ትርፋችን የሕዝባችን አንድነት፣ እኩልነት፣ ሰላም እና መረጋጋት ነው!

ትርፋችን የሕዝባችን አንድነት፣ እኩልነት፣ ሰላም እና መረጋጋት ነው!

ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት እና ፍትሕ ግብረ ኃይል በአውሮፓ የተሰጠ የአቅዋም መግለጫ

ትርፋችን የሕዝባችን አንድነት፣እኩልነት፣ሰላም እና መረጋጋት ነው!በዚህ ምክንያት ዘረኛው እና ፋሽስቱ ወያኔ በሕዝባችን ላይ ያደርስ በነበረው የ27 ዓመት የመከራ፣የእስር ፣የእንግልት ዘመናት ሲሰሙ ለኖሩ የሰቆቃ ድምፆች፣የሐገር ህልውና መደፈር እና የብሄራዊ ማንነታችን መዋረድ እረፍት ነስቶን የጨለማው ዘመን ተገፎ ብሩህ ቀን እንዲመጣ እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሚስተናገድባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ይደረግ በነበረው የሞት የሽረት ትግል ሁሉ ከፍተኛ ዋጋ ከፍለናል።

መላው ሕዝባችንም ሆነ ግብረ ኃይላችን በወያኔ ፋሺስቶችም ሆነ በአምሳላቸው ጠፍጥፈው ከሰሩት ኢህአዴግ ምንም የሚገኝ ጥሩ ነገር አለመኖሩን በመረዳቱ በመራራው ትግል ውስጥ ገብቶ ስርዓቱን አንኮታኩቶ ከመቃብር አፋፍ ባቀረበበት ወቅት በድንገት ከመሀል ብቅ ያለው የጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዓብይ እና የቲም ለማ ቡድን ባሳዬው ሕዝባዊነት እና ኢትዮጵያዊነት ሙሉ እምነቱን ጥሎ ከዚህ ከለውጡ ሀይል ጎን መቆሙ እና የለውጥ ጅማሮውን ለማስቀጠል ሙሉ ድጋፉን መስጠቱ ግልፅ ነው።

እኛ የዚህ ግብረ ኃይል አባላትም የሕዝባችንን እፎይታ እና በለውጥ ኃይሉ የታዮትን እጅግ በጣም ፈጣን የሆኑ የለውጥ ጅማሮዎች ስናይ በእጅጉ ተደስተን ከለውጥ ሀይሉ ጎን ቆመን ድጋፋችንን ስናስይ ቆይተናል።

ነገር ግን ሕዝባችንም ሆነ ግብረ ኃይላችን ሙሉ እምነቱን ጥሎ ከጎኑ የቆመለት ለውጥ ከመቅፅበት ሁኔታዎች እየተቀያየሩ ከየአቅጣጫው የምንሰማቸው የሰቆቃ ድምፆች፣ቅጥ ያጣው የዜጎች መፈናቀል፣እየተፈፀሙ ያሉ አሰቃቂ ግድያዎች፣ የእምነት ቤቶች ላይ የሚፈፀሙ ቃጠሎዎች፣ዘረፋዎች እና ግልፅ መድልዎች እጅግ እያሳሰቡን መጥተዋል!

እየሄድንበት ላለነው የቁልቁለት ጉዞም የፍትሕ ስርዓቱ መዛባት ትልቅ አስተዋፅዖ እያደረገ ሲሆን ለዚህም ከብዙ በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል:-የተለያዮ አሰቃቂ ወንጀሎችን፣ኢሰብአዊ ድርጊቶችን፣ዘረፋዎችን የሚፈፅሙ ፣በሕዝባችን መሀል ጥላቻን፣ መለያየትን ፣መቃቃርን እየሰበኩ በግልፅ እልቂትን የሚያውጁ ወንጀለኞች በሕግ ፊት ቀርበው ባግባቡ ሲዳኙ አይታይም፤ ይልቁንም የተገላቢጦሽ የሕዝብአገልጋዮች በሚባሉ የመንግስት ባለስልጣናት ወከባ ይደርስባቸዋል:- ለዚህምበማንነት ላይ ያነጣጠረውን የቡራዮውን ሰቆቃ እና ይህንን የጭካኔ ተግባር የፈፀሙወንጀለኞች ለፍርድ ያለመቅረባቸው ጉዳይ እና ይልቁንም ወንጀለኞቹ ሳይሆኑየተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ሊታደግ በወጣው የአዲስ አበባችን ወጣት ላይ ይደርስየነበረው ወከባ ፣እስር እና እንግልት እጅግ በጣም አጠያያቂ እና እንደምሳሌ ሊጠቀስየሚችል ነው።

ቅድሚያ ለሚገባቸው የሕዝብ ጥያቄዎችም ቅድሚያ ተሰጥቶ ባለመሰራቱሀረጋውያን፣ነፍሰጡር ሴቶች፣ እንቦቀቅላ ህፃናት በግፈኞች ከቤት ንብረታቸው፤ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው የሚያሰሙትን የሰቆቃ ድምፅ መስማት እናማየት እጅግ በጣም ያማል ፤ሆን ተብሎ ታስቦ እና ታቅዶ በአዲስ አበባ፣በድሬዳዋ እናበሌሎችም በተለያዩ ከተሞች በውስጣቸው ያለውን ሕዝብ መብት እየነጠቁበግልፅ ከተሞቹን ለመቀራመት የሚደረጉ እሩጫዎች፤ 27ዓመቱን የፋሽስት ወያኔንየዘረኝነት አገዛዝ ጥለን በለውጥ ጎዳና ላይ ነን ስንል እየተንሰራፋ የመጣው የአንድዘር የበላይነት፤በዜጎች ላይ እየተደረገ ያለው መድልዎ፣ ቀበረንዋል ያልነውንየፋሺስት ወያኔ የዘር ፖለቲካ ለማስቀጠል የሚደርግ እርብርብ በእጅጉአሳዝኖናል።      

ማር በበላሁበት በጣፈጠው አፌ፣

ጎመን ጎረስኩበት አይ አለማረፌ።

በህግ እናስከብራለን ሰበብ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ተሰግስገው በወገኖቻችንላይ ፅንፈኞች የሚፈፅሙት የሰባዊ መብት ጥስት ፣ግድያና ማፈናቀል፣ የዜግነትመብትን ነጠቃ ግፈኛው ወያኔ 27ዓመት ባቆሰለውና ባልደረቀው የጀርባ ቁስል ላይጨው እንደመነስነስ ሆኖ ይሰማናል ሁሉ እልክ አስጨራሽ የሞት ሽረት ትግልሲደርግ የቆዬውም የህዉሀት ፅንፈኞችን በሌሎች ፅንፈኞች (ጠባቦች) በመተካት የሕዝባችንን ስቃይ ለማርዘም እና ሐገራችን እንድትበታተን ባለመሆኑ መንግስትበአስቸኩዋይ በእነዚህ ፀረ ለውጥ ሀይሎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ እና ባስቸኩዋይለሕዝብ ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለማንም ወደ ማይበጀው የእርስበርስ እልቂት እንድናመራ እየገፉባሉ ፅንፈኞች ተጠልፋችሁ እና ያመናችሁን ሕዝብ ከድታችሁ እንደዚህ አይነትአሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚቀጥሉ ከሆነ ሁሉም በሐገሩ እኩል ባለመብትእስኪሆን ድረስ ዛሬም እንደትላንቱ አምርረን እንታገላችሁዋለን።

ሐገራችን ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ!!!

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት እና ፍትሕ ግብረ ኃይል በአውሮፓ!!!                                                                                                                

LEAVE A REPLY