ኢትዮጵያ ነገ ዜና | በአዲስ አበባ ዛሬ ምጽት 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለማድል የእጣ ማውጣት ስነ ስራት ትካሄደ። ሰሞኑን በማህበራዊ እና መገናኛ ብዙሃን አወያይ ርእሰ ጉዳይ የሆነው የአዲስ አበባ የኮንዶምኒየም እጣ አሸናፊዎች ይፋ ሆንዋል::
በዚህም መሰረት የ20/80 ፕሮግራም ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 248 ስቲዲዮ፣ 18 ሺህ 823 ባለ አንድ መኝታ፣ 7 ሺህ 127 ባለ ሁለት መኝታ እና 5 ሺህ 455 ቤቶች ደግሞ ባለ ሶስት መኝታ ናቸው ተብሏል።
ፋና እንደዘገበው በእነዚህ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የሚካተቱት በ1997 ዓ.ም ተመዝግበው በ2005 ዓ.ም በነባር መደብ የተመዘገቡና በ2005 ዓ.ም የአዲስ ባለ ሶስት መኝታ ተመዝጋቢዎች ናቸው።
በእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ እንደተናገሩት፥ በግንባታ ሂደት ሁሉም ተጠቃሚ እንደሚሆን ቢታሰብም በጥንቃቄ ጉድለት ለጉዳትና ማህበራዊ ቀውስ የተዳረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ።
በተለይ ለቤቶች ግንባታ ሲባል ከእርሻ ቦታቸው የለቀቁ አርሶ አደሮችና የአርሶ አደር ልጆች የሁላችንም ህመም ነው ብለዋል። በዚህም የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔና የቤቶች አሰተዳደር ቦርድ አርሶ አደሮችና የአርሶ አደር ልጆች ያለ እጣ እንዲሰጣቸው መወሰኑን ይፋ አድርገዋል።
በተለይ የአዲስ አበባን ጉዳይ እንደ ርካሽ የፖልቲካ ትርፍ ሊንግዱበት በስፋት የሚንቀሳቀሱ የዘውግ ፖልቲከኞች እንድነብሩ የሚታወቅ ሲሆን የክተማዋ አስተዳደርቤቶቹን ለባለ እድለኞች ለመስጠት መወሰኑ ሊበረታታ እንደሚገባው አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል::