ብያኔወች
በዚህ ጦማር ላይ ኦነግ እና ኦነጋዊ የሚሉትን ቃሎች የምንጠቀመው ሁሉንም የኦሮሞ ጎጠኛ ድርጅቶና ግለሰቦች (ኦፒዲኦ፣ ኦዴፓ፣ በቀለ ገርባ፣ ጃዋር ሙሐመድ ወዘተ.) በሚያጠቃልል መልክ ነው፡፡ በጎጠኝነት ተጸንሶ፣ ደቁኖ የቀሰሰው የጎጠኘነቱ ሊቅ መለስ ዜናዊ እንዳለው፣ ኦፒዲኦ ፋቅ ቢያደርጉት ኦነግ እንደሆነ ሁሉ፣ ሌሎቹም የኦሮሞ ጎጠኞች እንዲሁ ናቸው፡፡
ብያኔ (definition)፡ ኦነግ ማለት ማናቸውም የኦሮሞ ጎጠኛ ድርጅት ወይም ግለሰብ ማለት ነው፡፡
እንዲሁም በዚህ ጦማር ላይ አማራ የሚለውን ቃል የምንጠቀመው ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ሱማሌ በመሳሰሉ ጥበቶች ራሱን በራሱ ሳያጠብ ጦቢያዊነቱን በማስቀደም በመላዋ ጦቢያ ላይ የሚኖረውን አማረኛ ተናጋሪ ጦቢያዊ በሚያጠቃልል መልኩ ነው፡፡
ብያኔ (definition)፡ አማራ ማለት ጦቢያዊነቱን በማስቀደም በመላው ጦቢያ ላይ የሚኖር አማረኛ ተናጋሪ ማለት ነው፡፡
በዚህ ብያኔ መሠረት አማራ በጦቢያ ውስጥ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ብቻ ሳይሆን ሁለተኛውን ኦሮሞን በሚሊዮኖች ይበልጣል፡፡ በሌላ አባባል በጦቢያ ውስጥ አማራ በከፍተኛ ደረጃ ዐብይቶን (majority) ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ ንዑስቶኖች (minorities) ናቸው፡፡
ኦሮሞ በጦቢያ ውስጥ ብዙሃን ነው የሚባለው ትርክት(narration) የኦሮሞ ጎጠኞች በመደጋገም ውነት ያስመሰሉት ኦዳ ውሸት ነው፡፡ በምንም ዓይነት ስሌት ኦሮሞ ዐብይቶን ሊሆን አይችልም፡፡
ኦሮምያ የተሰኘው ካማራ፣ ከጉራጌ፣ ከወላይታ፣ ከጉጅ፣ ከሱማሌ ወዘተ በተለጸቁ (annexed) (ማለትም ተነጥቀው በተቀላቀሉ) መሬቶች አለቅጥ የሰፋው ኢፍትሐዊ ክልልበሕዝብ ቁጥር አንደኛ ሊሆን ይችላል፣ ለዚያውም ከሆነ፡፡ ይህ ማለት ግን ኦሮሞ በቁጥር አንደኛ ነው ማለት አይደለም፡፡ ዐብይን ሙሐመድንና ለማ መገርሳን ጨምሮ ኦነጋውያን የሚጣጣሩት ግን እነዚህን እየቅል እውነታወች በማምታታ ለማታለል ነው፡፡ ጥረታቸው ደግሞ በሰፊው ተሳክቶላቸውአብዛኛውን ጦቢያዊ አታለዋል፡፡ ስለዚህም የጦቢያውያን(በተለይም ደግሞ ያማሮች) የመጀመርያ ሥራ መሆን ያለበትየኦነጋውያንን የቁጥር ቅጥፈት በመረጃ ሰይፍ መቅጠፍ፡፡
ሐቅ (fact)፡ ኦሮምያ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ነው ማለት፣ ኦሮሞ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ነው ማለት አይደለም፡፡
የቀማኞች ዲሞክራሲ
