በካራማራ ለኢትዮጵያ ዳር ድንበር | ያሬድ ሹመቴ

በካራማራ ለኢትዮጵያ ዳር ድንበር | ያሬድ ሹመቴ

በዛሬው እለት ከዛሬ 41 አመታት በፊት በካራማራ ለኢትዮጵያ ዳር ድንበር ተዋድቀው ነፃነት ለሀገራቸው ያመጡ ጀግኖችን ለመዘከር በትግላችን ሐውልት የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ በተከናወነው መሰናድኦ ላይ የሚዲያ ሆስት ባለሙያው ደቻሳ አንጌቻ ያቀረበው ታሪካዊ ዳሰሳ ለንባብ እንዲመች ሆኖ በማሳጠር እነሆ አቀበንላችኋል።

*በ1952 ብሪቲሽ ሶማሊ ላንድና ኢታሊያን ሶማሊ ከቅኝ ግዛት ነፃ ወጡ። ከ6 ወራት በኃላ የሶማሊያ ሪፐብሊክን መሠረቱ ።

*በመቀጠልም ባለ አምስት ኮከብ ባንዲራ በመቅረፅ (ከኢትዮጵያ፣ ከኬንያ ፣ ከጅቡቲ ) መሬቶችን ለመቁረስ የሚያስችል የታላቋን ሶማሊያ ህልም ለማሳካት ተንቀሳቀሱ።

*እነ ኦብነግና ምሶነግን በመጠቀም ተደጋጋሚ የሰርጎ ገብ ጥቃት ኢትዮጵያ ላይ ማካሄድ ተያያዙ። 1957 ዓ/ም በጀ/ል አማን ሚካኤል አንዶም የሚመራው የኢትዮጵያ ሰራዊት ከተመቱ በኃላ ትንኮሣቸውን ገቱ።

*1962 ዓ/ም ጀ/ል መሀመድ ዚያድባሬ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስልጣን ያዙ። ለተከታታይ 7 አመታትም በሶቪየት ህብረት ድጋፍ ግዙፍ ጦር መገንባት ተያያዙ ።

*በአንፃሩ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር የነበረው ደርግ በመኃል በኢህአፖ ፤ በትግራይና ጎንደር በህወኃትና ኢዲዩ በኤርትራ ክ/ሀገርም ሻዕቢያና ጀብሃ ከከፊል ምፅዋና አስመራ በስተቀር መላ ኤርትራን ተቆጣጥረው ማእከላዊውን መንግስት ክፋኛ አዳክመውት ነበር ።

*ጀነራል መሃመድ ዚያድባሬ በሀምሌ 15 /1969ዓ/ም ከሰርጎ ገብ ጥቃት ወደ ይፋው ወረራ መሸጋገራቸውን አወጁ

*ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም በሚያዚያ 4/1969 ዓ/ም በቴሌቭዢን መስኮት ብቅ ብለው ታሪካዊውን የእናት ሀገር ጥሪ አስተላለፋ ። በጥሪው መሠረት ሰፊ ድጋፍ አገኙ። በጥቂት ጊዜ ውስጥም ከ100,000 በላይ ሚሊሻና መደበኛ ሰራዊት አሰለጠኑ።

*የሶማሌው ወራሪ ኃይል በደቡብ ግንባር እስከ 700km በምስራቅ በኩል ሙሉ ኦጋዴንን ፣ጅጅጋን ይዘው ወደ ሀረርና ድሬዳዋ ጫፍ ቀረቡ።

*ወረራው ሲጀመር ያልተመጣጠነው የኢትዮጵያና የሶማሊያ ኃይል ንፅፅር ይህን ይመስላል። እግረኛ ክ/ጦር ሶማሊያ 8 ኢትዮጵያ 4፤ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ሶማሊያ 8 ኢትዮጵያ 4 ፤ ታንክ ሶማሊያ 608 ኢትዮጵያ 132 ፤ ተዋጊ አውሮፕላን ሶማሊያ 65 ኢትዮጵያ 8 ነበራቸው።

*በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከፊደል ካስሮዋ ሶሻሊስት ኩባ ከ16000-18000 ሰራዊትና የህክምና ባለሞያዎች ከደቡብ የመን በኩል 2000 የታንከኛ ብርጌድ ድጋፍ አግኝታ ነበር ።

*የኢትዮጵያ ሰራዊትም በጀግናው አየር ኃይላችን ታግዞ ሰፊ መልሶ ማጥቃት በሁሉም ግንባር ከፈተ። በእለተ እሁድ የካቲት 26/1970ዓ/ም ካራማራ ላይ የሶማሊያን ተስፋፊ ኃይል አከርካሪውን በመስበር 💚💛❤ ሰንደቅ አላማ የካራማራ ተራራ ላይ በክብር ሰቀለ። ከጥቂት ቀናት በኃላም የጀ/ል ዚያደባሬ ኃይል በይፋ መሸነፋን አምኖ ጦርነት አቁሞ ከቀሪ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ተጠራርገው ወጣ።

* በጦርነቱ መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ 18,200 የህይወት መስዋእት ፤ በ29,200 ቁስለኛ ሉአላዊነቷን ስታስጠብቅ ሶማሊያ ደሞ በ15900 ሞት ፤ በ26,200 ቁስለኛ ኪሳራ ደርሶባት የሀፍረት ሽንፈት ተጎነጨች።

LEAVE A REPLY