የኢትዮጵያ ቡናና መቀሌ 70 እንደርታ ጨዋታ ነገ ያለተመልካች በአ/አ ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ቡናና መቀሌ 70 እንደርታ ጨዋታ ነገ ያለተመልካች በአ/አ ይካሄዳል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ቡናና መቀሌ 70 እንደርታ ጨዋታ ሰኔ 7 በአዲስ አበባ ስታድየም በዝግ ያለ ተመልካች እንዲካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮረኔል አወል አብዱራሂም እንዲሁም የጽህፈት ቤት ኃላፊው ዶክተር እያሱ መርሃጽድቅ ጉዳዩን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም ጋዜጣዊ መግለጫ ፌዴሬሽኑ ተቋርጦ የቆየው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከአርብ ሰኔ 7 ጀምሮ እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ሌሎች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በየአምስት ቀን ልዩነት ይካሄዳሉ፡፡

በዚህም በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ሰኔ 25 እንዲጠናቀቁ ቀን እንደተቆረጠ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የሊግ ኮሚቴ ስብሳቢው ኮረኔል አወል አብዱራሂም አስታውቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY