የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም

ከ1 ዓመት ሕፃን ጀምሮ እስከ ጠ/ሚኒስትሩ የጡበት፤ ባለሪዱ  200 ሚለን ችግኝ ተከላ 

200 ሚሊየን ችግኞችን በአንድ ቀን በመትከል በዓለም የክብር መዝገብ ላይ ለማስፈር በዛሬው ዕለት ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም የተደረገው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ፍሬያማ ሆኖ መጠናቀቁ ተሰምቷል፡፡

ከአንድ ቢሊየን በላይ ሕዝብ አላት ተብሎ በሚነገርላት ሕንድ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ የሕዝብ ብዛቷ አንድ መቶ ሚሊዮን ብቻ የሆነው ኢትዮጵያ እስከ እኩለ ቀን ድረስ በነበረው የአረንጓዴ አሻራ ሩጫ 70 ሚሊን ችግኞችን በመትከል ሪከርዱን ለመስበር እንደቻለችም ተነግሯል፡፡

“በለውጡ መንግስት” ፊታውራነትና ሀሳብ አመንጭነት በአንድ ጀንበር 200 ሚሊየን ችግኞችን በመላ ገሪቱ የመትከል ዕቅድ በብዙ መልኩ አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተ ቢሆንም፤ መሪው ሲጠራው ብሎ በመውጣት የሚታወቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ የክረምቱ ቅዝቃዜ፣ የማለዳው ዝናብና ጭቃ ሳይበግረው በነቂስ ወጥቶ የታዘዘውን ፈፅሟል፡፡ በዚህ የችግኝ ተከላ ሂደ ኢትዮጵያውያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስር በሰደደባቸው የብሔርተኝነት ፖለቲካ የነበራቸውን መከፋፈልና መቃቃር በማስወገድገራዊ ጉዳይ አንድ ሆው ሲሰሩመልከት ተችሏል፡

ሀገራችን ካለችበት ውጥንቅጡ የወጣ የፖለቲካ መስመር፣ ሕዝብ ክፉኛ እየተማረረ ከሚገኝበትና ቀን ተቀን ከሚንረው የኑሮ ውድነት ችግር  የሚያወጣውን መሪ እንጂ ችግር የሚተክል መሪ አንፈልግም የሚሉ ወገኖበብዛትተስ ተውለዋል፡፡ የክረምቱ ወራት የጠቅላይ ሚኒስትሩ 4 ቢሊዮን ችግኝ ከተጨባጭ ዕውነታዎች ሲታይ ሊሆን የማይችል ከንቱ ቅዠት ነው በማለት የቁጥርና የሳብ ግነት በፕሮጀክቱ ላይ መኖሩን በምክንያታዊ ነጥቦች የሚቹም አልታጡም፡፡

ችግኝ መትከል በራሱ የአረንጓዴ አሻራ ኖሪያ ብቸኛ መገለጫ መስፈርት ሊሆን እንደማይገባው በመጠቆም፤ ችግኞቹ ከተተከሉ በኋላ ከሰውና ከእንስሳት ጥፋት ለማዳን የተሰራ ጠንካራና አስተማማኝ ነገር አለመኖሩን በመግለፅ“አረንጓዴ አሻራው” የፖለቲካ ትርፍ ማግኛ ዘዴ መሆኑን በመግለጽ መርሃ ግብሩን የሚያጣጥሉ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ በርግጥም ይህ ጉዳይ ዋነኛ ችግር መሆኑን በማለዳው ዘጋቢዎቻችን ዞር ዞር ብለው የቃኟቸውን ስፍራዎች በግልፅ ለመታዘብ ችለዋል፡፡

በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባሉ ወንዛማና ጫካ አካባቢዎች የከተማ መውጫ መንደርደሪያ ስፍራዎች፤ ለችግኝ ተከላው የተቆፈሩት ጉድጉዶች እምብዛም ከአካባቢው ነዋሪ ስፈራ የራቁ ናቸው ማለት አይቻልም፡፡

በእነዚህ ገጠራማ ቦታዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በከብት እርባታ፣ በወተት አቅርቦት በበግና ፍየል ሽያጭ ኑሯቸውን የሚገፉ ከመሆኑ አኳያ የበርካታ ነዋሪዎች እንስሳት ለግጦሽ የሚወጡት ችግኞቹ በተተከበት አካባቢ መሆኑ ዛሬ በስሜታዊነት የተተከሉት ችግኞች ነገ በትክክል የመፅደቃቸውን ነገር አሳሳቢ አድርጎታል፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የችግኝ ተከላ አስተባባሪዎች ነዋሪዎቹን “ለዛሬ ከብቶቹን አታውጧቸው” እያሉ ሲማፀኑ ለመመልከት ተችሏል። ነገስ?

