የህግ የበላይነት የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መሰረት ነው | የግንቦት 7 መግለጫ

የህግ የበላይነት የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መሰረት ነው | የግንቦት 7 መግለጫ

ሃገራችን ያለችበት የሽግግር ወቅት ብዙ ዋጋ የተከፈለበት ለቀጣዩ ሰላም የሰፈነባት፣ ሁሉንም ዜጎቿን በእኩልነት የምታስተናግድ የጋራ ሃገር ለመመስረት በመቻቻልና በትዕግስት ዘላቂ መፍትሄ የሚተከልበት ወሳኝና በፍፁም ሊያልፈን የማይገባ ወቅት መሆኑን ሰላም ፈላጊ ዜጎች በሙሉ እንደሚረዱት ለዚህም በአንድነትና በፍቅር እንደቆሙ እምነታችን ፅኑ ነው።

እንደሚታወቀው የለውጥ ሂደቱ ከተጀመረ ወዲህ በሃገር ውስጥም ሆና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብን ያስደመሙ በርካታ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማዋቅራዊ መስተካከሎች ተፈጥረው ታይተዋል፣ ተዛማጅ ሂደቶችም እንዲሁ በቀጣይ እንደሚከናወኑ እምነት ተጥሎባቸው ይገኛል።

ይሁን እንጂ ለውጡ ከተረከባቸው በርካታ ውስብስብ ሃገራዊ ችግሮች አንፃር ህዝባችንና ንቅናቄያችንን የሚያሳስቡ ችግሮች በተለያዩ ክልሎች መከሰታቸው አልቀረም።

ስለሆነም በሰሞኑ በለገጣፎ እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች የተወሰዱና እየተወሰዱ ያሉ” ከህገ ወጥ የቦታ ይዞታ ባለቤትነት” ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተብሎ አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደባቸውና የተወሰደባቸው ጉዳዬች በህጋዊና የህግ የበላይነትን ባጋናዘበ መንገድ ብቻ መከናውን የሚገባው መሆኑን እየገለፅን፣ ከህግ ውጭ በተወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች በሚመለከት መንግስት ተገቢ ህጋዊ ማስተካከያ እንዲወስድ አጥብቀን እንጠይቃለን።

አርበኞች ግንቦት ፯
የካቲት 15 / 2011

LEAVE A REPLY