ቀማኞች ሲቀማኙ ፍቅረኞች ናቸው፡፡ ዓይናቸውን የሚጥሉት በቅምኝቱ ቱርፋቶች ላይ እንጅ በቅምኝቱ ላይ ስላልሆነ፣ ቅምኝቱን ለማሳካት ማድረግ /የሚገባቸውን/ ሁሉ ባንተ ትብስ መንፈስ በሙሉ ስምምነትና ትብብር ያደርጋሉ፡፡ የቅምኝቱን አመራሮች የሚመርጡት ደግሞ የቅምኝቱን ቱርፋቶች አመርቂ ያደርጋሉ ብለው የሚያምኑባቸውን ግለሰቦች ብቻና ብቻ ነው፡፡ ማናቸውም የቅምኝቱ አመራር አባል ደግሞ የቅምኝት ሚናውን በሚገባ ካልተወጣ /የሚጎዳው/ እሱ ራሱ በመሆኑ፣ ቦታውን ከሱ ለተሻለ ግለሰብ ልቀቅ ሳይባል በደስታ ይለቃል፡፡ ማናቸውም የቅምኝቱ ዐባል ደግሞ ቅምኝቱን አመርቂ ለማድረግ ይበጃሉ የሚላቸውን ሐሳቦች የመግለጽ ሙሉ ነጻነት ብቻ ሳይሆን፣ እንዲገልጽም በእጅጉ ይበረታታል፡፡
ቅምኝቱ ከተከናወነ በኋላ ግን አብዛኞቹ የቅምኝቱ አባሎች በቅምኝቱ ቱርፋቶች ክፍፍል ቅር ይሰኙና በቅምኝቱ ወቅት የነበረው ፍቅር ወደ መናቆር ይለወጣል፡፡ በክፍፍሉ እጅግ የተጎዱት ደግሞ በክፍፍሉ እጅግ በተጠቀሙት ላይ መሣርያ እስከማንሳት ይደርሳሉ፡፡ በክፍፍሉ እጅግ የተጠቀሙት ደግሞ ጥቅማቸውን የሚያስከብር ድርጅት አቋቁመው በዘረፉት ልክየለሽ ሐብትና ንብረት አማካኝነት የበላይነት ይይዙና በሐብታሞች፣ ለሐብታሞች፣ የሐብታሞች የሆነ መንግሥት ይመሠርታሉ፡፡
የዚህ መንግሥት ዋና ሥራ ደግሞ ለግል ሐብት ከሚገባው በላይ አጽንኦት በመስጠት የዋኖቹን ቀማኞች የቅምኝት ቱርፋቶች መጠበቅና ማስጠበቅ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ መንግሥቱ የሚጠመደው በቅምኝቱ ክፍፍል እጅግም ያልተጠቀሙት የቅምኝቱ አባሎች እድላቸውን እየረገሙ ከፍፍሉን አሜን ብለው እንዲቀበሉ የሚያስገድዱ ሕጎችን በመሐገግና ሕግ አስከባሪውን ኃይል በማጠናከር ነው፡፡ አስገዳጆቹ ሕጎችና ደንቦች እየሰፉናእየጠነከሩ ሲሄዱ፣ በቅምኝቱ ወቅት የሰፈነው ነጻነት እየጠበበና እየተዳከመ ይሄድና በጊዜ ሂደት ወደ ሙሉ አምባገንነት ይለወጣል፡፡
እንደዚህ ዓይነት የሆነ ዓላማን ለማሳካት የግድ ስለሚያስፈልግ ብቻ በጊዜያዊነት የሚያገለግል፣ ዓላማው ከተሳካ በኋላ ወደ አምባገነንነት የሚለወጥ ዲሞክራሲ የቀማኞች ዲሞክራሲ ይባላል፡፡ የዚህ ጦማር ዓላማ ደግሞ የኦሮሞ ገዳ የሚባለው ሥርዓት ኦነጋውያን እንደሚሉት እውነተኛ ዲሞክራሲ ሳይሆን፣ ባሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ላይ ለተከናወነው መጠነ ሰፊ ቅምኝት እንዲያገለግል ብቻ በጊዜያዊነት ከተሠረተ በኋላ ቅምኝቱ /ሲገታ/ ወዲያውኑ የከሰመ የቀማኞች ዲሞክራሲ እንደነበር ማስገንዘብ ነው፡፡ አስቀድመን ግን ለዚህ ግንዛቤ የሚረዳንን ግሩም ምሳሌ ባጭሩ እንዳስሳለን፡፡
ያሜሪቃ የቀማኞች ዲሞክራሲ
