– ስለ ጄነራል ሰአረ መኮንን ገዳይ: ወታደሩ (ጠባቂው) አሁን በህክምና ላይ ይገኛል፣ አንገቱ ላይ ቆስሏል። ከሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ተይዘዋል። ጥቃቱ የተፈፀመ ቅፅበት “(ጥቃቱ ሲፈፀም) ደውለህ ትነግረኛለህ” ብሎ ነገሮት በሁዋላ ደውሎ የነገረው ተይዟል።
– የሰኔ 15ቱን ሁኔታ አቅልሎ ማየት ልክ አይደለም። እንቅስቃሴ ሲደረግ የነበረው ተጨማሪ ጀነራሎችን ጭምር ለመግደል እንደነበር መረጃ ደርሶናል።
– እኔ በፊት የተለየ የህዝብ ተቀባይነት የነበረኝ፣ አሁን ደሞ የተለየ ተቀባይነት የሌለኝ ነበርኩ ብዬ አላስብም። ተቀባይነቱ ቀነሰ የሚሉ ምን መረጃ ኖሯቸው እንደሆነ አላውቅም።
– የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ገንዘብ አሰባሰብ እኔን ከመደገፍ እና ካለመደገፍ ጋር መያያዝ የለበትም። ሆኖም ከነበረ መሆን አልነበረበትም።
– በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙርያ: አሁን ጭለማ ቤት ታስሮ ያለ የለም፣ ሰው አይገረፍም፣ ጥፍር አይነቀልም።
-ምርጫ: በኢህአዴግ ዘንድ ምርጫው አይደረግ የሚል አንድምታ የለም። ምርጫው ይካሄዳል ብለን እየተዘጋጀን ነው።
– ኢንተርኔት መዘጋት: መዘጋቱ ያስፈለገው የሰዎችን ህይወት እና ንብረት ከጥቃት ለማትረፍ ነው። ኢንተርኔት ውሀ ወይም አየር አይደለም። ለመዝጋት ምክንያት የሆኑንን ምክንያቶች ካልፈታን ለሳምንት ሳይሆን እስከ ወዲያኛው ሊዘጋ ይችላል።
– አሜሪካ ኤምባሲ ለፕሬዝደንት ፅህፈት ቤትነት ተገንብቶ የነበረው ህንፃ ለሰላም እና እርቅ ኮሚሽን ቢሮ ሆኗል። መከላከያ ትልቅ እና ውብ ህንፃ እየገነባ ነው፣ በቅርቡ ይጠናቀቃል። INSAም የራሱን ህንፃ ቦሌ መድሀኒአለም አካባቢ እየሰራ ነው። ሁሉንም በመጪው አመት ለመጨረስ ታስቧል።