በህገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ዶላር ተበራክቷል፤ 41,693 ዶላር ተያዘ

በህገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ዶላር ተበራክቷል፤ 41,693 ዶላር ተያዘ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የለውጥ እንቅስቃሴ በመካሄድ ላይ እንዳለች በሚነገርላት ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በህገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ገንዘቦች በቁጥጥር ሰር ላይ እየዋሉ መሆኑ ተገለፀ። በትላንትናው እለት 41 ሺህ 693 የአሜሪካ ዶላር በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ደመላሽ ተሾመ እንደተናገሩት ግለሰቦቹ በትናንትናው ዕለት ታህሳስ 10/2011 ዓ/ም በቶጎ ጫሌ ኬላ ነው የተያዙት።

አቶ ደመላሽ አክለውም ተመሣሣይ ወንጀሎችን ለመከላከል መንግሥት ከምንጊዜውም በላይ ጠንክሮ እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረው ህዝቡም እያደረገ ላለዉ ንቁ ተሳትፎ ምስጋናቸዉን ገልጸዋል፡፡

በተደጋጋሚ በድንበር አካባቢዎች የሚታየው ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ብዙዎች ከሀብት ማሸሽ ጋር ሲያያይዙት ጥቂት የማይባሉ አስተያየት ሠጭዎች ግን ለሽብር ተልዕኮ የሚውል ሊሆን ይችላል ሲሉ ይሞግታሉ።

LEAVE A REPLY