የዘንድሮው የማትሪክ ፈተና 24 ሰዓት በካሜራ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ

የዘንድሮው የማትሪክ ፈተና 24 ሰዓት በካሜራ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የዘንድሮው የ10ኛ ክፍል ፈተና በ138 መስመሮች በሄሊኮፕተር ጭምር በመታገዝ ወደ ፈተና ጣቢያዎች ማሰራጨቱን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

ሀገር አቀፍ የፈተናውን ሂደት በጣምራ የሚመሩት ትምህርት ሚኒስቴር፣ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና የፈተናዎች ኤጀንሲ ናቸው:: በፈተናው ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ሁለቱም ትቋማት  በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና የፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓርዓያ ገብረእግዚአብሄር ለፈተናዎቹ ህትመት፣ ጥራትና ስርጭት ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ጥበቃ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል:: ለእያንዳንዱ የፈተና ህትመት እንቅስቃሴም 24 ስዓት የካሜራ ክትትል መደረጉን ጭምር አስረድተዋል፡፡

በ138 መስመሮች በሄሊኮፕተር ጭምር በመታገዝ ፈተናዎቹ የተሰራጩ ሲሆን፣ በ10ኛም ሆነ በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለሚሳተፉ 82 ሺህ 785 መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ለአበል፣ ትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎች 220 ሚሊየን ብር ወጪ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል፡፡

የትምህር ሚኒስትር ዲኤታዋ ጽዮን ተክሉ በበኩላቸው፤ ተማሪዎች በሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አሉባልታዎች ሳይዘናጉና ሳይደናገጡ ፈተናቸውን መፈተን እንዳለባቸውና ከፈተና ሂደቱ ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚዲያ የሚወጡ መረጃዎች ካጋጠሙም ጥቆማ መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ የዘንድሮው የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በ2 ሺህ 866 የፈተና ጣቢያዎች ይሰጣል፡፡

LEAVE A REPLY