አበው ‘አንድ ሞኝ ያሰረውን ሃምሳ ሊቅ አይፈታውም ‘ እንዲሉ አራት ሚሊዮን ሕዝብ በነበረበት የዛሬ መቶ አመት በሚኒሊክ ዘመቻ አምስት ሚሊዮን ኦሮሞ ተገሏል ብሎ የሚያስተጋባ ይህንንም እውነት አድርጎ የሚከራከር ጅል አይተናል:: ሚኒሊክ ጡትም ቆርጧል በሚል በአንድ ሃሳዊ የወያኔ አሽከር ለቀረበ ድርሰት የአኖሌ ሃውልት በሚሊዮን ብር ወጪም ታንጿል:: ኦሮሞ የሞተላት ባንዲራ የሱ እንዳልሆነች: በመስዋትነቱ ያቆያት ሃገር ለኦሮሞ እስር ቤት በመሆኗ እንድትፈርስ በመቃብሯም ላይ ኦሮምያ የምትባል ሃገር እንዲመሰርት የተዛባ አስተምህሮ በስፉት ተራግቧል:: ይህ ሁሉ የኦሮሞን ሕዝብ የማይመጥን የመከነ አስተሳሰብ በወያኔ አሻጥር: ከእውቀት እጥረት: ከፖለቲካ ድህነት: ፖለቲከኞቹ ከተጣባቸውየበታችነት ስሜት የመጣ ይሆናል በሚልም ሲታለፍ ቆይቷል::
ጸጋውን እረግጦ ጠላት ያስጨበጠውን መርገም ያከበረው የፖለቲካ ኤሊት ጥላቻን እየዘራ መለያየትን እየሰብከ ሃገር ሊያጠፋ ብዙ ድንጋይ ፈንቅሏል:: ለዘመናት በደም ተዋህዶ በጋብቻ ተጋምዶና በማህበራዊ ሕይወት ተቆራኝቶ የኖረውን ሕዝብ ጥቂት ጠላቶች የዘሩት እንክርዳድ ብዙ ሞኞችን አብቅሏል:: ይህው በጥላቻ የሚነዳው የህዝብን ትግል አጣሞ በዘመነ ዲሞክራሲ የከረመ የታሪክ አዛባ እየዛቀ የጥፋት ጉድጏድ የሚቆፍረው መንጋ መስመሩን አልፎ ሕዝብን ከማፋጀቱ በፊት በግዜ አደብ እንዲገዛ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል:: የትም አይደርስም የሚል ንቀትን ትቶ ሃገር ማዳን የሚቻልበትን መላ ለመፈለግ መንቀሳቀስ ይኖርብናል::
ለዚህ ሁሉ ጥላቻ በወተር በአርባጉጉና በበደኖ ለተፈጸመው ጭካኔ: ለሜንጫው ምኞት ለግንጠላው ጥማት: አዲስአበባን ለመንጠቅ የሚደረገው እሩጫ ሁሉ ምንጩ ተገፍቼ ነበር የሚል የተዛባ የታሪክ አተያይ ነው:: ሚሽነሪዎች በወንጌል ጥላ! አረቦች በፋይናንስ: ወያኔና ሻብያ በጥላቻ ታሪክና በበታችነት የፖለቲካ ጥብቆ አደንቁረው ያሳደጉት የኦሮሞ የፖለቲካ ኤሊት የደቀነው አደጋ እራሱንም እንደ ሚያጠፋው ባለመረዳቱ በታሪክ አጋጣሚ እጁ የገባውን ሃገር የመምራት እድል አባክኖ የታሪክ ማፍሪያ እንዳይሆን ደጋግሞ ሊያስብበት ይገባል::
በአንድነት ፖለቲካ አራማጁ በኩል ለዘመናት የተገፋበት የኦሮሞን የፖለቲ ካ ኤሊቶች የማባበልና የመለማመጡ መንገድ ከትርፍ ይልቅ ትልቅ ኪሳራ መሸመቻ ሆኗል:: በትክክለኛ የታሪክ ኩነት ላይ ተመስርቶ ግልጽና እውነተኛ አቋምን ማስተናገ ድአለመቻሉ ዛሬ ላይ ለሚታየው የወራሪና የመጤ ትርክት እራሱን የቻለ ጠባሳ እኑሯል:: ታሪክን የመጋራቱና ሃገር በመመስረት ሂደት ውስጥ ሁሉም ወገን ድርሻ ቢኖረው ም ታሪክን በሃቅና በማስረጃ አረጋግጦ ሸውራራ አስተያየቶችን ማረቅ ይገባ ነበር::