በዚህን መሰሉ አጣብቂኝ ችግሮች ውስጥ ዛሬ በሙላ ሀገሪቱ በርከታ ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል፡፡ ከአንድ ዓመት ሕፃን እስከ ጠ/ሚኒስትሩ ከጎዳና ተዳዳሪው እስከ ኢንጅነሩ፣ ከቤት ሰራተኛ እስከ ክልል ሹመኛ መላውን የሕብረተሰብ ክፍል ባሳተፈ መልኩ የተካሄደውና ሀገራችንን በግማሽ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በዓለም የክብር መዝገብ ላይ በቀዳሚነት ለመስፈር ያስቻላትሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ብቻ ሁለት መቶ ሚሊዮን ሀምሳ አራት ሺህ ችግኞች መተከላቸው ተረጋግጧል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የት ተገኙ? የሚለውን በወፍ በረር እንቃኘው፡፡

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ በአርባ ምንጭና ወላይታ

የሐሳቡ አመንጪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ከሚገኙ ዳገታማ ሥፍራዎች በአንዱ ይገኛሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ አርባ ምንጭ ከተማ ገብተዋል፡፡ በዛው ወላይታ ሶዶም ተገኝተዋል፡፡

ከከተማዋና ከፌደራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ፕሮጀክታቸውን እውን በማድረጉ ሂደት ተሳትፈው፣ የሚመሯት ገር በአስራ ሁለት ሰዓት ውስጥ 66 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የለም ክብረ ወሰንን ጨብጣ የቆየችውን ህንድን በስድስት ሰዓት ርብርቦሽ ብቻ 70 ሚሊዮን ችግኞችን ተክላ ቀዳሚውን ስፍራ እንድትይዝና አዲስ ታሪክ እንዲጻፍ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል፡፡

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ከመላ ሀገሪቱ ከተሞች ሁሉ አርባምንጭና ወላይታ ሶዶን የመረጡት ምክንያት ነው፡፡ አንድም በወቅታዊ የክልል እንሁን ጥያቄ ዞኖቹ ለአመጽ ዳር ዳር ያሉ ከመሆናቸው ባሻገር፤ ባለፈው ዓመት ሰኔ 16 ቀን በመስቀል አደባባይ በደረሰው ቦንብ ፍንዳታ የተሰዋውን የወላይታ ተወላጅ ወጣት ለማሰብ እንደሆነም ታውቋል፡፡ በመስቀል አደበባዩ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ የተሰው ወጣቶችን ጠ/ሚኒስትሩ  በዚህ መልክ ማሰባቸው በራሱ መሪን ትክክለኛ ስብዕና የሚያሳይ ድርጊት እንደሆነ በመጠቆም ብዙዎች አድናቆታቸውን ቸረውታል፡፡

ከአርባ ምንጭ ወደ ወላይታ ሶዶ ያመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወላይታም በተመሳሳይ  የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በወቅታዊ ጉዳዮችና በሃገሪቱ ሁለንተናዊ ችግሮች ዙሪያ በተዘገጀላቸው ፕሮግራም ላይ ከነዋሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት በጎንደር

የኢፌሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ልክ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመሐል ሀገር ሲጠበቁ እሳቸው ግን ወደ ጎንደር ተጉዘዋል፡፡ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ላይ በቅርቡ ወደ ስልጣን ከወጡት፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጋር በመሆንም ተሳትፈዋል፡፡  

የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሴት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን “ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ምንዝ” ቀበሌ ነው ለችግኝ ተከላው ፕሮግራም የተገኙት፡፡

በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ምንዛሮ ቀበሌ 6 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ ዝርያዎችን ያካተ 24 ሺህ ችግኞች ለመትከል የታሰበውን ፕሮግራም አዲሱ አማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና ተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ከክቡር ፕሬዝዳንቷ ጋር  በስፍራው ላይ ገና በማለዳው በመገኘት አስጀምረውታል፡፡

