ግንቦት 20 ለኔ ፤ ያኔም ሆነ ዘንድሮ || መስፍን ማሞ ተሰማ

ግንቦት 20 ለኔ ፤ ያኔም ሆነ ዘንድሮ || መስፍን ማሞ ተሰማ

ሠላም ለናንተ ይሁን!

በአምባ ገነኑ የደርግ ዘመነ መንግሥት እስከ ግንቦት 20/1983 / ኢትዮጵያውያን (ከዘር ሀረጋቸው በፊትናበላይ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑና የማይደራደሩ፣ ታሪካቸውን በታሪክነት ተቀበሰለው የታሪክ ቂም በቀልያልወረሱና ለዚህም ያልዘመቱ ሁሉሀገር ነበራቸው፤ መቀመጫ ሰሜን ብንወጣ ጎጆ ብንቀልስ ደቡብ ብንወርድስራ ብንፈልግምሥራቅ ብንቀመጥ ሱቅ ብንከፍት፤ ምዕራብ ብንኖር ብንነግድ/ብናስተምር ማንም መጤ፥ ማንም ሠፋሪ እያለ አያፈናቅለንም በገጀራና በቀስትአይፈጀንም ነበር

እንደ መንግሥት ደርግ ሁሉንም ዘር ማንዘር ሳይዘረዝርበሥልጣኑ የመጣበትን ሁሉ ፈጅቷል አስሯል አሳዷል እኔምበወጣትነት ዘመኔ ደርግን ለመጣል ከህይወት መትረፍበመለስ መራር መከራ ተቀብያለሁለዓመታት በወህኒመማቅ ወጣትነት ዘመኔን ገብሬያለሁመስዋዕትነትከፍያለሁ ያም ሆነ ይህ ግን በደርግ አገዛዝ ዘመን ሀገርናታሪክ ነበረኝ/ነበረን ከሁሉም በላይ ደግሞኢትዮጵያዊነታችንን ደርግ አልገፈፈንም በዘር ማንዘርክልል ሸንሽኖ ከሰውነት ተራ አላወረደንም

ግንቦት 20 ግን በኢትዮጵያ የዘመናት ታሪክ የተለየ ነውየጣልያን ቅኝ ገዢ እንኳን ያላደረገውን የወያኔ ኢህአዴግቅኝ ገዢዎች ግፍና ዘመን ወለድ ታሪካቸውን ኢትዮጵያንናኢትዮጵያዊነትን ማርከው ቅኝ ያደረጉበት ወቅ 

በአጭሩ ወያኔ መራሹ ኢህአዴግ ኢትዮጵያን የማረከበት ጊዜነው ግንቦት 20 ኢትዮጵያ እስከ አንገቷ ለሰጠመችበትየዘርና የመጠፋፋት ቂም በቀል አረንቋ ብቸኛው ተጠያቂበግንቦት 20/1983 / የኢትዮጵያን መንበር የማረከው ኢህአዴግ የተባለ የዘረኞች ስብስብ ነው ኢህአዴግ አራትኪሎ ቤተ መንግሥት ሲገባ ኢትዮጵያን ማረክ የዘመተበትን የዘር ማንዘር አሸን ክታብ አራግፎ በምትኩ ኢትዮጵያዊነትን ተላበሶና አትዮጵያዊነቱን እንዳለተቀብሎ ከዘር ቆጠራ ከአጥንት ለቀማ ተላቆ እና የዘርችግኝ እየዘራ ከመኮትኮትጥላቻ ወለድ ታሪክ ከመፈብረክ ይልቅ ብሄራዊ ህብረትንና ኢትዮጵያዊነትን ቢኮተኩትናቢያሳድግ ኖሮ ዛሬ ይህ ሁሉ ዘረኝነት ዋይታ ግፍ እልቂትና መፈናቀል አይኖርም ነበር!!

አዎ! በግንቦት 20 ኢትዮጵያን የተቆጣጠረው የዘር ድርጅቶችስብስብ ኢህአዴግ በመላዋ ኢትዮጵያ የዘረጋው ዘረኛ ሥርዓትባይኖር ኖሮ ዛሬ መጤሰፋሪወራሪክልልብሄር ብሄረሰብህዝብ የሚለው እጅግ ከፋፋይ እና ሁዋላ ቀር መለያመታወቂያችን አይሆንም ነበርይህ ሁሉ ግን ግንቦት 20 ያፈራው አሜኬላ ነው!!

እና ይህንን የግፈኞችና የወራሪ ሥርዐት ነው በበኩሌ ሀገሬን ከለቀቅሁበት የግንቦት 20 ዋዜማ ጀምሮ በስደት ዓለምአቅሜ በፈቀደው ሁሉ ስታገለው የኖርኩትየተሰደድኩትም ሆነ የታገልኩት ኢህአዴግ ከነ ሥርዐተ ማህበሩና አብዮታዊ ዲሞክራሲ ግሳንግሱ ጋር እንዲቀየር ነው

እርግጥ ነው ከመጋቢት 2010 ጀምሮ ወያኔ መራሹ ኢህአዴግበፈላጭ ቆራጭነት አራት ኪሎ ባይኖርም ቅሉ እነሆፍፁማዊ ትዕቢትና አይነኬነት የሚያትት መግለጫ የሚያወጣው ወያኔ አሁንም የኢህአዴግ አከርካሪ ነው። የአራቱ ድርጅቶች አንደኛው አካላቸው ህወሃት ነውሳጠቃልል ግንቦት 20 ኢትዮጵያና ዜጎቿ ኢትዮጵያውያን በኢህአዴግ የተማረኩበት እንጂ ነፃ የወጣንበት አይደለም፤ በግንቦት 20 ላይ አቋሜ 1983 ዓ/ም ላይ ይኸው ነበር ዛሬም2011 / አቋሜ ይኸው ነው!!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር

ግንቦት 20/2011 (ሜይ 28/2019)

ሲድኒ አውስትራሊያ

mmtessema@gmail.com

LEAVE A REPLY