጥቃቸው ወደ ሃገረ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።
ይሁን እንጅ መንግስት የዲሞክራሲውን ምህዳረ ለማስፍት በሚያደረገው ሆደ ሰፊነት እና ታጋሽነት አንዳንዶች መንግስት አልባ እየመሰላቸው፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ተመልሶ ወደስልጣን ለመመለስ በሚያደረጉት ህገወጥ እንቅስቃሴ የዜጎች ሰላም እየደፈረሰና የህይወት፣ የንብረት እና ሌሎችም አላስፈላጊ መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ።
ይሁን እንጅ ከዚህ በሗላ መንግስትና መከላከያ ሰራዊታችን ይህንን ስርዓት አልበኝነት በቀላሉ አያየውም። መንግስት ከምንጊዜውም በበለጥ ቁረጠኝነቱን እና የዜጎቹን መብት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እረምጃ ለመውሰድ በተጠንቀቅ ላይ መቆሙንና ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ችግሮች በተከሰቱባቸው አካባቢዎች የማያዳግም እረምጃ መውሰድ እንጀምራለን።
ውድ የኢትዮጰያ ሰላም ወዳድ ህዝብ ሆይ ማንኛውም የፀጥታ ችግር በሚታይባቸው አካባቢዎች ጥቆማዎችን በፌስቡክ ገጻችን በተጠቀሱት ቁጥሮችና
991 addis abeba police coommision
993 orromia police commisssion
916 /915 federal police commission
911 police information service
912 fire bridge service
ሌሎች አድራሻዎች በማድረስ እንድትተባበሩን ጥሪያችንን እናስተላልፍለን።
ኢትዮጰያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!!
የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት
ታህሳስ 10,2011.