ወረራ ወይም መስፋፋት ማለት የይፋ ገፈፋ ወይም ቀማኛነት ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል አሜሪቃ፣ ካናዳ አውስትራልያና ኒውዚላንድ የሚባሉት አገሮች ያውሮጳ ጥርቅምቅም ነጮች (በተለይም ደግሞ የእንግሊዞች፣ ስፓኒሾች፣ ፈረንሳዮች፣ ጀርመኖችና ደቾች) ቅምኝታቸውን ለማሳካት ሲሉ ብቻ ሳይወዱ በግድ በመሠረቱት የቀማኞች ዲሞክራሲ አማካኝነት የፈጸሟቸው ቅምኝቶች ውጤቶች ናቸው፡፡
ያሜሪቃን የቀማኛ ዲሞክራሲ ብንወስድ ለቅምኝቱ አመራር የተመረጡት ግለሰቦች (ዋሽንግተን፣ ጀፈርሰን፣ ጃክሰን ወዘተ.) ብዙ ሺ ጋሻ መሬት ቀምተው ጉምቱ ባላባት በመሆን የቀማኛነት ችሎታቸውን በከፍተኛ ደረጃ ያስመሰከሩ ግለሰቦች ነበሩ፡፡ በቅምኝት የተመሠረተችው አሜሪቃ ዲሞክራቲክ የሆነችው ቅምኙቱን ለማሳካት መሆን ስለነበረባት እንጅ፣ መሆን ስለፈለገች አይደለም፡፡
አሜሪቃ ዲሞክራቲክ የሆነችው በዲሞክራሲ ስለምታምን ቢሆን ኖሮ ጥቁር አፍሪቃውያንን እና ፈጅሬ አሜሪቃውያንን(native americans) በተመለከተ ፍጹም ኢዲሞክራቲክ ባልሆነች ነበር፡፡ ቁም ነገሩ ዲሞክራቲክ መሆኗ እንጅ እንዴት ሆነች አይደለም (የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው፣ the end justifies the means) እንዳይባል ደግሞ ዲሞክራሲው የቀማኞች፣ ለቀማኞች፣ በመቀማኞች የሆነ ውስን ዲሞክራሲ ነው፡፡ ማለትም ዲሞክራሲው ትክክለኛ ዲሞክራሲ ሳይሆን የቀማኞች ዲሞክራሲ ነው፡፡
ባርያ ፈንጋዩ ቶማስ ጀፈርሰን (Thomas Jefferson) የነጻነት አዋጅ (Declaration of Independence) በተሰኘው ሐተታው ላይ ሁሉም ሕዝቦች እኩል ናቸው ነው ሲል፣ ሕዝብ የሚለውን ቃል የተጠቀመው በሐይማኖታቸው ተጨቁነው፣ በድኽነታቸው ተንቀው፣ በወንጀለኛነታቸው ተግዘው አሜሪቃ ምድር ላይ የተሰባሰቡንትን ርዝራዥ አንግሎ ሳክሶን ፕሮቴስታንቶችብቻና ብቻ በሚወክል ትርጓሜ እንደነበር ግልጽ ስለነበር ማብራራት አላስፈለገውም ነበር፡፡ አብርሃም ሊንከልን (Abraham Lincoln) ባሮችን ነጻ ወጥታችኋል ሲላቸው ደግሞ ያንግሎ ሳክሶኖችን የቅምኝት ጥቅሞች ለማስከበር የምትዋጉ ወታደሮች የመሆን ነጻነት /አላችሁ/ ማለቱ እንጅ፣ ላንግሎ ሳክሶኖች ብቻ የቀረበውን የዲሞክራሲ ማዕድ ትቋደሳላችሁ ማለቱ አልነበርም፡፡
ያንግሎ ሳክሶኖች ሎሌወች የነበሩት የቀሩት ነጮች (በተለይም ደግሞ አይሪሾችና ጣልያኖች) በጀፈርሰን ‹‹ሕዝቦች›› ውስጥ የተካተቱት እነሱም በቅምኝት ተክነው የቀማኞች አባል ከሆኑ በኋላ ነበር፡፡ የጭቁን ጥቁሮች ትግል እየጠናከረ በመሄድ ያንግሎ ሳክሶኖችን የቀማኛ ዲሞክራሲ መፈታተን ሲጀምር ደግሞ የጀፈርሰንን ‹‹ሕዝብ›› ተርጓሜ ይበልጥ በማስፋት ነጭ በሚለው ቃል መተካት የግድ አስፈለገ፡፡ አንግሎ ሳክሶን ፕሮቴስታንቶች ብቻ ይንፈላሰሱበት በነበረው የቀማኞች ዲሞክራሲ ጃንቤት (mansion) ውስጥ የሚገኙት የተወሰኑት ክፍሎች ለሁሉም ነጮች ተከፈቱና እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ እንዲዝናኑባቸው ተፈቀደላቸው፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከዝቃጭ ይቆጠሩ የነበሩት ምሥራቅ አውሮጳውያን (በተለይም ደግሞ ፖሊሾች፣ ዩክሬኖችና ቸኮች) የጥቁርን ትግል ለማፈን የግድ ስላስፈለጉ ብቻ ደማችን አንድ ነው ተባሉ፡፡ የዝቅተኝነት ስሜት ክፉኛ የጎዳቸው እነዚህ ምሥራቅ አውሮጳውያን ደግሞ ያንግሎ ሳክሶኖች ሽንገላ አማለላቸውና ውነትም ደማችው ካንግሎ ሳክሶኖች ደም ጋር እንድ መሆኑን ለማስመስከር ሲሉ ብቻ ካንግሎ ሳክሶኖች የባሱ ዘረኞች ሆኑ፡፡ ከለማበት የተጋባበት፡፡
ቅምኝት ካለቀ በኋላ የቀማኞች ዲሞክራሲ እንደሚያልቅለት ለመረዳት ባሜሪቃ ውስጥ እየተከሰተ ያለውን ክስተት ማስተዋል ይበቃል፡፡ በቅምኝት ዘመን የነበረው ያሜሪቃ ዲሞክራሲ ለሁሉም ቀማኞች ፍጹም ነጻነት ያጎናጸፈ ዲሞክራሲ ነበር፡፡ ቀማኞቹ በሐብት ይበልጥና ይበልጥ እየተለያዩ ይበልጥና ይበልጥ እየተቃቃሩ ሲሄዱ ግን ዲሞክራሲው ይበልጥና ይበልጥ የሐብታሞች፣ ለሐብታሞች፣ በሐብታሞች እየሆነ መጣ፡፡ ያሜሪቃው የርስበርስ ጦርነት የተነሳውም የደቡቡ ዲክሲ (Dixie) ድኻ ቀማኛ በሰሜኑ ያንኪ(Yankee) ሐብታም ቀማኛ ላይ በማመጹ ነበር፡፡ ከኔ ወይም ከጠላቶች በሚል አጣብቂኝ ውስጥ የሚከተው፣ እኩይ ቡችሎቹን አወድሶ ሰናይ ተቀናቃኞቹን የሚያወግዘው፣ ያሻውን ሹሞ ያሻውን የሚሽረው፣ ሁሉን በጁ በደጁ ያደረገው፣ ዜጎቹን ሰባት/ሃያ አራት የሚሰልለው የዘመኑ ያሜሪቃ መንግሥት ደግሞ ዲሞክራት ነው ከማለት ይልቅ አምባገነንነት የተጠናወተው አጼፈናኝ (imperialist) ነው ማለት ይበልጥ ይገልጸዋል፡፡ በዚህ መንገድ ከቀጠለ ደግሞ ፍጹም አምባገነን የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡
በመሬት ቅምኝት ዘመን የተሠረተው ያሜሪቃ የቀማኞች ዲሞክራሲ፣ የመሬት ቅምኝቱ ሲያክትም ያላከተመበት ምክኒያት ቅምኝቱ አሁንም ቢሆን በተዛዋሪ ዘዴወች በተለይም ደግሞ በጠገራዊ (financial) ዘዴወች እየተከናወነ በመሆኑ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ባለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች አማካኝነት የአልምዕራብ (non-western) አገሮች አንጡራ ሐብት ወደ ምዕራብ አገሮች በተለይም ደግሞ ወደ አሜሪቃን በገፍ የሚጎርፍበት ጠገራዊ ቅምኝት (financial robbery) ዳፋው ከመሬት ቅምኝት ቢብስ እንጅ አያንስም፡፡
የኦሮሞ ገዳ
