መለስ ለቡና ምኑ ነው? በመለስ አስተዳደር የአዲሳባ እግር ኳስ ደጋፊ ከፖሊሶች ዱላ በቀር ምን ተርፎታል? መለስ የአዲስ አበባን ወጣት “አደገኛ ቦዘኔ” ብለው ሌብል ከማድረግ የዘለለ ምን አድርገውለታል? እውነት የቡና ደጋፊ ሆነ የአዲስ አበባ ወጣት የመለስ ዕዳ አለበት?
ይመስለኛል መቀሌዎች የተሸወዱት የመለስ ለቅሶ ግዜ የወጣውን ህዝብ በማየት መለስ ተወዳጅ ነው ብለው በማሰብ ነው ይሄ ብዙዎች የተጭበረበሩበት ክስተት ነው… ወዳጄ ለመለስ ለቅሶ ሰዉ ሆ ብሎ የወጣው… መለስን ስለሚወደው አልነበረም በጣም ጨካኝ ካላልከኝ ካልቀበርኩ አላምንም ብሎ ነው!
እና መቀሌዎች የአዲሳባ ሰው የመለስ ምንም እዳ የለበትም እና መለስን ከዳችሁ ሊባል አይችልም!
የመቀሌዎች ተቃውሞ፤ የቡና ደጋፊዎች ባለፈው ግዜ ከአዲስ አበባ ስታድየም የመለስን ፎቶ ስላወረዱት መሆኑ ነው… ላወቀበት ይሄ ለመለስም ውለታ ነው ሰዉ እያየው “ይሄ እርኩስ” እያለ ባየው ቁጥር ከሚረግመው እንኳንም አወረዱት እናንተስ ብትሆኑ ዘላለም መሰቀሉ እንዴት ደስ ይላችኋል?
ጥሩው ነገር ግን ተቃውሞው ሰላማዊ ነው ነው… እስካሁን ምንም አይነት ጥቃት አልሰማሁም ለዚህ መቀሌዎች አመሰግናለሁ… ጩኸቱን አዲስ አበባ ስታድየም ስትመጡ ታወራርዱታላችሁ!