ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ በሱዳን የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ወደሀገር ሲመለሱ፣ ከሱዳን እሥር ቤት የተፈቱ ኢትዮጵያውያንን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡
እሥረኞቹ ትናንት አርብ ግንቦት 30 ቀን ከእስር ተለቅቀው ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ለማድረግ ከዚህ ቀደም በመንግሥት ከተደረጉ ተደጋጋሚ ሙከራዎች ነበሩ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም ትናንት ከሱዳን ባለሥልጣናት ጋር የኢትዮጵያዊያኑን ጉዳይ አንስተው በመነጋገራቸው ታውቋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደረጉት ጥረት ሊሳካ በመቻሉ ለበርካታ ዓመታት በባዕድ አገር ዕስር ላይ የነበሩት ወገኖች ነጻ ሊወጡ ችለዋል፡፡
በአማካይ እስከ 20 ዓመት ተፈርዶባቸዉ እስር ላይ የነበሩት 78 ኢትዮጵያንን ለማስፈታት መንግስት ላለፉት ወራት ከሱዳን መንግስት ጋር ሲደራደር መቆየቱን ከጠ/ሚ/ር ቢሮ የወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡
(ፎቶ ኢቢሲ)