– የአማራ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ጄነራል አሳምነው ጽጌ በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸው ተገለጸ:: ብርጋድየር ጄነራል አሳምነው ቅዳሜ ዕለት ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ተሞክሯል የተባለውን “መፈንቅለ መንግሥት” መርተዋል ተብልው በመንግስት እየተፈለጉ ነበር::
– የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጄነራል አሳምነው ጽጌ ባህር ዳር ዙሪያ ዘንዘልማ በሚባል ልዩ ቦታ በመንግስት ታጣቂዎች መገደላቸውን ይፋ አድርጓል::
– አቶ ምግባሩ ከበደ ከአደጋው በሗላ ቆስለው በሆስፒታል ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል::
– የኤታማዠር ሹም ጄነራል ሳእረን ገድሏል የተባለው ጠባቂያቸው ራሱን ማጥፋቱን ቢቢሲ ዘግቧል:: የጄነራል ሳእረ የቀብር ስነ ስርአት ነገ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል::