የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ብጥብጥ እንዲነሳ ባደረጉ 58 ተማሪዎች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ብጥብጥ እንዲነሳ ባደረጉ 58 ተማሪዎች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ብጥብጥ እንዲነሳ በማድረግ እና የተቋሙን የመማር ማስተማር ሂደት እንዲደናቀፍ አድርገዋል ባላቸው 58 ተማሪዎች ላይ ዩንቨርስቲው ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል፡፡

ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ግንቦት 27 ቀን 2011 ዓ.ም የዩኒቨርስቲው ሴኔት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ያሳለፈውን ውሳኔ ትናንት አርብ ግንቦት 30 ቀን2011 ዓ.ም በውስጥ ማስታወቂያ ለተማሪዎች ይፋ አድርጓል።

በዩኒቨርሲቲው ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማስተባበር፣ በመምራት እንዲሁም በግልና በቡድን በመሳተፍ፣ በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት በማድረስ እጅ ከፈንጅ የተያዙ 14 ወንድ እና ሁለት ሴት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው እንዲሰናበቱ ሴኔቱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን በመያዝ በተማሪዎችና በዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ላይ ጉዳት ለማድረስ የሞከሩ፣ ጉዳት ያደረሱና የተቋሙን ደንብ የጣሱ 12 ወንድ ተማሪዎችንም ለአንድ ዓመት ከትምህርታቸው ማገዱን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

በተጨማሪም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በሁከትና ብጥብጡ ተባባሪ ለነበሩ 30 ተማሪዎችም የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

LEAVE A REPLY