የደማስቆ መንገድ /አንዱዓለም አራጌ/

የደማስቆ መንገድ /አንዱዓለም አራጌ/

—በድቅድቁ ለሊት በሐምሌ ጭለማ

በሀገር በምድሩ ፍርሃት ሲፀና

በዘውድ በመትረየስ በዘር ያልተፈታ

አውራ ሊቀ ጠበብት የተባ ብዕር ጌታ

የገባኦን ፀሐይ የፔሎን ጨረቃ

ለተገፋው ምርኩዝ ለህዝብ ጠበቃ

ሞት በነገሠበት በዚያ በጣዕር ማማ

በጠኔ መላዕክት ወገኑ ሲቀጣ

የክፉ ቀን ደራሽ የጠል ደመና

ምናቡ የማይነጥፍ የአዛውንት ገበሬ

የተኛውን ጎንታይ ሌላው ጉዱ ካሣ

መስፍን ወ/ማርያም የዳልጋው አንበሣ

የደማስቆ መንገድ የለውጥ ሃዋርያ

መጥምቁ ነፃነት የማለዳ ጮራ

የህሊና ደውል ከሩቅ የሚጣራ

የበራ ገነት የዕውቀት መሠላል

በትውልድ ጅረት በነፃነት ፀደይ

ሲያበራ የሚኖር የማይጠፋ ቀንዲል

መስፍን ወ/ማርያም ደማቅ የአጥቢያ ኮኮብ ።

ሚያዚያ 16 ቀን 2010 ዓ.ም አንዱዓለም አራጌ ለፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም የልደት በዓል የገጠመው ግጥም ።

LEAVE A REPLY