በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ዙሪያ የተረጋገጡ እውነቶች ዝርዝር

በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ዙሪያ የተረጋገጡ እውነቶች ዝርዝር

– የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንንና በጡረታ ላይ የነበሩት ሜጄር ጄኔራል ገዛዒ አበራ በጠባቂዎቻቸው ተገድለዋል

– የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና የህዝብ አደረጃጀት አማካሪ የሆኑት አቶ እዘዝ ዋሴ መገደላቸው  ተረጋግጧል

– የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ምግባሩ ከበደ በጥይት ቆስለው ከፍተኛ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

– ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ በአማራ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ  አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል። ክልሉ ከፌዴራል ጋር በመተባበር የመለየት ስራ መያዙን ገልፀዋል።

– በአዲስ አበባ መውጫ እና መግቢያ በሮች ላይ እጅግ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ ሲደረግ አምሽቷል።

– የመፈንቅለ መንግስት ሙከራው የአማራን ህዝብና ክልል የማይመጥን አሳፋሪና አሳዛኝ ክስተት ነው ሲሉ አቶ ደመቀ መኮንን ለስራ ጉዳይ ከሚገኙበት አሜሪካ ተናግረዋል። አቶ ደመቀ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩን የፌደራልና የክልል አካላት በቅርበት እየተከታተለው ነው ብለዋል።
– ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ቆስለው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። ዘግይተው በደረሱ መረጀወች ደግሞ ጄኔራል አሳምነው አለመያዛቸውን እና እየተፈለጉ መሆኑን የአማራ ክልል አስታውቋል።

– ጄነራል ሰዓረ መኮንን በጠባቂያቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ መገደላቸውን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር እና የሕወሓት ሊቀ-መንበር ዶክተር ደብረ ጺዮን ገብረ ሚካኤል ተናግረው የኤታማዦር ሹሙ ግድያ በባሕር ዳር ከተሞከረው መፈንቅለ-መንግሥት ጋር ተያያዥ እንደሆነ ዶክተር ደብረ ፂዮን በመቀሌ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

– ትናንትና በባሕር ዳር ከተማ ጸጥታ አስከባሪዎች ከከፈቱት ተኩስ የተረፉት አቶ ላቀ አያሌው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትን በጊዜያዊነት እንዲመሩ ተሹመዋል።

– አቶ ላቀ በትናንትናው ዕለት በባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው የርዕሰ-መስተዳድሩ ቢሮ ለስብሰባ በተቀመጡበት «አስር ሰዓት ስብሰባ ጀምርን… አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ የተወሰኑ የጸጥታ አስከባሪ ኃይሎች ልብስ የለበሱ መጥተው ቢሯችን ላይ ተኩስ ተኮሱብን። ማለታቸውን ዲ ደብሊው ዘግቧል።

 

LEAVE A REPLY