የክልል ፖለቲካ ጦስ || አብርሃ በላይ ( ኢትዮሚድያ )

የክልል ፖለቲካ ጦስ || አብርሃ በላይ ( ኢትዮሚድያ )

“ውኃ ከጥሩ፣ ነገር ከሥሩ” – ሀገርኛ አባባል!

የሓየሎም አርአያ አባት ኢትዮጵያዊው አርበኛ ደጃዝማች አርአያ ገ/እግዚአብሄር ጣልያን ከተባረረ በኋላ፣ በሽሬ አውራጃ በደመወዝ እንዲተዳደሩ በጃንሆይ ይወሰናል። ጃንሆይ በርካታ አገር-ገንቢ ሥራዎች እንደሰሩ ሁሉ ደካማ ጎንም ነበራቸው። አንዱም የጣልያን ባንዳዎችን ይሾሙ ነበርና የሽሬ አውራጃ ዋና ጸሐፊ እና ገንዘብ ከፋይ ሁነው የተሾሙት ደግሞ ኤርትራዊው አቶ ሓጎስ (የዛሬው የህወሃት ፖሊትቢሮ አባል የቴዎድሮስ ሓጎስ አባት) ነበሩ። አቶ ሓጎስ ያው እንደ አቶ መለስ አያትና እና እንደ አቶ ስብሃት ነጋ አጎቶች ለጣልያን ያደሩ ባንዳ ነበሩ።

በባንዳ መሾም እጅጉን ያዘኑት አርበኛው ደጃዝማች አርአያ ደመወዛቸውን ለመውሰድ ከጥቂት ወራት በኋላ ወደ አቶ ሓጎስ ቢሮ ይሄዳሉ። አቶ ሓጎስ ደግሞ ደጃዝማች አርአያን ሲያዩ “የት ከርመው ነው አሁን ገንዝብ ክፈለኝ የሚሉኝ?” ይሏቸዋል። ድሮውም ተከፍተው የቆዩት ደጃዝማች አርአያ ከፈረሳቸው ይወርዱና “አንተ ባንዳ – ካንተ ኪስ ክፈለኝ ያልኩህ መሰለህ እንዴ…” ብለው በያዙት ከዘራ ሊያዋራርድዋቸው ሲሉ፣ ሓጎስ ሆዬ ምናቸው ሞኝ ነው? ከአርበኛው ዳጃዝማች እግር ስር ጥቅልል ብለው ይወድቁና፣ “ኧረ ጌታዬ ስቀልድ ነው! ኧረ ስቀልድ ነው! ደግሞስ በገንዘብዎ ምን አግብቶኝ!” ብለው ነፍሳቸውን ያተርፋሉ። ደጃዝማችም – “አንተ ምን ታደርግ፣ ባንዳዎችን እየሾሙ ያዋረዱን ጃንሆይ ናቸው” ብለው ይሄዳሉ።

(ይህ ታሪክ ያጫወቱኝ ልጅ እያሉ ካጎታቸው ከደጃዝማች አርአያ ጋር በቦታው የአይን ምስክር የነበሩት የዛሬው የዲሲ ነዋሪ አቶ መኮንን ዘለለው ናቸው። አቶ መኮንን በቅርቡ ከነ ዶ/ር አረጋዊ በርሀ እና ከእንጂኔር ግደይ ዘርአጽዮን ጋር የታንድ መሪዎች ሆነው ኢትዮጵያ ይገኛሉ)።

ሓየሎም አርአያ በአዲስ አበባ እ.እ.አ. በ1996 በአስመራዎቹና በአራት ኪሎዎቹ የባንዳዎች ሴራ ሲገደል፣ ቴዎድሮስ ሓጎስ ደግሞ ዛሬ የኤፈርት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ከሌሎች አዛውንት ባንዳዎች ጋር መቀሌ ይኖራል።

የባንዳ አገዛዝ በኢትዮጵያ ቀዳሚ ስራው ኢትዮጵያን እንደ ካንሰር ሴሎች የሚበጣጥስ “የዘር ፌዴራሊዝም” መትከል ነበር። ይህ እርምጃ ያለምንም ጥርጥር ሆን ተብሎ የተሰራ ወንጀል ነው። (The killils are political tumors deliberately planted on the body politic of Ethiopia. The tumors – before they become malignant (cancerous) – should be removed to save the country from a painful death. In other words, a change to the constitution is a must. This type of struggle is naturally championed by individuals like the charismatic Eskinder Nega, who identifies himself first and foremost as Ethiopian, has both the vision and courage to mobilize millions of Ethiopians to remove ethnic federalism and save Ethiopia).

ህወሃት አምባገነን አልነበረም። ምክንያቱም አምባገነን እንኳን የሀገሩ ለም መሬቶችዋና የባህር ዳርቻዋ ተሟግቶ ሊሸጥ ቀርቶ፣ ቅንጣት ታክል ያገሩን መሬት አሳልፎ ሲሰጥ በታሪክ አይታወቅምና! ህወሃት ዲሞክራቲክም አልነበረም። ገዳይነቱ ግልጽ ነውና። እንደኔ ከሆነ ህወሃት በስልጣን ላይ የነበረበት ዘመን (1991 – 2018) የጠላት ዘመን ተብሎ በታሪክ ቢመዘገብ የሚመጥን ይመስለኛል።

LEAVE A REPLY