ህወሃት ከትከሻ ኦነግም ከአንቀልባ ወርደዋል | መስፍን ማሞ ተሰማ

ህወሃት ከትከሻ ኦነግም ከአንቀልባ ወርደዋል | መስፍን ማሞ ተሰማ

ሠላም ለናንተ ይሁን!

የትግላችንና የመሥዋዕትነታችን የመታሰራችንና የመሰደዳችን ውጤት የሆነው አብያዊው መንግሥት በኢትዮጵያ መንበር ላይ ሲቀመጥ ለ27 ዓመት በምድሪቱ ላይየሰቆቃና የርኩሰት የጥፋትና የዝርፊያ ሁሉ ቁን የሆነውአሸባሪውና ዘረኛው ህወሃት ከኢትዮጵያ ትከሻ ላይያለጥርጥር ተመን ወርዷል

የወረደውና የተዋረደው ህወሃት መቀሌ ትግራይ መሽጎ ይንደፋደፋልበወላለቀ ጥርሱ እየገለፈጠበተሸበሸበ እጁእያጨበጨበ በስታዲየምና በአዳራሽ እየተሰበሰ የቁምተዝካሩን ያወጣል ማጋነን የመሰለው በቅርቡ መቀሌዩኒቨርሲቲ የተካሄደውን ስብሰባ ይመልከት

በዚያ አዳራሽ የክፉ ሰዎች ስብስብ የሆነው ህወሃት ጣዕረሞት ላይ ስለመሆኑ ስብሃት ነጋ አስረጅነት የቀረበ«አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም» የሚለው ብሂል ማሳያ ነው። 27 ዓመት ዲሞክራሲን ቤተ መንግሥት ሆኖ ሲሰይፍ የኖረውህወሃት መቀሌ ላይ መሰየፍ ባቃታቸው የጃጁ እጆቹእያጨበጨበ የፀረ ዲሞክራሲነቱን ተዝካር አውጥቷል

አሸባሪው ህወሃትና በኢትዮጵያ ምድር በአምሳያው ፈጥሮየዘራቸው አሜኬላዎች ሁሉ በለውጡ ማዕበል ተጠራርገውየኢትዮጵያ ትንሣዔ ዕውን እንደሚሆን ከቶም አንጠራጠርም የጊዜ ጉዳይ እንጂ ህወሃት ከነርኩሰቱከነግብረ በላዎቹ መቀመቅ ይወርዳል

ከህወሃት በተጔዳኝ የኢትዮጵያን ትንሣኤ እያወከ ያለው ኦነግነው ህወሃት እንደ ድርጅት ከፅንሱ እስከ ውልደቱከውልደቱ እስከ ጣዕረ ሞቱ ለኢትዮጵያ ጠንቅ እንደሆነ ሁሉኦነግም እንዲሁ ነው ኦነግ ስለ ኢትዮጵያ መጥፋት እንጂስለ ኢትዮጵያ ኖር አልሞም ሆነ ሰርቶ አያውቅምኢትዮጵያውያንን ለመሰየፍና ኢትዮጵያን ለመበተንየሜንጨኛውን ጃዋር እና ኑን የኦነጋውያንን ስብሰባፉከራ ዋቢ ማቅረብ ይበቃል ኢትዮጵያን ማፍረስ እንጂማዳን አላማችን አይደለም ያሉትን

ኢዮባዊ ትዕግሥት የሰፈነበት አብያዊው መንግሥት የኦነግንእኩይነትና በቀል በይቅርታና በንስሃ ለማስተሰረይ በዘረጋለትየሠላም እጅ «ተቀብሎ» ከአስመራ አዲስ አበባ ሲገባ ለኦነግየተደረገውንና ኦነግ በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ደረገውንኢትዮጵያ መቼም አትረሳም ቡራዩ ይመሰክራል

ይህም ሁሉ ሆኖ ለኦነግ «የሳሳ ልብ» የነበረው አብያዊውመንግሥት ባልዋለበት ገድል ኸት ያበዛውን ኦነግበአንቀልባ አዝሎ ሲያባብለው ወራትን አስቆጥሯልኦነግታዝሎም መዝለሉንና ጀርባ መንከሱን አላቆመም ኦነግንያዘለው አብያዊው መንግሥት ኢትዮጵያዊ ነው እናም ኦነግጀርባዋን እየነከሰ የሚያደማው ሠላም ፈላጊዋን ኢትዮጵያንነው ኦነግ ዕብደት ላይ ነውአብይንና ለማን ወለጋ ላይአጥምዶ በጥይት ለመጣል ማሴሩን ሰምተናልአብይ ራሱበአደባባይ ነግሮናልናአብይንና ለማን ለመግደል ማቀድየለየለት ፀረ ኢትዮጵያዊነት ነውኦነግ ታድሶም ተሞርዶከዕብደቱ ሊድን ከቶም አይችልም

ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ኦነግንና ኦነጋውያንን አዝላየምታባብልበት ጀርባ የላትም መቀሌ ትግራይ እንመሸገው አምሳያው ህወሃት ነቀምት ቄለም ወለጋ ውስጥየከተመውና በየጉድባው አድፍጦ ህዝብንና ሀገርንየሚያሸብረው ኦነጋዊ ሁሉ ከኢትዮጵያ ጋር «መደመር» ከቶምቢሆን አይችልምና መቀነስ አለበት

ኦነግ ታዘለበት አንቀልባ ያወረደው ክንዱን ሊያነሳየወሰነው አብያዊው መንግሥት እርምጃው ዘገይምሀገርንና ህዝብን ከኦነግና ኦነጋውያን ጥፋት ለመታደግአልረፈደምና «ቅነሳው» ይበልጥ ተጠናክሮና ፈርጥሞይቀጥል ዘንድ እንጠይቃለን

ከእንግዲህ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ኦነግንና ኦነጋውያንንህወሃትንና ህወሃታውያንን እና መሰል ወዘተርፈዎችንማዘል ሆነ መሸከም አንችልምአንገፍግፈውናልናበቃንበቃን በቃን!!!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ!

ታህሳስ 2011 ዓ/ም (ዲሴምበር 2018)

ሲድኒ አውስትራሊያ

mmtessema@gmail.com

LEAVE A REPLY