ኦሮሞ ከመነሻው ፈልሶ፣ በጦቢያ ላይ ተስፋፍቶ፣ ግብርና ተምሮ በቋሚነት ከመስፈሩ በፊት አርብቶ አደር የነበረ በመሆኑ፣ ከኗኗሩ ምንነት የመነጨ ነጻነት የሚመስል መረን ለቀቅነት ወይም ልልነት ነበረው፡፡ ዘላን የተባለበትም ምክኒያት ባሻው ጊዜ ወዳሻው ቦታ ስለሚዘል ነው፡፡ የከብት ጭራ የሚከተል አርብቶ አደር፣ በሬ እንደሚጠምድ አርሶ አደር ጥብቅ ሊሆን አይችልም፣ መሆንም የለበትም፡፡ አርብቶ አደራዊ ኑሮ የሚኖሩ ወይም ደግሞ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ይኖሩ የነበሩ ብሔረሰቦች አኗኗራቸው በተወሰነ ደረጃ ልቅ መሆኑን ለመረዳት ያፋሮችን፣ የኢሳወችን፣ የሱማሌወችን፣ የከረዩወችን፣ የቦረናወችን አኗኗር ከደገኛው ጦቢያዊ ጥብቅ አኗኗር ጋር ማነጻጸር ይበቃል፡፡
ሙሐመድ ሐሰንን የመሳሰሉ የኦሮሞ ታሪክሲነኛወች(historians) ግን የኦሮሞን ከዘላንነት የመነጨ መረን ለቀቅነት ከዲሞክራሲ ጋር ሥራየ ብለው ያምታቱታል፡፡ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ የኦሮሞ ብሔረሰብ ከሌላው ጦቢያዊ በተለየ መልክ ዲሞክራቲክ ነበር በማለት በብዙ ረገዶች(በስነቃሎች፣ በጽሑፍነክ ትውፊቶች ወዘተ.) የሚሰማቸውን ባዶነት ለሙላት ነው፡፡ በዚህ ረገድ ደግሞ ኦሮምኛ የማያውቀው አስመሮም ለገሰ በኦነጋዊ ባልደረቦቹየተተረጎመለትን የገዳ ትርክት ተሳስቶ (ወይም ሆን ብሎ) ወደ ዲሞክራሲ ትርክት በመቀየር የጻፋቸው ጽሑፎች ያንበሳውን ሚና ተጫውተዋል፡፡
የገዳ ስርዓት ማለት የኦሮሞ መስፋፋትና መንሰራፋትን ለማሰለጥ (make efficient) ብቻና ብቻ የተሰረተ የቀማኞች ዲሞክራሲ ማለት ነው፡፡ በሌላ አባባል የገዳ ስርዓትበዲሞክራሲ የሚያምን ሕዝብ የሰረተው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ሳይሆን፣ በቀማኛነት ለመስፋፋት የግድ ስለሚያስፈልግ ብቻ መስፋፋቱ እስከቀጠለ ድረስ እንዲያገለግል የተሰረተየተስፋፊ ቀማኞች ዲሞክራሲ ነው፡፡ የገዳ ስርዓቱ አመራሮች ዲሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የሚመረጡት ደግሞ፣ አነዚህ አመራሮች የመስፋፋትና የመንሰራፋት አመራራቸውን በከፍተኛ ብቁነትና ስልጠት (efficiency) የሚያከናውኑ መሆናቸው ጥቅሙ ለሁሉም የስርዓቱ አባሎች በመሆኑ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ይህን ዓይነት የአመራሮች ዲሞክራሲያዊ አመራረጥ በኦሮሞ መስፋፋት ወቅት እንጅ በፊትም በኋላም አልነበረም፡፡
የገዳ ስርዓት የኦሮሞን ሕዝብ ዲሞክራሲያዊነት የሚያመለክት ልዩ ክስተት ሳይሆን ቀማኞች ቅምኝታቸውን ለማቀላጠፍ የሰረቱት የቀማኞች ዲሞክራሲ ነው፡፡ ከማናቸውም ሕዝብ የመነጨ ማናቸውም ቀማኛ ሲካፈል ይጣላል እንጅ /ሲቀ/ማኝ ግን ፍጹም ዲሞክራሲያዊ ነው፡፡
