ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣ጄኔራሎችና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ተወሰነ

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣ጄኔራሎችና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ተወሰነ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ የወልቃይት የማንነት አስመላሽ ኮሚቴዎች፣ በ2001ዓ.ም “በመፈንቅለ-መንግስት ሙከራ” የተከሰሱት ጄኔራሎችና ሌሎች በግንቦት ሰባት፣ በኦነግ እንዲሁም “በሀይማኖት አክራሪነት” ተከሰው ጉዳያቸው በሂደትና የተፈረደባቸው 101 የፖለቲካ እስረኞች እንደፈቱ መወሰኑን ዛሬ ማምሻውን ኢቢሲ ዘገበ።

እንደ ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን(ኢቢሲ) ዘገባ፤ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት ተብለው የተጠረጠሩ 56፣ የኦነግ 41 እንዲሁም በሀይማኖት አክራሪነት የተጠረጠሩ 4 ሰዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ክሳቸው እንዲቋረጥ ከተደረገላቸው መካከል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣ ጌታቸው አዳመ፣ አታላይ ዛፌ፣ ንግስት ይርጋ፣ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌና ሌሎችም እንደሚገኙበት ታውቋል።

የኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ዛሬ በጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የመጨረሻ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ለየካቲት 22/2010 ዓ.ም ቢሰጥም ክሱ ተቋርጦ እንዲፈቱ መወሰኑ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY