ትዝታ /ቢንያም ለማ/

ትዝታ /ቢንያም ለማ/

የትዝታ ስፍራ ልብ ላይ ነው ብሎ ልቡን እያሻሸ የሚያኖጎራጉረው፤
ሽንፈታም አዝማሪን የልኩን ልንገረው??



ንፍጤን እያበሰች አጥብቃ ስታቅፈኝ አጥብቃ ስትስመኝ ካፍንጫዬ የቀረው የናታ’ለም ጠረን፤
እንኮይና ዶቅማ ሸንኮራና ሎሚ ገዝታ እንደምትመጣ የገባቺው ኪዳን፤
# ልቤ_ላይ_የት_አለ ???
.
.
.
.
የተቆለፈውን፥የዳንቴል ሹራቤን፥ከፍታ እየቆለፈች
ጥዑም አንደበቷን፥እንደልጇ እንደኔ፥እያኮላተፈች
ረዥሙ ስሜን ቆርጣ እየቀጠለች
“ዬ” ን እየጨመረች
“ይዬ”ን እያከለች ……
ጎረቤት በር ላይ፥ፊቴን ወደ ቤቱ፥አዙራ እያቆመች
ባልተኮላተፈ፥በተቀላጠፈ፥ርቱዕ አንደበት፥ረዢም ስም ጠርታ፥አደራ እየሰጠች
.
.
.
.
የተዘቀዘቀ፥ዕድፋም ነጠላዋን፥ደጋግማ እያጣፋች
በነተበ ሸበጥ፥አዋራ እያስነሳች
ገበያ ከሚተምም፥የ’ዝብ ጎርፍ መሃል፥ገብታ ከሰጠመች
#ደቂቆች_አለፉ
#ሰዓታት_አለፉ
#ቀናት_አንቀላፉ
#ወራት_ታይተው_ጠፉ
#ዓመታት_ተረፉ
#እመጣለሁ ‘ሚል የመጨረሻ ቃል
እየቆየ ሲሄድ ከእንኮይ ከሸንኮራ እጅጉን ይጠብቃል።
.
.
.
.
ደግሞ………………
በደል በበረዘው፥የጎደለ አደራ፥ዘመን ተለክቶ፥አደገ ተባልኩኝ
አድልዎና ንፍገት፥ባጀቡት ችሮታ፥ልጅነቴን ቸርኩኝ
በውለታ አንቀልባ፥እልፍ ዕዳ እያዘልኩኝ።
*
*
*
*
ያረጉኝን ሳስታውሰው፥ቂመኛ ነህ እየተባልኩ
ያረጉልኝን ስረሳ፥ውለታ ቢስ እየተባልኩ
ማደግ አለመሞት አይደል?፥እንደምንም ይኸው አደግኩ።
.
.
.
ይሁን፦
ይሁን አይባልም፥
አደራ ቢኖርም፥
አደራ ባይኖርም፥
ወይ ማደግ ወይ መሞት፥ለማንም አይቀርም
እንኮይ፣ዶቅማ፣ሎሚ፥ሸንኮራ እያሰቡ
ጠይም ደርባባ ሴት፥እመጣለሁ ኪዳን፥የሰባራ ልብን ‘ሚያነክስ ተስፋ፥አጉል እየቀቡ
ማደግና መኖር ከመሞት አይቀልም፥ከመሞት አይልቅም
እንደውም ለ’ልፍ ቀን፥ለብዙ ዘመናት፥በ’ስትንፋስ ቁጥር ልክ፥ማጣጣር አይሰቅም?
#ይሰቅቃል
# ደሞ ፦
እሳትና ውሃ፥እኩይና ቅዱስ፥ለይታ እያሳየች፥ ያሳደገች እናት፥እመጣለሁ ብላ
አትመጣም የሚል ቃል፥ቢደመጥ ከሌላ
ለ’ኔ ለናቱ ልጅ፥ታምኖ አይታመንም
አለመምጣቷ እንኳ፥ግዙፍ ሃቅ ቢሆንም
ከናፋቂ ልብ ውስጥ፥ቅንጣት ተስፋ አትመክንም።
.
.
.
መናፈቅ የሚሉት፥መራራ ጥበቃን፥ጥቂት ጣ’ም የምትሰጥ፥ተጥላለች ተስፋ
ሐቅ እየገዘፈ፥በጅ ቢዳሰስ እንኳ፥ኮስምና ‘ማትጠፋ……





LEAVE A REPLY