በአካባቢው የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች አርሶ አደሮና ወጣቶች በነቂስ ወጥተው ታሪካዊ አጋጣሚውን በመጠቀም ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በርካታ ችግኞችን ተክለዋል፡፡ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ህብረተሰቡ ችግኖቹን ከመንከባከብ ባሻገር በክረምቱ ወራት የተያዘው 4 ቢሊዮኝን ችግኞችን የመትከል ዕቅድ ዕውን ለማድረግ ከፍተኛ ርብርቦሽ እንዲያካሂድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ረፋድ ላይ ወደ ጎንደር ከተማ የተመለሱት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ በጎንደር ከተማ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን ጎብኝተዋል፡፡    

 ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽሽመልስ አብዲሳ ጥምረት በምስራቅ ሸዋ ዞን

ባለቤታቸውን ወደ አርባምንጭ የሸኙት ቀዳማይ እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ወደ ምስራቅ ሸዋ ዞን (ኦሮሚያ ክልል) በመጓዝ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ በዚህ ስፍራ ወጣቱ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲም በተመሳሳይ ሁኔታ አሻራቸውን አስቀምጠዋል፡፡

በምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ አካባቢ “ጎዲ ገዴ” በሚባለው ስፍራ ተገኝተው ነው ቀደማይ እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸውና አቶ ሽመልስ አብዲሳ የአረንጓዴ አሻራ ቀንን ያስጀመሩት፡፡ለቱ  በተጨማሪ የኢፌሪ አየር ይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ ርደሳና የአየር ይል አባላት፣ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ እንዲሁም ገር መከላከያ ሠራዊት አባላትና የስፍራው ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

ፕሮግራሙ የተገኙ አባገዳዎች በገዳ ስርዓት ለዛፍ እና ለችግኝ የሚሰጠውን ቦታ በማሰብ ዛሬ ለተተከለው ችግኝ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ተገቢውን እንክብካቤ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው እንዲህ ዓይነቱ የተጠናከረ የሕዝብ ሕብረትና አንድነት እስከ ምሽት 12 ሰዓት በሚዘልቀው መርሃ ግብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ በማቅረብ አብሮአቸው ወጥቶ ችግኝ ለተከለው ሕብረተሰብ ልባዊ ምስጋናቸውን አድርሰዋል፡፡

          ከአማራ ክልል ይልቅ የኦሮሚያዋን ትንሽ መንደር የመረጡት ደመቀ መኮንን

በሰፊው የአማራ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ገጠራማ ስፍራዎች መበአንዱ ይገኛሉ የሚለው ግምት የብዙዎች ነበር፡፡ በአሳዛኝ መልኩ ከተቋጨ አንድ ወር ያለፈው የክልሉ ባለስልጣናት የተገዳዳይነት መንፈስ በቅጡ ያልሰከነበትን የፓርቲያቸው መቀመጫ ያልተገኙት (ም/ጠ/ሚ) ደመቀ መኮንን  ወደ ኦሮሚያ ክልል አቅንተዋል፡፡

ገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ትንሽዋ መንደር “ጠዴ” አካባቢ በመገኘት ያስጀመሩ ም/ጠ/ሚኒስትሩ የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ሰውን ከተፈጥሮ ጋር የማዋደድ ተግባር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ብረተሰቡ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ መጽደቃቸውን ማረጋገ እንደሚኖርበትም ጠቁመዋል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የችግኝ ተከላ መር ግብር በጊዜያዊ ስሜትና በትንንሽ አጀንዳዎች የመጠላለፍ አካሄድን ለመቅረፍና አብሮነትን ከጎልበት ባሻገር ፍትህንና አንድነትን ለማንገስ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባዋልም ብለዋል፡፡

 ዶ/ር ደብረፅዮ አረንጓዴ አሻራዬን አኑሪያለሁ አሉ

የትግራይ ክልል ትናንት ማምሻውን ባወጠው መግለጫ ከፌደራል መንግስቱ ቁጥጥር ውጪ መሆኑን ያሳየበት ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሕወሓቶች “ አረንጓዴ ልማት ለመለስ ራዕይ” በሚል መርህ የችግኝ ተከላውንም ሆነ የሚገኘውን የአለም ሪከርድ ክሬዲት ለሟቹ ጠ/ሚ/ር ለመስጠት ፍላጎት እንዳላቸው በመግለጽ ሕዝብና መንግስትን ሆን ብለው ለማበሳጨት ሞክረዋል፡፡ ዛሬ በተለያዩ የክልሉ ቦታዎች ላይም ይህንን የሚያሳይ ምስልና መፈክር በርካታ ወጣቶች ይዘው ታይተዋል፡፡

