የእፉኝት ልጆች /ዮሃንስ ደሳለኝ-ጀርመን/

የእፉኝት ልጆች /ዮሃንስ ደሳለኝ-ጀርመን/

ድሮ ድሮ ያኔ በደርግ ዘመን በተለይ በ1970ዎቹ አካባቢ ጎላ ብሎ የወጣ አንድ አባባል ነበር “አብዩት ልጇን ትበላለች “ የሚል እናም ያ መፈክር እያደር አብዮቷ በዙሪዋ ያሉትን በልታ ጨረሰችና ሰፊውን ህዝብ ማዳረስ ጀምራ ጭራሽ ይባስ ብላ የሬሳ ዋጋ አስከፍላ መጨረሻዋ የበላችውንና የበላትን ይዛ አበው እንደሚሉት አንጣሪ ላንጣሪያ ቢደጋገፍ ተያይዞ ዘፍ ብላ ለሌላ ተረኛ በላተኛ አሳልፋ ሰጥታ አሁን ለምናየው ሁኔታ በቃን። ያሁኖቹ አብዮተኞች ደግሞ አደራረጋቸው ከመጡበት የደደቢት ጫካ ጀምሮ እየተበላሉ እዚህ ደረሱ ከላይ በርዕሴ ላይ እንደጥቀስኩት የአሁኖቹ ገዥዎቻችን የእፉኝት ባህሪይ አላችው ለግንዛቤ እንዲረዳ የዚችኑ የእባብ ዝርያ የሆነችውን እንሰሳ ባህሪይ እንይ፤ ሴትዋ ከተቃራኒዋ ጋር ግኑኝነት ሰታደርግ ብልቷ ጠባብ ሰለሆነና ሰለሚያማት ወንዱን ነክሳ ትገለውና ታረግዛለች አባት የሌላቸው ልጆችም ከዚያው ጠባብ ማህፅን መውጣት ሰለማይችሉ የእናታቸውን ሆድ ቀደው እሷንም ገለው ይወለዳሉ እንዲህም እያለ የህይወቱ ውደት ይቀጥላል (the routine goes like this) የወያኔና ተከታዩቹ ባህሪይም ከዚሁ ጋር ዝምድና አለው ከደደቢት ጀምሮ ይህንንም እየተገበሩት ይገኛሉ የእነሱ ለየት የሚያደርጋቸው መበላላቱ ከነሱም አልፎ በብሄርና በቡድን እየለየ ህዝቡ እንዲባላ መዋቅር (system)መዘርጋታችው ነው ።

አሁንማ እነሱ የሚፈልጉት አጀንዳ እየትፈፀመላችው ይገኛል እርስ በእርስ መጠላለፍ ለእነሱ ዕድሜ ማራዘሚያ እየሆነ ነው በየቦታው የፈነዳው ግጭት ለነሱ ደስታ እንጅ ምንም የሚያስፈራ የሚያስደነብር አይደለም ምክኒያቱም እነሱ ከጫካ ጀምሮ ወንድሞቻቸውን እየገደሉ አዲስ አበባ ስለደረሱ ደም እንደጠማው ጋኒን ሰላም የሆነ ምድር አይመቻቸውም ለነገሩ ግጭቱ መጠነኑን እያሰፋ መጣ እንጅ በቀደሙት ዓመታት እኮ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በቤንሻንጉል ሲታረዱና ሲሰደዱ ለአሁኑ ሁኔታ መምጣት አመላካች መሆኑን ማጤን ግድ ነበር ፣እነኝህ የእፉኝት ልጆች ስራቸው ሁሉ የጥፋት ነው በትምህርት ፖሊሲ ብትሉ ፣በኢኮኖሚ ፖሊሲ ብትሉ፣በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ብቻ ምን አለፈችሁ በሁሉም ነገረ ላይ ካለማበላሽትና ማኮላሽት ሌላ ስራ የላችውም።

በትምህርት ፖሊሲ ረገድ እነ ገነት ዘውዴ ያወጡት ፖሊሲ በሁሉም የመማሪያ ክፍሎችና ተቁማት ያሉ ተማሪዎችና አስተማሪዎች ክህሎት አጥያያቂ ሁኔታ በገባበት ወቅት እንደሽን በፈሉት ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተማሪዎችን አስመረኩ ብቻ ለማለት ምንም ዓይነት የትሟላ የስራ ዘርፍ ሳይኖር እንዲሁ በባዶ ሜዳ የተመረኩትም ተማሪዎች በስራ ማጣት ገማሹ ከቤተሰቡ ጋር ጥገኛ ሆኖ ይኖራል ሌላው ደግሞ የሚያስጠጋው ሲያጣ ያው የተለመደውን ስደት አማራጭ አድርጎ በመውሰድ አገር ለቆ ይኮበልላል በአንዲት አገር ወስጥ የተማረ የሰው ኃይል በበዛ ቁጥር ዕድገቷ የዚያኑ ያህል እንደሚጨምር ሳይታለም የተፈታ ነው በአንድ ወቅት “የኛ ሙሽራ ባለሱሪ አገባች አስተማሪ” “የኛ ሙሽራ ኩሪባችው በእንግሊዝ አናግሪችው “ ተብሎ የተገጠመላችው ምሁራን ወይም እነሱን ማግባት ምን ያህል እንደሚያስከብር የተነገረላችው ዛሬ በነእፉኝት ልጆች ክብራችው ወርዶ ማየት ምንኛ ያማል አሁን አሁን የተማረን ማዋረድ የትምህርትን ዋጋ (value) ማሳጣት ለወያኔዎቹ የዕለት ተዕለት ስራችው ሆኗል ፣አገሪቱ በአንድ ወቅት ብዙ ዋጋ ከፍላ ያስተማረቻቸው ምሁራን የሴክረታሪ ሳይንስ ምሩቅ የሆነችው ገነት ዘውዴ ያለምንም ምክኒያት በማባረር በምትኩ ካድሪዎችን በመሰግሰግ በትውልድ ላይ ቀልድ ጀመረች ጌቶቹዋም ይህ አልበቃችው ሲል ቤታችው ቁጭ ብለው ዲግሪና ዲፕሎማ በመግዛት ግማሹ ዶክተር ሲባል ግማሹ ፕሮፈሰር እየተባለ ትውልድ ላይ አላገጡ ባለፉት አምስት አስርታት ዓመት ብዙ ምሁራንን ያፈራው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዛሬ የማሃይማን መፈንጫ ሆኗል።

