የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ

/ኢትዮጵያነገዜና/፡- በክልሎች እና በማንነት ጥያቄዎች ዙሪያ በተደጋጋሚ የሚነሱ ችግሮችን በማያዳግም መልኩ ለመፍታት ያስችላል የተባለው የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።

በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ከተወያየበት በኋላ በ33 ተቃውሞና በ4 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽን በክልሎች የአስተዳደር ወሰንና በማንነት ጥያቄዎች ዙሪያ በተደጋጋሚ የሚነሱ ችግሮችን ሀገር አቀፍ በሆነ እና በማያዳግም መልኩ ለመፍታት ከማከስቻሉም በላይ ከወሰን አስተዳደር ጋር ተያይዞ በብሄር ብሄረሰቦች መካከል የቅራኔ ምንጭ የሆኑ ችግሮችን ገለልተኛ በሆነ፣ ሙያዊ ብቃት ባለው እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍትሄ የሚያፈላልግ መሆኑም ተጠቅሷል።

ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሆነው ኮሚሽኑ አሳታፊ፣ ግልጽ፣ አካታችና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ከአስተዳደር ወሰኖች፣ ራስን በራስ ማስተዳደር እና ከማንነት ጋር የተያያዙ ግጭቶችን እና መንስኤዎቻቸውን በመተንተን የመፍትሄ ሀሳቦችን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለአስፈፃሚ አካላት የማቅረብ አላማ እንዳለውም ተገልጿል።

LEAVE A REPLY