የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም

የሀዋሳ ከተማ፣ የሲዳማ የሀድያ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ከስራ ታገ

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደህዴን) በሲዳማ ዞን ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን የዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ የሲዳማና የሀዲያ ዞን ከፍተኛ አመራሮችን ከሃላፊነት አገደ፡፡

ለተከታታይ ቀናት ዘለቀውና በሐምሌ 11/11/11 ለተፈጠረው የሲዳማ ክልልነት ጥያቄ ገ-ወጥ አመጽ፤ እጃቸው አለበት በመባሉ ነው የሥራ ላፊዎ እግዱ የተላለፈባቸው፡፡ እነዚህ የስራ ላፊዎች በጥቂት ቀናት ውስጥ በቁጥጥር ስር ሊውሉ እንደሚችሉም ከወዲሁ በስፋት እየተነገረ ነው፡፡ ከፍተኛ አመራሮቹ የም/ቤት አባል በመሆናቸው ያለመከሰስ መብታቸው በሕገ ደንቡ አማካይነት እስኪነሳ ድረስ በፖሊስ እንዳልተያዙ በቦታው ካሉ ታማኝ ምንጮቻችን መረዳት ችለናል፡፡

....ን በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ “ሀዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን የገጠር አባቢዎች በተከሰተው ግጭት ውስጥ የራሳቸው ሚና የነበራቸው በመሆኑ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሲዳማ ዞን አመራሮችን ከስራ አግጂያቸዋለሁ” ሲል ይፋ አድርጓል፡፡ የሀድያ ዞን አስተዳዳሪዎችም ተመሳሳይ ዕርምጃ በመውሰዳቸውና አካሄዱን በመከተላቸው ዕግዱ በእነሱም ላይ ተፈፃሚ ሆኗል ብሏል፡፡

በተለይም ላለፉት አስራ ሁለት ወራት በሲዳማ ጉዳይ የነበረው እንቅስቃሴ በግልፅ እየታየ አስቀድሞ መፍትሔ ከማበጀት ይልቅ በዝምታ የተሸበበው ደ.ኢህ.. በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውንና አካላቸውን ካጡ፣ ብዙ ንብረት ከደመ በኋላ አመራሮን ከስራ ማገዱ በብዙዎች ዘንድ መነጋሪያ ርዕስ ሆኗል፡፡

የደ....ንን እንደ ፓርቲ በደቡብ ክልል የመቀጠል ሕልውና ሊፈታን የሚችል ጥያቄ ያነሳው ሲዳማ ደቡብ ክልል የስልጣን መዋቅር በተወላጆቹ አማካይነት አብዛኛው ቦታ ሆን ተብሎ እንዲያዝ፤ በእነ ሽፈራው ሽጉጤ አማካይነት አስቀድሞ መራቱ እየታወቀ ነገሩን በቸልታ መመልከቱ፣ ....ን በብዙ መልኩ ግልብ” እና “ተጋላጭ” ድርጅት እንዲሆን አደርጎታል የሚሉ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። 

ባለቀ ሰዓት “አለሁ” ያለው የወ/ሮ ሞፈሪያት ካሚል ደ....ን በከፋ እና በወላይታ ዞኖችም ተመሳሳይ ድርጊቶች እየተስተዋሉ በመሆናቸው ይህ ሁኔታ በፍጥነት ሊገታ ካልቻለ የዞኑ ላፊዎች በሕግ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ በመግለጫው አሳስቧል፡፡

የአማራ ክልል ም/ቤት የ47 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በጀትን አፀደቀ

የአማራ ክልል ም/ቤት የክልሉን የ2012 በጀት የሆነውን 47 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ተቀብሎ አፀደቀ፡፡ የቀጣይ ዓመት የክልሉ በጀት እንዲፀድቅ የቀረበው በአማራ ክልል ምክር ቤት አራተኛ ቀን የጠዋት መርሃ ግብር ነው፡፡

እንደ ክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ላፊ ጥላሁን መሐሪ (ዶክተር) ገለጻ ከሆነ ከበጀቱ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው ለወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተመደበው በጀት ድጋፍ ነው፡፡ ከመንግስት ግምጃ ቤት ከተመደበው ጠቅላላ በጀት 61 በመቶ ትኩረት ተሰጥቶት የበጀት ድልድሉ መሰራቱንም ከሓላፊው ሪፖርት መረዳት ተችሏል፡፡

በዚህ መሰረት መደበኛ ወይም ለካፒታል ሥራዎች ማስፈፀሚያ 8 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ተመድቧል፡፡ ይህ ከመንግስት ግምጃ ቤት ከተመደበው በጀት 20 ነጥብ 4 በመቶ ድርሻ አለው፡፡ ጥቅል በጀቱ ከባለፈው በጀት ዓመት አንር ሲለካ በ943 ሚሊዮን 420 ሺህ ብር ብልጫ አሳይቷል፡፡ የአዳዲስ ተቋማት መመስረትና የራተኞች ደምወዝ ለውጥ መኖር ለልዩነቱ ምክንያት ሆኗል፡፡ ከበጀቱ ውስጥ 7 ቢሊዮን 207 ሚሊዮን 738 ሺኅ ብር የሚሆነው ለደወዝና ለስራ ማስኬጃ ይውላል፡፡

1 ቢሊዮን 604 ሚሊዮን 262 ሺህ ብር ደግሞ ነባርና አዲስ ካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ እንደሚውልም ተሰምቷል፡፡ የገጠር መንገድ መጠጥ ውሃን በሁሉም አካባቢዎች ለማዳረስ 250 ሚሊዮን ብር ተመድቧል፡፡

የመንግስት ልማት ድርጅቶችን አቅም ለመገንባት 100 ሚሊዮን ብር፣ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የመሬት ዝግጅትና የመሰረተ ልማት አቅርቦት ለማሟላት 700 ሚሊዮን ብር በበጀት ዓመቱ ተይዟል፡፡ ለጤና ጣቢያዎች ግዥ ማስፈፀሚያ፣ ለስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ማስፈተኛ፤ ለመጽሐፍት ህትመት፣ ለተገነቡ ማህበራዊ ተቋማት ማጠናከሪያና ለተሸከርካሪ ግም ከፍተኛ በጀት ተመድቧል፡፡

ካለፈው ዓመት በጀት በ3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለውን የ47 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የ2012 ዓ.ም በጀትን የምክር ቤቱ አባላት ሙሉ በሙሉ አፅድቀውታል፡፡

110 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የያዘ ግለሰብ በጎንደር በቁጥጥር ስር ዋለ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አንድ ግለሰብ ምንጩ ያልታወቀና 110 ሺኅ የአሜሪካ ዶላር በህገ ወጥ  መንገድ  ይዞ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል፡፡

ግለሰቡ ይህን ያህል ዶላር ይዞ መንቀሳቀሱ ብቻ ሳይሆን ማንነቱን በሚገልው መታወቂያው ላይ ስራ ፈላጊ የሚል ጽሁፍ መስፈሩ ግርምት ከመፍጠሩ ባሻገር ከተጠርጣሪው ግለሰብ ጀርባ ያለውን እንቅስቃሴ የበለጠ አጠራጣሪ አድርጎታል፡፡

አቶ ገብረሕይወት አስማረ የተባለው  ግለሰብ አስመልክቶ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት ምክትል ኮማንደር አስማማው ካሴ እንደገለፁት ከሆነ ተጠርጣሪው ግለሰብ እጅ ላይ ከ100 ሺየአሜሪካ ዶላር በተጨማሪ በርካታ የእንግሊዝ ፓውንድ መገኘቱ ታውቋል፡፡

ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ሞተው ከተገኙ አንድ ዓመት ሞላቸው

በኢትዮጵያ ግዙፍ ፕሮጀክ እንደሆነ የሚታመንለት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ (ራሳቸው አጥፍተዋል በሚል ፖሊስ ሲገለጽ) አንድ ዓመት ሆኗቸዋል፡፡

የእዚህ ታሪካዊ ፕሮጀክት ላፊ በለውጡ ማግስት መስቀል አደባባይ መናቸው ውሥጥ ሕይወታቸው አልፎ ከተገኙ በኋላ ፌዴራል ፖሊስ ኢንጅነሩ ራሳቸውን እንዳጠፉ በምርመራ ደርሼበታለሁ ማለ ይታወሳል፡፡ ብዙዎች መግለጫው ባይዋጥላቸውምፖሊስ መኪናው ውስጥ የተገውም ሽጉጥ የኢንጅነሩ እንደነበር አረጋግጫለሁ ማለቱ አይዘነጋም፡

