ኢትዮጵያ የ74ኛው የተመድ ጉባኤ ም/ፕሬዝዳንት ሆና ተመረጠች

ኢትዮጵያ የ74ኛው የተመድ ጉባኤ ም/ፕሬዝዳንት ሆና ተመረጠች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ለ74ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳትና ምክትል ፕሬዝዳንት ሀገራትን መርጧል፡፡ ኢትዮጵያ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ምክትል ፕሬዝዳት በመሆን እንድትሰራ ተመርጣለች፡፡

የፊታችን መስከረም ወር ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው 74ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ናይጄሪያ ጉባዔውን በፕሬዝዳንትነት እንድትመራ ተውስኗል:: ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች 5 የአፍሪካ አገራት ደግሞ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ስብሰባውን በተጣማሪነት ይመራሉ ተብሏል፡፡

በ74ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የዘላቂ ልማት ግቦች፣ የፖለቲካ ጉባኤ፣ የፋይናንስ ለልማት ስብሰባ፣ የአየር ንብረት ለውጥና ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን ከከፍተኛ ጉባኤዎቹ መሀል ዋነኛዎቹ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

LEAVE A REPLY