ዶ/ር አብይ የጌዳኦ ተፈናቃዮችን እየጎበኙ ነው: መጎብኘት ያለባቸው ቦታዎች አልታዩም ተብሏል

ዶ/ር አብይ የጌዳኦ ተፈናቃዮችን እየጎበኙ ነው: መጎብኘት ያለባቸው ቦታዎች አልታዩም ተብሏል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የጌድኦ ተፈናቃዮች ላለፉት አስር ወራት ከተለያዩ የአካባቢው ወረዳዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች ዋንኛ ምክንያት ተፈናቅለው በተለያዩ የአካባቢው ትምህርት ቤቶች እና አብያተ ከርስቲያናት ተጠልለው ይገኛሉ::

በመጠለያው አካባቢ ከርሃብ በተጭማሪ ተላላፊ በሽታዎች ከፍተኛ ሰጋት መሆናችውን ኢትዮጵያ ነገ የገለጹት የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአንድ ዲፓርትመንት ሃላፊ ሁኔታው ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበው እንደነበር አይዝንጋም::

የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያትም ሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚጎበኙት ገደብ በተባለ ቦታ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ብቻ እንደሆነ የገለጹ የአካባቢው ተውላጆች ገደብ የሰፈሩ ተፈናቃዮች አካባቢው ከተማ በመሆኑ አስከፊውን ገጽታ ለመመልከት ወደ ውስጥ ዘልቀው በሚገኙ የገጠር አካባቢዎች በከፍተኛ ስቃይ ላይ የሚገኙና አስቸኳይ እርዳታ ሊደርሳቸው የሚገቡ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን አሳስበዋል::

54800061_10156969787196411_3929505088514555904_n

እንደ አካባቢው ነዋሪዎች ገለጻ የጌዲኦ ተጎጅዎችን ጎቲቲ በምትባል መንደር በተለይ በመካነየሱስ: በቃለህይወትና ሮሖቦት አብያተ ክርስቲያናት ተጠልለው እንደሚገኙና የመንግሰት ባለስልጣናትም ሆኑ የተራድኦ ድርጅቶች ትከከለኛ ተጎጀዎችን ጉስቁልና ለመመልከት ወደስፍራው እንዲያቀኑ ይጠይቃሉ::

ሰፕሪንግ አካባቢ ያሉትን ተፈናቃዮች ማየቷን የገለጸችልን በነርስ ሙያ የተሰማራች ኢትዮጵያዊት የህክምና ባለሙያ ዶ/ር አብይ ይህንን ቦታ መጎብኝት አለባቸው ሰትል ገልጻለች::

ባሳለፍነው ሳመንት ጀምሮ በተለያየ መልኩ በስቃይ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ለመታደግ ጥረት ማድረግ በተጀመረበት በአሁኑ ወቅት መንግስትም ትኩርት እንዲሰጥ ግፊት ሲደረግ ሰንብቷል:: ግሎባል አሊያንስ በመባል የሚታወቀው እና ታዋቂው የኪነጥበብ ሰወ ታማኝ በየነ በሚሳተፍበት ተቋም በተጀመረ የጎ ፈንድ ሚ የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት ወደ 1ሚሊዮን የሚጠጋ የአሜሪካን ዶላር እየተሰበሰበ እንደሆን ላማወቅ ተችሏል::

LEAVE A REPLY