እስካሁን ድረስ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የመነጋሪያ ርዕስ የሆነው የኢንጅነር ስመኘው በቀለ አሟሟት የተለያዩ መላምቶችን እያስተናገደ እነሆ ድፍን አንድ ዓመት ሞልቶታል፡፡ ከጅማሬው አንስቶ የህዳሴውን ግድብ በዋና ስራ አስፈፃሚነት ሲመሩ የቆዩት እኚህ ሰው ከዚህ ዓለም ከሞት ከተለዩ በኋላ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ በቦታው ቢተኩም አሁንም ፕሮጀክቱ ባለበት እንደቆመ ነው ማለት ይቻላል፡፡ መንግስትም የሥራ ውሉ ለተጓተተው ኢንተርናሽናሉ ኒ ካምፓኒ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከመክፈል አልዳነም፡፡

አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ጉዳይ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ አቃቤ ሕግ ያቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎች በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረቡ በመሆኑ፣ ማስረጃዎቹን አቃቤ ህግ እስከ መስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በአማርኛ ቋንቋ አስተርጉሞ እንዲያቀርብ አዟል፡፡

ፍርድ ቤቱ በተባለው ጊዜ የሚቀርቡትን የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ ብይን ለመስጠት መስረከም 30 ቀን 2012 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል፡፡

በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት በጥረት ኮርፕሬት የሀብት ምዝበራ ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያለው አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) “በሙስና እና ስራን በአግባቡ ባለመስራት” ወንጀሎች አራት ክሶች እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል፡፡

ኢቦላ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ጥብቅ ቁጥጥር ተጀመረ

በዴሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

በኮንጎ ማ” ግዛት የኢቦላ ቫይረስ ምልክት በመታየቱና የኢትዮጵያ አየር መንገድም ወደ ዴሞክራቲክ ሪፐብክ ኮንጎ ከተማ በሳምንት ሰባት ቀን በረራ ማድረጉ የቫይረሱ ስርጭ ወደ ገር ቤት የሚገባበትን ዕድል ይፈጥራል የሚል ስጋት በመኖሩ በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የማጣሪያ ፍተሻ እየተካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የጤና ሚንስትሩ ዶክተር አሚን አማን በሶማሌላንድ፣ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን መግቢያና መውጫ በሮች ላይም የጥንቃቄ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ኢቦላ በአሁኑ ወቅት ከኮንጎ አልፎ አሜሪካና ስፔን ላይ መከሰቱን የጠቆሙት ዶ/ር አሚን ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ትልቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ ለእዚህ መከላ ስራ መንግስት 250 ሚሊዮን ብር መድቧል፡፡ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ትኩሳትና ልዩ ምልክቶች ሲታዩ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋማት በማምራት ሊታይ እንደሚገባም ሚኒስትሩ በመግለፅ ይፋዊ ጥሪን አቅርበዋል፡፡

የቦይንግ ማክስ 8 አደጋ መዘዙ በዝቷል

ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 ከተከሰከሰ በኋላ በመላው ዓለም አውሮፕላኖቹ እንዳይበሩ እገዳ የተጣለበት ቦይንግ በአውሮፕላኖቹ መዘዝ በሩብ ዓመት ውስጥ ብቻ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የ3.4 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንዳጋጠመው ይፋ አድርጓል።

በዚህ የተነሳም በተለያዩ ቀጠናዎች ከሚገኙ አየር ተቆጣጣሪዎች ጋር የሚደረገው ትንቅንቅ የሚቀጥል ከሆነ እና አውሮፕላኖቹን በአጭር ግዜ ውስጥ ወደ በረራ መመለስ ካልቻልኩ ማክስ 737 አውሮፕላኖችን ማምረቴን ሙሉ በሙሉ አቆማለሁም ብሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገዱ አውሮፕላን ከመከስከሱ አምስት ወራት ቀደም ብሎ የኢንዶኔዢያው ቦይንግ 737 ማክስ መከስከሱ የሚታወስ ሲሆን የሁለቱ አውሮፕላኖች ለአደጋ መጋለጥ ምክንያት ዝርዝር ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቶች እንዲሁም የአየር በረራ ደህንነት ባለስልጣናት አውሮፕላኖቹ ኤምካስ ተብሎ የሚጠራው መተግበሪያቸው ላይ እክል መኖሩን ጠቁመዋል። ቦይንግም በኤምካስ ስርዓቱ ላይ ችግር እንዳለ አምኖ እሱን ለማስተካከል እየሰራ ይገኛል። ሁለቱ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከተከሰከሱ በኋላ ቦይንግ በወር ያመርት የነበረውን 737 ማክስ ከ52 ወደ 42 መቀነሱን የኩባንያው ሊቀመንበር ለባለሀብቶች ተናግረዋል። በእነዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች ኩባንያው በሶስት ወራት ውስጥ 3.4 ቢሊየን ዶላር ከስሯል።

LEAVE A REPLY