በኢኮኖሚ ፖሊሲውም ዘርፍ ብናይ በየዓመቱ 11%አደገ የሚባለው፣ (ቁጥሩ ለምን ሁሌ እንደማይቀየር ባይገባኝም )ግራ የተጋባው ኢኮኖሚ ውስጡ ሆነው የሚኖሩት በየቀኑ እየናረ ባለው ኑሮ ሰቆቃ ውስጥ ጨምሯችው መድረሻ ባጡበት ሰዓት መንግስት ዕድገትን በተናገረበት አፉ ሰለዋጋ ግሽበት ሲናገር የገዥዎቻችን የዕውቀት መጠን ምን ላይ እንደሆነ አመላካች ነው አማካሪ ተብየወቹ ከየትኛው ፕላኔት እንደመጡ እነሱ ብቻ ናቸው የሚያውቁት ፣በኑሮ ማሻቀብ ምክኒያትና በተያያዝ ጉዳዮች አደባባይ የወጣውን ህዝብ የእፉኝት ልጆች መልስ ጥይት ከሆነ ሰንብቷል ፣በአንዲት አገር አብዛኛውን የገበያ ስርዓት ጥቂት ግለሰቦች ከተቆጣጠሩት የመንግስት ሚና እምብዛም ነው የሚሆነው ይህም ሁኔታ በአሁኒቷ ኢትዩጵያ ተከስቱዋል የስርዓቱ ደጋፊዎች የሆኑ እንደፈለጉ ይዘርፋሉ ደስም ሲላችው ደግሞ ወደ ውጭ አገራት ያሸሻሉ ግማሹም በየቦታው በአንድ ግዜ እየበቀሉ በምናያችው ፎቆች ራሳችው በሰጡት ኪራይ ሰብሳቢ ስም ገንዘብ እየሰበስቡ በድሃው ላይ ይዝናናሉ ደሃው ደግሞ ውይ የበይ ተመልካች ይሆናል አልያም ይሰደዳል ከዚያም በተሰደደበት እንኩዋን በደል ሲደርስበት የተበላሸውና ፈሩን የለቀቀው የውጭ ፖሊሲያቸውም እኩዋን ሊታደጋቸው ይቅርና ማንነታችውን እያጣራሁ ነው የሚል መልስ እየሰጠ በትውልድ ላይ ማፌዙን ቀጥሉዋል።

አሁን ደግሞ ያው ከተነሱበት ጫካ የተጠናወታችሀው ከፉ ባህሪ ያዳቆነ ሰይጣን ሳይቀሰሰ አይቀርም እንዲሉ ይህው መበላላት ጀምረዋል ፣ባለፉት ሳምንታት እንደሰማነው ራሱ ፈጥሮት ይሄው ልክፍቱ መቃብር እስኪወስደው ድረስ ሲበጠብጠጥ የነበረው ሟቹ መለስ ሚስት ሚስኪኗና ደሃዋ አዜብ ግንባር ቀደም ተበይ ሆናለች ፣ይሄ እንግዲህ ከህወሓት መሰንጠቅ በኃላ ሁለተኛውና አነጋጋሪው ሆኗል መውጫ ቀዳዳው ሲጠብ እንደእፉኝት ልጆች የቅርብ የሆነውን ሁሉ እያስወገዱ እነሱ የእፉኝቶችሁ አባትና እናት ላይ የደረሰው ተመሳሳይ ሁኔታ እስኪመጣ እየተበላሉ መቀጠል የወያኔ የኑሮ ዘይቤ ሆኑዋል። ታዲያ እነዚህ ለቀረባችሀው ነገራቸውን ሁሉ ላወቀ አብሮ ለታገለ ባለውለታቸው ያልራሩ ለእኛ ይራራሉ ብላችሁ ታስባልችሁ?! ስለዚህ ሌላ የእፉኝት ኔትወርክ ሳይዘረጉና ለኛም ሳያቃምሱን ከወዲሁ ሆ!ብለን በአንድ ልብ ተነስተን ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ በምንችለው ሁሉ ነገር ማለትም መጻፍ ያለበትም ሳያቋርጥ እየጻፈ እያጋለጠ ፣መዋጋት ያለበትም እየትዋጋ ፣በገንዘብ ትግሉን የሚደግፍ ገንዘብ እየለገሰ ሃሳብ ያለው ሃሳቡን እየሰጠ ፣መረጃ ያለው መረጃ እያቀበለ ብቻ በተለያየ መንገድ በጠመጠቀም ግባተ መሬታችውን ማፋጠን አለብን።

LEAVE A REPLY