አይ አዲሱ || አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ

አይ አዲሱ || አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ

አዲሱ.. እንጀራ በኪሱ፣
ወጡን በምላሱ፣
ማስጎንበሱ ሳያንስ፣
ጭራሽ ማጰጰሱ።
ይቺ ቤተ እግዚአብሔር.. ይቺ ቤተ ክህነት፣
ቃል-ኪዳን ናት’ና ለዓለም ቅድስና።
ይቺ ቤተ ታቦት..ይቺ ቅድስና፣
ዳግም በሰላሣ አትሸጥምና..
የምትሸቅጠውን ካላወቅህ በቅጡ..
በገበያ አታልፍም፣
ከእብሪት መሰላል አንድ ጊዜ ከወደቅህ..
ዘላለም አተረፍም።
ሳንታመም ብን’ድን ሳይሻል አይቀርም..
ቢያሽረን ነው ጥሩ፣
የሚፈሰው እንባ ደም ነው’ና ግብሩ..
መሿሿም መች ሊሆን ለፀጋ መንበሩ።
.
አዲሱ..መች ይፈራል እሱ..
እንጀራ በኪሱ..ወጡን በምላሱ..
በውርደቱ ልኬት ሁሉን ማስጎንበሱ..
አይ አዲሱ..!

 

LEAVE A REPLY