የኦሮሞ የፖለቲካ ኤሊት: ሚኒሊክ ከኦሮሞ ይወልዳል ብትለው: የሃይለስላሴ የዘር ሃረግ ከኦሮሞ ቤተሰብ ያለውን ትስስር ቢቆጠር: የኦሮሞ ጀግኖችን ታሪክ ቢነገር ጥላቻ ያወረው የበታችነት ስሜት ያሳበደው መንጋ መቼም አይገባውም:: ከኦሮሞ የሚወለዱትን በሕይወት ያሉ ባለ ግርማ ሞገስና ምሁር የጦርና የሲቪል አስተዳደ ር የቀድሞ መሪዎችን አይቶ: የሃይማኖት አባቶችን ስብከት ሰምቶ ሊስተካከል አይፈልግም:: በጥቁር ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ጉልህና ታላቅ ድርሻ ካለው ማህበረሰብ መፍልቁን ሲነገረው ውሎ ቢያድር አይሰማም:: ጥቂት ሞኞች የነዙትን የጥላቻ ታሪክ አራብቶ ታሪኩ ያደረገውና የባርነት መንፈስ የተቆራኘው መንጋ በደም ጥማትና በበቀል ሱስ ተነስቶ ሊጥለው የሚችለው አደጋ ከባድ ነው::
ጎንደር ቤተመንግስት የኦሮሞ ገዥዎች ሚና ነበራችው የሚል የሚያኮራ ታሪክ ሲነገር ጎረምሳው ጎንደር እስላም ይዋረዳል ባሌ ላይ ቢሆን በሜንጫ አንገቱን ይባላል ይልሃል:: ጎንደር ጎጃም ሸዋና ወሎ የኦሮሞ ደም ደሜ ነው ብሎ ለወገኑ እንዳልጮኽና የጨለማውን ግዜ አብሮ እንዳልተሻገረ ቀን የወጣለት የመሰለው የኦሮሞ ፖለቲከኛ በእርጉዝ ሴት ላይ ጎጆለማፍረስ ፈጠነ:: ሱሪውን አስወልቆ ሲገርፈው የነበረ ውን ከሰው በታች ያዋለውን እናትን ልጇ እሬሳ ላይ ያስቀመጠውን ጥፍር ነቃዩን ጌታቸው አሰፉን መያዝ ሳይችል አሮጊትና ሕጻናትን ቤታቸውን አፍርሶ ሜዳ ላይ ለመጣል ደፈረ::
ጠባቡና ጽንፈኛው በታላቁ ኦሮሞ ስም የሚነግደው መንጋ ለምን በዚህ ሰአት የሞት አዋጁን አነሳ የግንጠላ አጀንዳውን አራገብ አንገት መቅያ ሜንጫውን ሳለ ብሎ መጠየቁ ተገቢ ነው:: በእኔ እምነት ከታች የቀረቡት ሁኔታዎች የተመቸ ግዜ ፈጥሮልናል ከሚል እሳቤ ተነስተው ይመስለኛል::
- ጽንፈኛው ቡድን የማዕከላዊው መንግስት አውራ ሆነው የወጡትን ዶር አብይና ለማ መገርሳን በኦነግ ሁከትና በኦሮሞ አንድነት ሽፉን በተራዘመ ሴራ አዳክሞ በዘረጋው ጽንፈኛ መዋቅር ተጽዕኖ የማሳረፍ አቅሙን በማጠናከሩ
- የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል እንዲሉ የዜግነት ፖለቲካ አራማጁና ገና ከማለዳው እጅ ሰጥቶ በመቀመጡ:: እክቲቪስቱና የሲቪክና የሚድያ ተቋማት ፈጥነው መደመራቸው::
- መላው ሕዝባችን ከኦሮሞ ድርጅት በወጡት ዶ/ር አብይና አቶ ለማ መገርሳ ፍቅር ደንዝዞ በንግግራቸው ውበት ተማርኮ በተስፋ ቃላቸው እረክቶ ከትግሉ ግንባር አፈግፍጎ በመቀመጡ::
- አማራው የሰይጣን ቁራጭ የሰዶም አውራ ከሆነው ሕወሃት ጋር ለፍልሚያ መፋጠጡ:: በውስጥ በተቀሰቀሰበት የጸጥታ መናጋት በመወጠሩ::
- በአማራውና በሌሎች ብሄረሰቦች መካከል ለረጅም ግዜ የዘለቀው የመተጋገዝና በኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ላይ የነበረው የጋራ አመለካከት አሁን ላይ የለም ከሚል አተያይ::
- የአማራን ፖለቲካ እንመራለን የሚሉ ጎረምሶች ባለማወቅ ባራመዱት የተምታታ ትርክት አማራው ከደቡብ ብሄር ተወላጆች ጋር የነበረውን ጠንካራ የኢትዮጵያዊነት ሕብረት አናግቷል ከሚል ግምት!
- በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባሰፈነው ጠባብ ብሄረተኝነት የብሄራዊ አንድነት ስሜት ነጥፏል:: በአዲስ አበባም ሆነ በስልጣን ጠቅላይነት የሚጋፉ የተባበረ ሕብረ ብሄራዊ ሃይል የለም የሚል መደምደሚያ ላይ የተረደሰ ይመስላል::
-
የጽንፈኛው የኦሮሞ ኤሊት ማስደንበሪያና መከራከሪያ እርስታችን ተውሯል: ተገፍተናል : ማንነታችን ላይ በደል ደርሷል የሚል የሻገተ ታሪክ በማንገብ በሐገራችንና በሰላማችን ላይ የመቶ አመት ሂሳብ ለማወራረድ በድፍረትን ሲንቀሳቀስ ቆይቷል::
የታሪክ ሂሳብ ማወራረዱ ለማንም የማይበጅ መሆኑን ዶ/ር መራራ በግልጽ ተደጋግሞ ሲገልጸው የቆየ መሆኑ የሚታወስነው:: ነገር ግን ይህ የተዛባ የታሪክ አተያይ ሳይንሳዊ ቴክኒካዊና ይፋዊ በመሆነ መልኩ በብሄራዊ ደረጃ እንደ ሃገር ሊፈታየሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው:: ኢትዮጵያ ታሪኳን የምትቆጥረው የባርነት ሰንሰለት ከተፈታላቸው አፍሪካውያን አንጻር ሳይሆን ምድርና ሰማይ ከተዘረጋበት አመተ አለም ጀምሮ ቢሆንም ጥቂት ሞኞች ታሪክ ብለው የጀመሩ የተረት ትርክት ይህው ዛሬ ብዙዎች የሚጋሩት ሃገር አጥፊ የፖለቲካ ስንቅ ሆኗል::
ስለሆነም የታሪክ የአርኪዎሎጂ የፖለቲካና የሕግ ባለሙያዎች ያሉበት እውነት አፈላላጊ ኮሚሽን አቋቁሞ;-
ማን ወራሪ ?
ማን ተወራሪ ?
ማን ሰፉሪ ? እንደሆነ
ሃገሪቷም ከየት ተነስታ የት ላይ እንዳለች ?
ዜጎቿ አውቀን በሰላም በአብሮነት ይሁን በልዩነት ለመኖር እንድንችል የታሪክ ጥያቄዎች ሊመለሱ ይገባል:: አለያ የማንም ጀብራሬ ሞቅ ያለው እለት እየተነሳ ችካል የሚተክል ሲመረቅን ከግዛቴ ውጣ ብሎ ሊያውጅ የማይችልበት የእውቀትና የሃገር ባለቤት ነት መብታችን ሊከበር የሚችልበት ግልጽ የሆነ ሁኔታ መፈጠር አለበት::ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርክ!!! አሜን!!!