አወዛጋቢው የትግራይ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አህመድንና ፌደራል መንግስቱን ገር መምራት አይችሉም እያሉ ሲተቹ ቢሰነብቱም፤ ደጋግመው በነገር የሸነቆጡዋቸው አለቃቸው ያመነጩትን አረንጓዴ አሻራ ፕሮጀክት መቀበላቸውን ግን በይፋ አሳይተዋል፡፡

ከዶ/ር ዐቢይ ጋር ሲሆኑ የሚደመሩት፣ ወደ ትግራይ ክልል ለመሄድ ሲሳፈሩ የሚቀነሱት ዶክተር ደብረፅዮን ዛሬ በእንደርታ ወረዳ በልዩ ስሙ “እንደገሸለማ” በሚባል ስፍራ ተገኝተው ችግኝ ተክለዋል፡፡ ከልባቸው ይሁን በተለምዶአዊ የአርቲስት ባህሪያቸው በውል ባይለይለትም አረንጓዴ አሻራዬን አኑሬያለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ለሕዝብም ለመንግስትም ሊጨበጡ ያልቻሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ በዛሬው ቀን ብቻ 12 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተክሉ ነው የገለፁት፡፡ የችግኝ ተከላው በለም አቀፍ ደረጃ ክብረወሰን ለማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን የተፈጥ ብትን ለማዳና የግብርና ምርታችንን ለማሳደግም ተቀዳሚ ዓላማችን አድርገን ልንሰራበት ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዶ/ር ደብረፅዮን ዛሬ በትግራይ የተጀመረውንና እየተካሄደ ያለውን ሁለተኛው የትግራይ ምሁራን ኮንፍረንስን በመቐለ ከተማ አስጀምረዋል፡፡ ከችግኝ ተከላ መር ግብሩ በኋላ ወደ ጉባኤው ያመሩት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የምሁራኑ ኮንፍረንስ ትግራይ ህዝብ ችግሮች መፍትሄ ይሰጣል ብለው እንደሚያም በመክፈቻ ሥነ – ሥርዓላይ ባደረጉት ንግግር ይፋ አድርገዋል፡፡

 የሞፈሪያት ካሚልና ተሸመ ቶጋ ችግኝ ተከላ ጀርባ ያለ ውስጣዊ ስጋት

የጠ/ሚ/ር ዐቢይ አህመድ “ቀኝ እጅ ናቸው” የሚባሉትና ሰሞኑን በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ ገፆች የመግደል ሙከራ እንደተካሄደባቸው ሲወራባቸው የከረሙት የሠላም ሚኒስትሯ፤ ወላይታ ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ ወ/ሮ ሞፈሪያት   ራሳቸውን ችለው ወደሌላ ስፍራ ከማምራት ይልቅ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር አብረው አርባ ምንጭና ወላይታ የተጓዙት ከውስጣዊ ስጋት በመነጨ እሳቤ እንደሆነ ይገመታል፡፡

በክልል እንሁን ጥያቄ የታመመውን የወላይታንና የአርባ ምንጭ ህዝብን ከበሽታው በጊዜ ማከም የደኢህዴንን ሕልውና በሁለት እግሩ ማቆም የፈለጉ ይመስላል፡፡ ተብሏል።  

አምባሳደር ተሾመ ቶጋም ወደ ወላይታ ሶዶ አምርተው ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሰላም ሚኒስቴሯ ሞፈሪያት ካሚል ጋር አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

የደ....ን (የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ሁለቱ ነባር አመራሮች ከመሪያቸው ጋር በመሆን ወደ ወላይታ ሶና አርባምጭ እንዲያመሩ ያስገደዳቸው በዞኑ የተነሳው የክልልነት ጥያቄ  ሲዳማ ዞን የተለያዩ ከተሞች እንደተከሰተው አመፅ እንዳይሸጋገር በመስጋት መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩና ከፍተኛ ባለስልጣናቱ ከችግኝ ተከላው መርሃ ግብር ባሻገር የአባቢውን ነዋሪዎች በጉዳዩ ዙሪያ በጥልቀት ሲያወያዩም ውለዋል፡፡ ቆፍጣናዋና ደፋሯ የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሞፈሪያት ካሚል ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉለት ለውጥ በደቡብ ክልል በተለያያዩ ዞኖች የሚነሳው የመከፋፈል ጥያቄና ሁከት እንዳይቀለበስ ከወዲሁ መስራታቸውና አጋጣሚውን መጠቀማቸው ተገቢም ነው ተብሏል፡፡

LEAVE A REPLY