ርዮት | አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ ከኦሮሞ አርቲስቶች፣ አትሌቶችና ሌሎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጧቸው ምላሾች (ፌብሩዋሪ 8፣ 2019)
አንዳችን ስለ አንዳችን ተግባራት ካለማወቃችን የተነሳ ካልሆነ በቀር፣ እነ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጠዋትም ማታም ሻይ አብረን ስንጠጣ፣ የኦሮሞን ጥቅም አዲስ አበባ ውስጥ ለማስጠበቅ፣ በተለይም ካሁን ቀደም ተገፍቶ ከአዲስ አበባ ሲወጣ የነበረውን አርሶ አደርና፣ ኦሮሞነት ከከተማ ውጭ እንዳይሆን ከፍተኛ ስራ እየሰሩ ነው፡፡
ስራው የሚያስገኘውን ውጤት አብረን በጋራ የምናየው
ነው የሚሆነው፡፡ ማድረግ ያለብን መርዳት ነው፤ ከጎናቸው መቆም ነው፡፡ በኢንጂነር ታከለ ኡማ ላይ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ ሌላ ዘመቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ ስለ አዲስ አበባ ልዩ ጥቅም የሚባለው ጉዳይ፣ ለፓርላማ ቀርቦ፣ ለምንም ነገር ቀርቦ ወደፊት ከመሄዱ ወዲህ፣ በአዲስ አበባ መንግስት ካቢኔ ውሳኔ የኦሮሞን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚቻልበትን መንገድ ለመፈለግ፣ ካሁን ቀደም የተሰሩትን ስህተቶች ማረም የምንችልበትን መንገድ ለማግኘት እንዲቻል አስበው ሌት ተቀን እየሰሩ ነው ያሉት፤ የአዲስ አበባ
መሪዎች፡፡
ይህንንም ሁሉን ነገር በሚዲያ መናገር አስቸጋሪ ነው፡፡ እኔ ዳታ አልሰጣችሁም፡፡ ከፈለጋችሁ እመኑንና ከጎናችን ቁሙ
እንጂ፣ እዚህ መድረክ ላይ ተናግረን፣ ቃል ገብተን፣ ዳታ ሰጥቼ፣ የገንዘብ መጠን ተናግሬ ልሄድ አልችልም እኔ፡፡ ካመናችሁን (ትረስት ካደረጋችሁን)፣ በቲም ለማ አመራር ካመናችሁ፣ በዶክተር ዐቢይ አህመድ አመራር ካመናችሁ፣ በኢንጂነር ታከለ ኡማ አመራር ካመናችሁ ግን፣ እውነቱን ነው የምነግራችሁ እርዱን፣ አብራችሁን ቁሙ፤ ከላይና ከታች ያለብንን ግፊት ተረዱልን፡፡
ሁሉን ነገር፣ … ለመቶ ዓመታት ጭቆና ስር መቆየት አስቸጋሪ ነው፡፡ የሀገረ መንግስትን እሳቤ (ስቴት ኮንሴፕት) ያጠፋብሀል፤ ስነልቡናህን ይነጥቅሀል፡፡ መንግስት ስትሆን ደግሞ የሆነ ነገር ተናግረህ የሆነውን ያህል ትሰራለህ፡፡ ወደ ቀዬህ ተመልሰህ ደግሞ ከሌሎች አመራሮች ጋር ለዚህ ህዝብ ምን እናድርግለት ብሎ፣ በሊሂቃን (ኤሊት) ደረጃ የራሱ እውነት አለው፡፡ አርቲስቱም የራሱ እውነት አለው፤ እንደምን አድርጌ መሪዎቼን ረድቼ አሻግራለሁ ይላል፡፡ አትሌትም የራሱ እውነት አለው፤ እንደዚህ ነው የሚሰራው፡፡
የኛ ደግሞ ሁሉም ነገር ወደ ገብያ ወጥቶ፣ ወደ አደባባይ ወጥቶ፣ ወደ ሚዲያ ደርሶ፣ ታውጆ፣ ተነግሮ ካልሆነ አይሆንም፡፡ ይሄ ነው እያስቸገረን ያለው፡፡ አብረውን ያሉ ሌሎች ሰዎች በመኖራቸው ደግሞ፣ አዲስ አበባን ጨምሮ፣ የሌሎችን ጥቅም ስለሚነካ ደግሞ በዚያም በኩል ሌላ እሳት አለ፡፡ ጉዳዩ በጣም ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ጉዳይ በብልሃት እንሂድበት፤ በእምነት እንሂድበት፤ አንዳችን
ስለሌላችን ተግባራት ክትትሉ ይኑረን፤ እርስበርሳችን እንደጋገፍ፤ ጎን ለጎን እንቁም፤ መብታችን ምላሽ ያገኛል ብለን እናምናለን፡፡
ወደ ማእከል መመለስ አለበት ጥያቄያችን፡፡ ይህቺን ኢትዮጵያ የምትባለዋን ሀገርም በእጁ ጠፍጥፎ፣ ቅርጽ ሰጥቶ የሰራት ኦሮሞ እራሱ በመሆኑ፣ ኦሮሞ ኢትዮጵያን እየመራ፣ የኢትዮጵያን አመራር ይዞ ነው፣ ይህቺን ሀገር እየመራ ነው ላሉት ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጠው ብለን ነው የምናምነው እኛ፡፡ ለዚህም እየታገልን ነው፡፡
በእናንተ ድጋፍ፣ አብረን ታግለን፣ አብረን ደክመን ይህን ከግብ አድርሰናል፡፡ የሆነ ምእራፍ ያህል ውጤት ማየት ችለናል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ የተቀሩት ዝርዝር ጥያቄዎቻችን ይመለሳሉ፡፡ የ 150 ዓመታት ጥያቄዎች ነው ያሉን፡፡ የ 150 ዓመታት ጥፋት ነው ያለው፡፡