ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ሊካሄዱ የነበሩ የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ተራዘሙ

ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ሊካሄዱ የነበሩ የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ተራዘሙ

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን ለአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ደብዳቤ ጽፏል።
/Ethiopia Nege News/:- ከኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በከፍተኛ ሊግ የእግር ኳስ ውድድር ደንብ ባወጣው ኘሮግራም መሰረት የሁሉም ክልል ተወዳደሪ ክለቦች በሜዳቸውና በመረጡት ከተማ ስቴዲየም ከሜዳቸው ውጭ ጨዋታቸውን እንደሚያካሂዱ ይታወቃል፡፡

ይሁን ና የ28ተኛው ሳምንት የከፍተኛ ሊግ 2 ጨዋታዎች ማለትም አውስኮድ ከመቀሌ ከተማ እና ባህርዳር ከተማ ከሽረ እንደስላሴ ባህር ዳር ከተማ ላይ እንዲካሄድ ፊዴሬሽኑ ባወጣው ኘሮግራም መሰረት በሁሉም ተወዳዳሪ ክለቦች ዝግጁቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህርዳር ከተማ ከሚገኙ የተለያዩ ቢሮዎች የባህርዳር ጨዋታዎች በአዲስ አበባ እንዲከናወኑ በተደጋጋሚ ጥያቄ መቅረቡን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፈው ደብዳቤ ገልጿል፡፡

ጥያቄው በወቅቱ በፅሁፍ ባለመገለፁ ምክንያት ፌዴሬሽኑ በሚያካሄደው ሃገር አቀፍ የውድድር ኘሮግራም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ስላስከተለም በውድድሩ ደንብ መሰረት ውድድሮቹ የሚካሄዱባቸውን ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ፊዴሬሽኑ ለመወሰን የሚገደድ መሆኑን እናሳውቃለን የሚል ደብዳቤ በቀን 13/2009 ለሁለቱም ክለቦች በመጻፍ ጨዋታው ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል፡፡

በባህርዳርና መቀሌ ከነማ ክለቦች መካከል የሚካሄዱ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግጭቶችና በፖቲካዊ አንድምታዎች እየተስተዋለባቸው እንደሆነ መረዳት ይችላል። ለዚህም ይመስላል የመቀሌ ከነማ “ጥበቃ ይደረግልን፤

ለደህንነታችንም ዋስትና ይሰጠን በማለት እስከ ትናንት ማታ ድረስ ባህር ዳር ከተማ አለመግባታቸው ታውቋል።IMG_6498ባደለፈወው ግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ባህር ዳር ከነማና መቀሌ ከነማ በ23ኛው ሳምንት መቀሌ ላይ በነበረው ጨዋታ ዳኛው ተገቢ ያልሆነ ቅጣት ምት ለመቀሌ ከነማ መስጠታቸውና በሗልም ጨዋታው ሊጠናቀቅ 16 ደቂቃዎች ሲቀሩት የቀይ መስቀል ሰራተኖች የባህር ዳር ከነማን የተጎዳ ተጫዋች ይዘው ወጥተው በቁማቸው በመጣላቸው ምክንያት ከፍተኛ ግጭት ተፈጥሮ የባህር ዳር ከነማ ቡድን ጉዳት እንደደረሰበትና ጨዋታውም መቋረጡ የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY