የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ሃላፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ዋና ኦዲተር ጠየቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ሃላፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ዋና ኦዲተር ጠየቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የባንኩ ሀላፊዎች የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድን እንዲያስተዳድሩ ሃላፊነት ቢሰጣቸውም ሀላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ተብሏል:: በዚህም ከፍተኛ ኪሳራ በመንግስት ላይ ስላመጡ በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባቸው ዋና ኦዲተር ጠይቋል፡፡

ዋና ኦዲተር ቤሮ ይህንን ያለው የ2010 በጀት አመት የበጀትና የዕቅድ አፈጻጸምን አሰመልክቶ ያከናወነውን ስራ በተመለከተ ለህዝብ ተወካዩች ምክርቤት ሪፓርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው:: ስራቸውን በአግባቡ ያልተወጡ የባንኩ አመራሮች በህግ ይጠየቁ ሲልም ምክር ቤቱን ጠይቋል፡፡

የተመደበው 10 ቢሊዮን ብር ለታለመለት አላማ ስለመዋሉ በኦዲት ማረጋገጥ አልተቻለም ያለው ኦዲት ቢሮ በድሬዳዋ ከተማ ብቻ ከ ፈንዱ ብድር የወሰዱ 124 ኢንተርፕራይዞች በስራ ላይ አለመገኘታቸውን በማሳያነት አቅርቧል፡፡

መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም ይህን መሰል ሁኔታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሚታይ የኦዲት ግኝቱ አመላክቷል:: በዚህም መንግስት የተዘዋዋሪ ፈንዱን አፈፃጸም በተመለከተ ፈጣን እርማት ሊያደርግ እንደሚገባና የስራ ሃላፊነታቸውን ያልተወጡ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የስራ ሃላፊዎችም በህግ እንዲጠየቁለት አሳስቧል፡፡

LEAVE A REPLY