የእነ አቶ በረከት ክስ በባህርዳር ፍርድ ቤት እንዲቀጥል ተወስኗል

የእነ አቶ በረከት ክስ በባህርዳር ፍርድ ቤት እንዲቀጥል ተወስኗል

/ኢትዮጵያነገዜና/፡- የ62 አመቱ አቶ በረከት ስምዖን እና የ 53 አመት እድሜው አቶ ታደሰ ካሳ ዛሬ በባህርዳር ፍርድ ቤት ቀርበው የተከራከሩ ሲሆን  በእስር ቤት ቆይታችን ሰብዓዊ መብታችንን እና ክብራችንን የሚጎዱ ተግባራት እንደተፈጸመባቸው አቤቱታ አሰሙ። 

እስረኞቹ የገንዘብ ችግር እንዳለባቸው፣ የጤና ችግር ምክንያት የሚቀርብላቸው ምግብ በተገቢው ሰዓት እንደማይቀርብላቸው፣ በጣቢያው አካባቢ የነበሩ ወጣቶች ያለአግባብ የደቦ ፍርድ እየተወሰደባቸውና የፍርድ ሂደቱ ቤተሰቦቻቸው ወደሚኖሩበት አዲስ አበባ እንዲዛወር ጠይቀዋል። በማያያዝም አቶ በረከት ስምኦን ላለፉት ጥቂት ጊዜያት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ሲዘዋወሩ እንደነበር በማስገንዘብ የተከሰሱበትን ክስ በዋስ ተለቀው እንዲከራከሩ ጠይቀዋል።

አቃቤ ሕግ በቅርቡት ቅሬታዎችና ጥያቄዎች ላይ ምላሽ  የሰጠ ሲሆን የክሱን ሂደት በሚመለከትም ወንጀሉ የተፈጸመው በክልሉ መሆኑን በማስገንዘብ በተለይ ተከሳሾቹ በቦርድ አመራርነት በሚመሩት ጥረት በመባል የሚታወቀው ድርጅት በኩል ለእንግሊዝ ካምፓኒ በ90 ሚሊዮን ዶላር የተሸጠው ዳሸን ቢራ ገንዘብ በጥረት ሂሳብ ውስጥ ባለማግኘቱ የምርመራ ሂደቱን እንዳወሳሰበው ገልጿል።

አቃቤ ሕግ በርካታ ምስክሮች በክልሉ እና ከክልሉ ውጭ ስለሚገኙ በመግለጽ መረጃዎችንና ምስክሮችን ለመሰብሰብ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል።

LEAVE A REPLY