በቱርኮች ነፍጠኞች የተመራው የግራኝ አህመድ ወረራአማራ የሚባለውን ጀግንነቱ የተመሠከረለትን ታላቅ ሕዝብተቋማት ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ በማፈራረስ እጅጉን አዳከመው፡፡ የሱማሌን ጅራፍ ይሸሹ የነበሩት የኦሮሞ አርብቶ አድሮች ደግሞ ግራኝ የፈጠረላቸውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ባባ ገዳወቻቸው መሪነት ድንገተኛ አደጋ እየጣሉ፣ በሐይማኖቱ ቀናኢ የነበረውን አማራ ስምንተኛው ሺ ደረሰ እስከሚያስብሉት ድረስ ሴት፣ ወንድ፣ ሕፃን፣ አዛውንት ሳይሉ በሰይጣናዊ ጭካኔ ጨፈጨፉት፡፡ የፈሪ ብትር ሆድ ይቀትር ነውና፣ የነዚህ አንድም ቀን ፊት ለፊት ተዋግተው የማያውቁ ፈሪወች ብትር ከግራኝ ብትር የከፋበት አማራ፣ ከግራኝ ቁስል እስከሚያገግም ድረስ ምርጫ ስላልነበረው እጅግ ሰፊና ለም ከነበረው ርስቱ እየተፈናቀለ ከኦሮሞ አደጋ ጣዮች ራሱን በቀላሉ ለመከላከል ወደሚችልባቸው ተራሮች በመሸሽ ዝንጀሮቴኔ ኑሮ ለመኖር ተገደደ፡፡ አደጋ ጣዮቹም አማራውን እግር በግር እየተከተሉ፣ ያማራውን ምድር በየጎሳቸው በመከፋፈል ወረምንትስ፣ ወረቅብጥርስ እያሉ ሰየሙት፡፡ ላኮመልዛ ወሎ፣ ፈጠጋር አሩሲ፣ አንጎት ወለጋ፣ እናርያ ኤሊባቡር፣ ሸምብራ ቁሬ ዱከም፣ በራራ ፊንፊኔ ሆኑ፡፡
አማሮች ነፍጥንና አነፋፈጥን ከፖርቱጋሎች ተምረው ግራኝን አሸንፈው ካገገሙ በኋላ ፊታቸውን ወደ ኦሮሞ ተስፋፊወች አዞሩ፡፡ አደጋ መጣል እንጅ መዋጋት የማይችለው የኦሮሞ ተስፋፊ ባራት ማዕዘናዊ የውጊያ ጥበብ (ፊታውራሪ፣ ግራዝማች፣ ቀኛዝማች፣ ደጃዝማች) በተካኑት አማሮች ፊት መቆም አቃተው፡፡ የነፍጥ ድምጽ ሲሰማ ኦቦው ካቦ ሸማኔ ፈጠነ፡፡ የቱርክ ነፍጠኞች በከፈቱለት ሰፊ በር ያለ ምንም ፊት ለፊት ውጊያ ሰተት ብሎ የገባው የኦሮሞ ተስፋፊ፣ ነፍጥና ነፍጠኛ የሚሉትን ቃሎች አምርሮ ጠላቸው፡፡ ሰይጣኑ፣ ጭራቁ በነፍጠኛ ተመሰለ፡፡ ራቡ፣ ጥማቱ፣ ማይምነቱ፣ አረመኔነቱ በነፍጠኞች ተሳበበ፡፡
አማሮች ግራኝን ድል ነስተው የኦሮሞን ቅምኝት ሲገቱት፣ ቅምኝቱን ለማቀላጠፍ ሲባል ብቻ የተሰረተው የገዳ የቀማኛ ዲሞክራሲ ግልጋሎቱን ስለጨረሰ ወዲያውኑ አከተመ፡፡ የገዳ የቀማኛ ዲሞክራሲ ባቀላጠፈው መስፋፋት ይበልጥ የተጠቀሙት ጉምቱ ቀማኞች አባ ጅፋር፣ አባ ምንትስ የሚባሉ አምባገነኖች ሆኑ፡፡ በቅምኝቱ እጅግም ያልተጠቀመው ተራ ኦሮሞ ባምባገነኖቹ ላይ ሲያምጽባቸው ደግሞ ባማራ ማሰበብ ያዙ፡፡
በኦሮሞ ተስፋፊወች እጅጉን የተበደለው አማራ በደሉን ስላስቆመ ብቻ በዳይ ተደረገ፡፡ አማራ ከመስፋፋት ባይገታን ኖሮ፣ አማራ ወደኋላ ባይመልሰን ኖሮ፣ አማራ እንዲህ ወይም እንዲያ ባያደርገን ኖሮ እያሉ ማላዘን ብቸኛ መጽናኛ ሆነ፡፡ ያማራ ጥላቻ ተለኮሰ፡፡ አማራን ካለጠፋነው ያጠፋናል የሚለውን የሮማን ፕሮቻዝካን (Roman Prochazka) ሐሳብ የጦቢያ ፖሊሲያቸው የማዕዘን ዲንጋይ ያደረጉት ምዕራባውያን ደግሞ ነብታሚ ሙሐመድ ሐሰንን በመሳሰሉ የኦሮሞ ‹‹ምሁሮች›› አማካኝነት በእሳቱ ላይ ቤንዚን ጨመሩበት፡፡
የሙሐመድ ሐሰን ምሁርነት ሙሉ በሙሉ የተገነባው ኦሮሞን ቤተኛ ሐበሻን መጤ በሚለው ትርክቱ ነው፡፡ ይህን ትርክት ግን ብዙም ሐተታ ሳያስፈልግ አጥቂን በቀላሉ ለመከላከል በሚቻልባቸው በኦሮሞ ወቅያኖስ ውስጥ በሚገኙት ዝቋላንና ዝዋይን በመሳሰሉት ደሴቶች የሚኖሩት ጥንታዊ አልኦሮሞወች ከየት መጡ? በሚል አንድ ጥያቄ ብቻ ቆሻሻ ቅርጫት መጣል ይቻል ነበር፡፡
የነ ሙሐመድ ሐሰን ውሸት በእንጭጩ ሳይጋለጥ ቀርቶ ይህን ያህል ገዝፎ፣ ይህን ያህል ሕዝብ ለማሳሳት በመብቃቱ ዋናወቹ ተወቃሾች፣ የጨለማን ጤዛ በጠዋት ፀሐይ ማርገፍ የተሳናቸው (ወይም ያልፈለጉት)፣ የራሳቸው አሮባቸው የሰው የሚያማስሉት፣ የጦቢያ የታሪክ ምሁራን የሚባሉት ግለሰቦች ናቸው፡፡ እነዚህ ምሁራን የፈረንሳይ አብዮት፣ ያሜሪቃ የርስበርስ ጦርነት እያሉ በማያገባቸው ገብተው ሲፈተፍቱ፣ እነ ሙሐመድ ሐሰን በጦቢያ የታሪክ መስክ ላይ ያለ ምንም ተቀናቃኝ እንደ ልባቸው ፏለሉበት፡፡
ዋሾና ውሸቱ አይናቁም፡፡ ተጋጣሚው የቀረ ቡድን በፎርፌ ያሸንፋል፡፡ እነ ሙሐመድ ሐሰን ደግሞ የእስካሁን ግጥሚያወቻቸውን ሁሉንም ያሸነፉት በፎርፌ ነው፡፡ ካሁን በኋላ ግን ፎርፌው መቆም አለበት፡፡ መቆም ያለበት ደግሞ የጨዋነት ሕጸጽ ያለባቸው የኦሮሞ ጎጠኞች መቸም ሊገባቸው ስለማይችል ከፈሪነት በሚቆጥሩት፣ አህያ የበቅሎ አባት በሚባልበት ካህንኛ (politically correct) አነጋገር ሳይሆን፣ አህያ አህያ በሚባልበት መዕምንኛ (politically incorrect) አነጋገር ነው፡፡ ጥያቄው የህልውና ጥያቄ ስለሆነ፣ እንትን ብንል እንትና ይቀየማል የሚባልበት አይደለም፡፡ ሐቅ የሚያንቀው ጓጉሮ ይሙት፡፡
እየየም ሲደላ ስለሆነ፣ በሞት ሽረት ትግል ላይ ትህትናና ጨዋነት ቀርቶ ሰብአዊነትና ዲሞክራሲም ቅንጦት ናቸው፡፡ ለዚህ ማስረጃ ደግሞ ሰብአዊነትና ዲሞክራሲ ከኔ ወዲያ ላሳር የሚለው ያሜሪቃ መንግሥት በሁለተኛው ያለም ጦርነት ወቅት የገዛ ራሱን ዜጎች (እንጥፍጣፊ የጃፓን ደም ስላላቸው ብቻ) ከወንጀለኛ ቆጥሮ ሕፃን፣ ሴት፣ ወጣት፣ አዛውንት ሳይል ንብረታቸውን ነጥቆ፣ የዜግነት መብታቸውን ገፍፎ ሰብጉረኖ(concentration camp) ውስጥ ማጎሩን መጥቀስ ይበቃል፡፡
ሙሐመድ ሐሰን ምኒልክን ወራሪ ሲል፣ እሱ ራሱ የተስፋፊ ልጅ እንደሆነ ሊነገረው ይገባል፡፡ በቀለ ገርባ ፊንፊኔ ኬኛ ሲል የቆጡን አወርድ ብሎ የብብቱ እንዳይጥል ሊገለጽለት ይገባል፡፡ ሌንጮ ለታ በነፍጠኛ ሊያሾፍ ሲሞክር፣ በዱለኛ ሊሾፍበት ይገባል፡፡ ጃዋር ሙሐመድ በቆንጨራ ሲያስፈራራ በነፍጥ ሊንቀጠቀጥ ይገባል፡፡
ኦነግ ደግሞ ስለ ልቦለዳዊው አኖሌ ሲያላዝን ስለ እውነተኛው አርባጉጉ ሊወተወት ይገባል፡፡ አንደኛው ወገን ምዕተ ዓመታት ወደ ኋላ ሂዶ ተስፋየ ገብረአብ እና በረከት ስምኦን የተባሉ አማራጠል እኩይ ቧልተኞች (evil comedians) የጻፉለትን ልቦለዳዊ ስቅጠት (fictional trajedy) ቀን ከሌት እያነበነበ፣ ለኻጩን እያዝረበረበ ሲነፋረቅ፣ ሁለተኛው ወገን ግን ባንደኛው ወገን አሁን ትናንትና የተፈጸሙትን በምስል የተደገፉ አረመኔያዊ ጭፍጨፋወች ከናካቴው መርሳቱ ይቅር የማይባል ኀጢያት ነው፡፡ ለልቦለዳዊው አኖሌ ሐውልት ከቆመ፣ ለእውነተኛው አርባጉጉ የሐውልቶች ሐውልት የማይቆምበት ምንም ምክኒያት የለም፡፡
ለማጠቃለል ያህል የኦሮሞ ሕዝብ ገዳ የሚባል አፍሪቃ በቀል ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሰረተ ዲሞክራሲያዊነትን የተላበሰ ዲሞክራቲክ ሕዝብ ነው የሚባለው ትርክት ምንም መሠረት የሌለው ባዶ ቱልቱላ ነው፡፡ በመጀመርያ ደረጃ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንጅ ዲሞክራሲያዊ ሕዝብ የለም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የገዳ ዲሞክራሲ ምንጭ ቀማኛነት ሳይሆን የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ባህል ቢሆን ኖሮ ራሱ ኦነግ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ነበር፡፡ እነ አቦማ ዋቆ የመሳሰሉትን መሪወቹን የበላው ኦነግ ግን አመራሮቹን መቸም ቢሆን በገዳ ዘዴ ቀይሮ አያውቅም፡፡
ኦነግ እንደ ገዳ ዘመን አገሬውን እየነቀለና እየፈነቀለ በቀማኛነት ሊስፋፋና ሊንሰራፋ እስካልቻለ ድረስ ዲሞክራቲክ ሊሆን አይችልም፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዓይንና ናጫ የነበሩት የኦሮሞ ጎጠኞች በፍቅር ነፍዘው በየቦታው የሚሳሳሙት ደግሞ አዲስ ቅምኝት ስለታያቸው የቀማኛ ዲሞክራሲ ለመመሥረት ነው፡፡ የጦቢያውያን ወሳኝ ትግል ደግሞ ግራኝ ሙሐመድ ላስራ ስድስተኛ ክፍለዘመን አባገዳወች የቅምኝት በር እንደከፈተ፣ ዐብይ አህመድ ለዘመናችን ኦነጎች የቅምኝት በር እንዳይከፍት፣ እየከፈተ ከሆነ ደግሞ ሳይበረግደው ለመጠርቀም ነው፡፡
የሚቀጥለው ጦማር የሚያተኩረው በቅቤ አፉ እየደመረ በጩቤ ልቡ በሚቀንሰው፣ ኦነጋዊነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥና ይበልጥ ግልጽ እየሆነ በመጣው ባብይ አህመድ ላይ ነው፡፡ እስከዚያው የጦቢያ አምላክ አብሔር ይጠብቅዋ፣ ይጠብቀን፡፡ ስላነበባችሁኝ አኮቴ (thank you)፡፡
መስፍን አረጋ ዘነገደ ኩሽ
የትብቱ ቀብር ደሴ ሳላይሽ፡፡
mesfin.arega@gmail.com